Get Mystery Box with random crypto!

ከ3 ሺሕ በላይ ጥይት ከነተጠርጣሪዎቹ በቀጥጥር ስር ዋለ!! የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መ | ETHIO-MEREJA®

ከ3 ሺሕ በላይ ጥይት ከነተጠርጣሪዎቹ በቀጥጥር ስር ዋለ!!

የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት ባደረጉት ክትትል በአንድ የእንጨት ሥራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ከ3 ሺሕ በላይ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ ቀለበት መንገድ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ጥይት ስለመኖሩ ከሕዝብ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ሲከታተሉ ቆይተው ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በህግ አግባብ በድርጅቱ ውስጥ ባደረጉት ብርበራ በ4 ማዳበሪያ ተጠቅልሎ በድብቅ የተቀመጠ 1 ሺሕ 98 የብሬን እና 2 ሺሕ 162 የክላሽ ጥይት ተይዟል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ኅብረተሰቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ሊያስከትል የሚችለውን ሀገራዊ ጉዳት ተገንዝቦ የዚህ ህገ ወጥ ተግባር ተሳታፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየሰጠ ያለውን ጥቆማ እና መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ