Get Mystery Box with random crypto!

አቶ አብነት ገብረመስቀል በቦሌ ታወርስ ላይ ያላቸውን ድርሻ ለቀው እንዲወጡ ተፈረደባቸው አቶ አብ | ETHIO-MEREJA®

አቶ አብነት ገብረመስቀል በቦሌ ታወርስ ላይ ያላቸውን ድርሻ ለቀው እንዲወጡ ተፈረደባቸው

አቶ አብነት በነሃሴ 2014 ዓም አቅርበውት በነበረው ክስ የቀድሞ የቅርብ ወዳጃቸው እና አጋራቸው የሆኑት ሼክ መሃመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ በቦሌ ታወር ያላቸውን ድርሻ ለቀው እንዲወጡ ወይም ድርጅቱ እንዲፈርስ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ባሳለፍነው ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2016 የዋለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቦሌ ታወርስ የተባለው እና በወሎ ሰፈር አካባቢ የህንጻ ግንባታ ያለው ድርጅት እንዳይፈርስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም አቶ አብነት የሚገባቸው ድርሻ ተከፍሏቸው ከድርጅቱ ለቀው እንዲወጡ ወስኗል፡፡ቢሊየነሩ ሼክ መሃመድ በቦሌ ታወርስ ላይ የ60 በመቶ ድርሻ ያላቸው ሲሆን ቀሪው በቀድሞ አጋራቸው የተያዘ ነው።(ካፒታል)

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja