Get Mystery Box with random crypto!

አረብ ኤምሬትስ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ዝናብ ማስተናገዷ ተገለጸ። የዝናብ መጠን መመዝገብ ከጀመ | ETHIO-MEREJA®

አረብ ኤምሬትስ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ዝናብ ማስተናገዷ ተገለጸ።

የዝናብ መጠን መመዝገብ ከጀመረበት 1949 ወዲህ ከፍተኛ ነው የተባለው ዝናብ በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ጎርፍ አስከትሏል።የኤምሬትስ ብሄራዊ የሜትዮሮሎጂ ማዕከል በትናንትናው እለት ለ24 ስአታት የተመዘገበው የዝናብ መጠን ኤምሬትስ ከተመሰረተችበት 1971ም ሆነ በአካባቢው የዝናብ መጠን መመዝገብ ከጀመረበት 1949 ወዲህ ከፍተኛው ነው።

ማዕከሉ ከፍተኛው የዝናብ መጠን (254 ሚሊሜትር) በአል አይን “ካትም አል ሻክላ” በተባለው አካባቢ መመዝገቡን ገልጿል።የሜትዮሮሎጂ ተቋሙ ዝናቡ የኤምሬትስን የገጸምድር ውሃ ክምችት እንደሚያሳድገው መጠቆሙንም ዋም የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ጎርፍ ያስከተለ ሲሆን፥ በአለማችን ስራ ከሚበዛባቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የዱባይ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉ ነው የተገለጸው።

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja