Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 132.13K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-04-19 12:30:09
የመንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው #የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ልዑክ ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ።

የልዑካን ቡድኑ ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጄቫ፣ ከአለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የምስራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ሃላፊ ቪክቶሪያ ክዋክዋ፣ ከዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የአይዳ ሃላፊ ከሆኑት አኪህኮ ኒሺዮ እና ከሌሎች የዓለም ባንክ እና የአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መገናኘቱ ተጠቁሟል።

በተደረጉ ውይይቶችም ላይ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል፣ ስለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታና የወደፊት ተስፋ፣ የተረጋጋ አገራዊ ጥቅል ኢኮኖሚ ለማምጣት እየተሰራ ስላለው የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትና የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ምርታማነትን ማሳደግ እና የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚን ለማሳለጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መሆናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሁለቱም ተቋማት ኢትዮጵያ እየወሰደቻቸው ያሉትን እርምጃዎች ማለትም ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ለመቅረፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁለተኛ ምዕራፍ ሀገር አቀፍ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አድንቀዋል ሲል ሚኒስቴሩ በመረጃው አካቷል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
17.3K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 12:06:08 አዲስ አበባ እና አቅራቢያ ለምትገኙ በሙሉ!!

የOnline እቃዎችን በብዛት ዋጋ ከኛ ያገኛሉ

Amazon,Alibaba,Aliexpress, በኢትዮጵያ

Join us ከታች ይጫኑ፣ አሁኑኑ ይቀላቀሉ!

https://telegram.me/AddisEka1

https://telegram.me/AddisEka1

https://telegram.me/AddisEka1

https://telegram.me/AddisEka1

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ! በቅናሽ ይሸምቱ!

High Quality  Big Discount #Ethiopia
  ተአማኒነት እና ጥራት መገለጫችን ነው!
15.3K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 11:19:18
Adjustable Laptop & Tablet Stand
High Quality(ብረት የሆነ)

የቀሩት ጥቂት ናቸው!

ላፕቶፕ ጭን ላይ አስቀምጠው መጠቀም ለከፋ ጉዳት እንደሚያጋልጥ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፤ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ተጣጣፊ የላፕቶፕ ፣ ታብሌት Holder በተመጣጣኝ ዋጋ ገዝተዉ ጤንነቶን ይጠብቁ።

ዋጋ፦  1200 ብር! Free delivery

ሱቅ ሲመጡ ና ብዛት ለምፈልጉም ቅናሽ አለን።
  0901882392    0931448106
15.9K viewsedited  08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 09:50:35
12pcs Silcone Kitchen Set

ከፍተኛ ሙቀት የሚቋቋሙ
ከሲልከን የተሰሩ
የማይመነችኩ

ዋጋ ፣ 1700 ብር / ዴሊቨሪ 150ብር

0901882392   
0931448106

አድራሻ፣ ከ4ኪሎ መገናኛ መንገድ ላይ ቤሊየር መብራቱ ጋር ከአቤኔዘር ህንፃ ፊትለፊት፣ አል-ዘይን ህንፃ 207ቁ

  በTelegram ለማዘዝ ይጠቀሙ
         @Antenehg1
17.5K viewsedited  06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 18:37:09
ከባንክ ብድር ለማግኘት የሞተ ሰው የወሰደችው ብራዚላዊት ተያዘች!

በላቲን አሜሪካዋ ሀገር ብራዚል ከሰሞኑ በባንክ እንግዳ ነገር ተከስቷል።

የ42 አመቷ ኢሪካ ቬይራ ኑኔስ በሪዮ ዴጄኔሮ ባንጉ በተባለ አካባቢ ወደሚገኝ ባንክ የ68 አመት አዛውንት በዊልቸር እየገፋች ታመራለች።ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ የተባሉት አዛውንት “አጎቴ ናቸው፤ ሞግዚያቸው ሆኘ የምንከባከባቸውም እኔ ነኝ” በማለትም ብድር ፈልገው እንደመጡ ለባንኩ ሰራተኞች ትናገራለች።

3 ሺህ 200 ዶላር ብድር ፈልገዋል የተባሉት አዛውንት ግን ዊልቼር ላይ ከመቀመጣቸው ባሻገር ትንፍሽ አላሉም።

“አጎቴ ትሰማኛለህ? መፈረም አለብህ፤ የማትፈርም ከሆነ ብድሩን መውሰድ አትችልም፤ ፈርም እንጂ፤ ራሴን አታሳምመኝ” ስትልም ከአዛውንቱ ምላሽ የለም። የባንኩ ሰራተኞች በሁኔታው ግራ በመጋባት ስለጤንነታቸው ቢጠይቁም “ደህና ነው” የሚል ምላሽ መስጠቷን የብራዚል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። አጠቃላይ የአዛውንቱ ሁኔታ ያጠራጠራቸው የባንኩ ሰራተኞች ወዲያው ለአስቸኳይ ጊዜ ሰራተኞች እና ለፖሊስ መደወላቸውን ተከትሎ የ42 አመቷ ጎልማሳ አሳዛኝ ድርጊት ተጋልጧል።

እንስቷ በዊልቼር እየገፋች የወሰደቻቸው ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ ህይወታቸው ማለፉ ይረጋገጣል።አስከሬናቸውን ይዛ ባንክ ያመራችው ኑኔስ አምታትታም ቢሆን በሟቹ ስም ለመውሰድ በማሰብ መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።ጠበቃዋ ግን ፖሊስ መረጃውን አዛብቶታል፤ አዛውንቱን ባንክ እስኪገቡ ድረስ ህይወታቸው አላለፈም በሚል አስተባብለዋል። ፖሊስ ግን ኑኔስ አዛውንቱ አጎቴ ነው ማለቷ ሀሰት መሆኑንና ሞግዚት ነኝ በሚል ከባንክ ለማጨርበር ያደረገችው ሙከራም በወንጀል ያስጠይቃል ብሎ በቁጥጥር ስር አውሏታል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
19.7K viewsedited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 14:52:13
ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ መፍቀዱ ተሰምቷል፡፡

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ  ማቅረቡን ፋና ዘግቧል

በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል።ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ፈቅዷል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
19.8K viewsedited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 12:31:13
የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ባለው ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ "የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተሰማርቷል" ብሏል።

ተቋሙ የባህር ሀይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች ግዳጃቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።

ማሪን ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሀይል መሆኑንም ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ መናገራቸውን የሀገር መከላከያ ስራዊት ገልጿል። ማሪን ኮማንዶ ከአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በወሰዳቸው እርምጃዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም በዚሁ ዘገባ ላይ ተጠቅሷል።

የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የ"ፋኖ" ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
19.5K viewsedited  09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 11:55:50
የውጭ ባለሀብቶች በጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ

ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ ተደረገ፡፡

በዚህም መሰረት የውጭ ባለሀብቶች በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

#የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው፤ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ የውጭ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢ ንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት ይችላሉ፡፡

የጅምላ ንግድን በተመለከተ ከማዳበሪያ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያሟሉ ለአገር ውስጥ ባለሃብት በተከለሉ ሁሉም የችርቻሮ ንግድ ስራዎች መሳተፍ እንዲችሉ መፈቀዱም ተጠቅሷል። በጉዳዩ ላይ በባለድርሻ አካላት የተካሄዱ ዝርዝር ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ መሠረታዊ የፖሊሲ ለውጥ ያደረገው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድም አዲስ የአፈፃፀም መመሪያ ማጽደቁን ከኢቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
19.2K viewsedited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 22:42:46
#ጤናመረጃ

ቲማቲም ለፊት ጥራት ያለው አስደናቂ ጥቅም!!

ቲማቲም ለቆዳችን እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አለው፤ ይህን ንጥረ ነገር ደግሞ ለፊት ጥራት ተብለው በውድ ዋጋ የሚሸጡ መዋቢያዎች ይጠቀሙበታል፡፡

በቀላሉ የምናገኘው ቲማቲምን በመጠቀም ቡጉርን፣ የቆዳ ጥቁረትንና ጥቁር ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ይረዳናል፣ በተጨማሪም ቲማቲም የቆዳን እርጅና እና መሸብሸብ ፍጥነትን የመቀነስ ችሎታ አለው፡፡

ለማዘጋጀት አስፈላጊ ነገሮች -

- 1 ቲማቲም
- 2 የሻይ ማንኪያ ስኳር
- 2 የሻይ ማንኪያ ማር
- 1 መለስተኛ የቡና ሲኒ >>

አዘገጃጀት

1) በመጀመርያ የፊታችን የቆዳችን ቀዳዳዎች መከፋፈት ስላለባቸው ፊታችንን በሙቅ ውሀ እንፋሎት መታጠን፡፡

2) ቲማቲሙን ይቆርጡና በሲኒ ላይ ይጨምቁታል፡፡
3) ጭማቂው ላይ ቅድሚያ ስኳሩን ቀጥሎ ማሩን ይጨምሩና ያዋህዱታል፡፡

4) ውህዱን ፊትዎ ላይ በስሱ ይቀቡታል ፡፡
5) ለ 2 ደቂቃ በዝግታ ያሹታል፡፡
6) ለተጨማሪ 2 ደቂቃ ደግሞ ባለበት ይተውታል፡፡

7) ባጠቃላይ ከ 4 ደቂቃ በኋላ በ ቀዝቃዛ ውሀ ይታጠቡታል፡፡ ማስጠንቀቂያ:- ለቲማቲም ሆነ ከላይ ለተጠቀሱት ውህዶች አለርጂክ ከሆኑ እንዲጠቀሙት አይመከርም፡፡ 
......
በተጨማሪም ቲማቲም ለቆዳ ጤንነት ያለውን ጥቅም በቀላሉ ሞክሮ ማየት ካስፈለገ የሚከተለውን ማድረግ ይቻላል።

ከ8 እስከ 12 የሚሆኑ ቲማቲሞችን ልጦ የልጣጩን የውስጠኛ ክፍል ፊት ላይ መለጠፍ፡፡ ቢያንስ ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ልጣጮቹን አንስቶ ፊትን መታጠብ፡፡ ከዛም ይህንን በተደጋጋሚ በማድረግ ለውጡን ማስተዋል እንችላለን።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.5K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 21:55:54
አረብ ኤምሬትስ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ዝናብ ማስተናገዷ ተገለጸ።

የዝናብ መጠን መመዝገብ ከጀመረበት 1949 ወዲህ ከፍተኛ ነው የተባለው ዝናብ በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ጎርፍ አስከትሏል።የኤምሬትስ ብሄራዊ የሜትዮሮሎጂ ማዕከል በትናንትናው እለት ለ24 ስአታት የተመዘገበው የዝናብ መጠን ኤምሬትስ ከተመሰረተችበት 1971ም ሆነ በአካባቢው የዝናብ መጠን መመዝገብ ከጀመረበት 1949 ወዲህ ከፍተኛው ነው።

ማዕከሉ ከፍተኛው የዝናብ መጠን (254 ሚሊሜትር) በአል አይን “ካትም አል ሻክላ” በተባለው አካባቢ መመዝገቡን ገልጿል።የሜትዮሮሎጂ ተቋሙ ዝናቡ የኤምሬትስን የገጸምድር ውሃ ክምችት እንደሚያሳድገው መጠቆሙንም ዋም የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ጎርፍ ያስከተለ ሲሆን፥ በአለማችን ስራ ከሚበዛባቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የዱባይ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉ ነው የተገለጸው።

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
14.3K viewsedited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ