2024-04-05 17:46:28
በአዲስ አበባ በነገው ዕለት የለውጡን ዓመታት የሚደግፍ ነው የተባለው ሰልፍ ሊካሄድ ነው!!
በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት ለሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ።
በሰልፉ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶችንም ግብረ ኃይሉ ይፋ አድርጓል። በዚህም ነገ ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን 2016 ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሄራዊ ቴአትር ወደ ወደ መስቀል አደባባይ ሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ፡፡
• ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
• ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ
• ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት ፡፡
• ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ፡፡
• ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት ላይ
• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ
• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ
• ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ
አካባቢዎች ዝግ ስለሚሆኑ አማራጭ መንገድ መጠቀም አስፈላጊ ነው ተብሏል። በእነዚህ አካባቢውችም ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰልፉ ፍፃሜ ድረስ ተሽከርካሪ ማቆም እና ማሳደር ተከልክሏል።
- ETHIO-MEREJA -
T.me/ethio_mereja
17.4K viewsedited 14:46