Get Mystery Box with random crypto!

ኢራን ሌሊቱን በጀመረችው ቀጥተኛ ጥቃት ወደ እስራኤል በርካታ ቁጥር ያላቸው ድሮኖችን እና ሚሳዔሎች | ETHIO-MEREJA®

ኢራን ሌሊቱን በጀመረችው ቀጥተኛ ጥቃት ወደ እስራኤል በርካታ ቁጥር ያላቸው ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን መተኮሷን አስታውቃለች።

ኢራን በኢምባሲዋ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስራኤልን እንደምትበቀል ስትዝት የቆየችው ሲሆን በዛሬው እለት መጠነ ሰፊ የድሮን እና ሚሳዔል ጥቃት ወደ ቴልአቪቭ መክፈቷን አስታውቃለች።እስራኤል እንደስታወቀችው ከ300 በላይ ድሮኖች አና ሚሳዔሎች ከኢራን፣ የመን እና ኢራቅ ውስጥ ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል።

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አድሚራል ዳንኤል ሀግሪ፤ ወደ እስራኤል ከተተኮሱ ከ300 በላይ ድሮኖና ሚሳኤሎች ውስጥ 99 በመቶውን ማክሸፍ እንደተቻለ ተናግረዋል።በአሜሪካ፣ በብሪታኒያ እና ፈረንሳይ እርዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢራን ድሮኖችና ሚዔሎች ድንበር ላይ ተመትተው ወድቀዋል።

እስራኤል ተከላከልኩ ትበል እንጂ የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤል አየር መከላከያዎችን ጥሰው በመግባት በርካታ ኢላማዎችን መምታታቸው መረጃዎች እየወጡ ነው።ኢራን ካህይበር የተባለው አደገኛው ሚሳዔል ወሳኝ የሆነ የእስራኤል የአየር ኃይል ጣቢያን መምታቱን የኢራን ዜና አገልግሎት አስታውቋል።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል በኤክስ ገጽ (በቀድሞ ትዊተር ገጽ) ባወጣው መረጃ አነስተኛ ቁጥር ላቸው ቦታዎች መመታታቸውን እና በጣም አነስተኛ መጠን ያላቸው ጉዳቶች መድረሳቸውን አረጋግጠቷል።

የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ሀገራው ከኢራን የሚሰነዘርባትን ማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ እንደምትቆም ገልጸው፤ “እኛን የጎዳ ሁሉ ይጎዳል” ሲሉ ዝተዋል።የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ከህሚኒ በሰጡት አስተያየት “ጺዮናዊው አስተዳደር ይቀጣል” ሲሉ የዛቱ ሲሆን፤ በተመድ የኢራን ተወካይ በበኩላቸው አሜሪካ በዚህ ጉዳይ ጣልቃ እንዳትገባ አስጠንቅቀዋል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja