Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.93K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2024-04-10 12:02:00
ሰበር ዜና!፡
የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል።

" ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው በከተማ ተገድለው ተጥለው ነው የተገኙት " ተብሏል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ታስረው በ100 ሺህ ብር በዋስ ከእስር ተለቀው ነበር። ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይተ ተመተው ተገድለዋል። ፓርቲያቸው እስካሁን ስለግድያው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja
19.0K viewsedited  09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 09:01:58
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው ለኢድ-አልፈትር በዓል በሰላም አደረሳቹ!

ኢትዮ መረጃ በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንልዎ ከልብ ይመኛል!

ዒድ ሙባረክ! Eid Mubarak
18.2K views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 22:20:16
Are you here? I asked for a private link from the admins of this channel:
ZERO RISK SGINALS with QUICK PROFIT

https://t.me/+CkJDUU9aMwY5YjVl
https://t.me/+CkJDUU9aMwY5YjVl
https://t.me/+CkJDUU9aMwY5YjVl

Private group, DON'T JOIN if you're not ready to change your life!
19.0K views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 13:25:09
በሰሜናዊ ጅቡቲ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አልፏል።

በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ ጎዶሪያ በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ 60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ 38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን በጅቡቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
19.8K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 20:29:50
ዛሬ በሳዑዲ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል!

ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

    ETHIO-MEREJA
   
T.me/ethio_mereja
14.5K viewsedited  17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 16:02:42
ባህርዳር

በአማራ ክልል መዲና በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል።

ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት ፥ አቶ ሙሄ ፣ ልጃቸው አበባዉ ሙሄ ፣ ሽኩር ሙሄ ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም።

በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን " ሀሩን ሚዲያ " ዘግቧል።እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።

    ETHIO-MEREJA
   
T.me/ethio_mereja
16.8K viewsedited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 13:07:48
ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር ታካሂዳለች - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

ኢትዮጵያ #የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር እንደምታካሂድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ገለፁ።

ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በፊት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እንቅስቃሴ ብትጀምርም በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በሌሎች ምክንያቶች ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን ጥረት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከቆመበት ለማስቀጠል የተለያዩ ተግባራት እያከናወነች ነው ሲሉ አቶ ገብረ-መስቀል ጫላ መናገራቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከተከናወኑ ተግባራት መካከልም የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሐምሌ 2015 ዓ.ም ወደ ጄኔቫ አቅንተው ከድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፤ በውይይቱም ኢትዮጵያ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የድርድር ሂደቱ እንዲጠናቀቅና የድርጅቱ አባል እንድትሆን ከሥምምነት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።

በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር ለማድረግ ፍላጎት ካላቸው ከአባል አገራቱ 180 የሚጠጉ ጥያቄዎችና 9 ሰነዶች መቅረባቸውን ተናግረዋል።በቅርብ ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ በሚያመቻቸው መድረክ ድርድሩ እንደሚጀመር ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

    ETHIO-MEREJA
   
T.me/ethio_mereja
16.3K viewsedited  10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 11:58:57
ዋው የሚያስብሉ የግድግዳ ምስሎች

Shine laminated(የሚያብረቀርቅ)ናቸው።
በውሀ የሚፀዳ እና HD ማራኪ ናቸው!
በቀላሉ ባለው ማንጠልጠያ ሚሰቀል!!

     በትዛዝ በ3ቀን እናደርሳለን።

  ዋጋ :-  1.50*80 - 3500ብር
  ዋጋ :-  1.20*60 - 3000ብር

አድራሻ 4killo/ቀበና #ቤሊየር አልዘይን ህንፃ 207ቁ

     0901882392 /
     0931448106

ተጨማሪ T.me/Dinkwallarts
ON HAND - የጌታ እራት አለ።
14.6K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 11:13:14
የቦይንግ አውሮፕላን የሞተር ሽፋን በበረራ ላይ ተገንጥሎ መውደቁን ተገለጸ

የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ የሞተሩ ሽፋን ተገንጥሎ መውደቁ ተነገረ።

ወደ አሜሪካዋ ሁስቶን በረራ ላይ የነበረው አውሮፕላ ቸግሩ ማገገሙን ተከትሎ ዴንቨር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ መገደዱ ተነግሯል።135 መንገደኞችንና 6 የበረራ አባላት ያሳፈረው አውሮፕላን ዴንቨር ለማረፍ ከመደገጉ በፊት 10 ሺህ 300 ጨማ ከፍታ ላይ እየበረረ እንደነበረም ነው የተገለጸው።ችግሩ ማጋጠሙን ተከትሎ የአሜሪካ የአየር መንግድ ተቆጣጣሪዎች አፋጣኝ ምርመራ እያደረጉ መሆኑም ተነግሯል።

የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ በቦይንግ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ ያጋጠመውን ችግር የአየር መንገዱ የጥገና ቡድን እንደሚመረምረው አስታውቀዋል።አየር መንገዱ ለእንደዚህ አይነት ክፍሎች ጥገና ኃላፊነት እንዳለበት አረጋግጧል።ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን የተመረተው በፈረንጆቹ በ2015 መሆኑን የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) መረጃ ያመለክታል።

ቦይንግ ኩባንያ የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ በቦይንግ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ ባጋጠመው ችግር ዙሪያ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

ኩባንያው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ምርቶች ላይ ካከናወናቸው 89 የጥራት ምርመራዎች ላይ በ33ቱ ጉድለት እንደተገኘበት መገለጹም ይታወሳል።

    ETHIO-MEREJA
   
T.me/ethio_mereja
14.6K viewsedited  08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 09:57:09
YANGOን የጉዞ ምርጫዎ ያድርጉ

ኪሶን ሳይጎዱ ከተማዋን ይንሸራሸሩ! ከYango ጋር፣ ከ72 ብር ጀምሮ ከምቾት እና ከቁጠባ ጋር ይጓዙ!

Yangoን ከApp Store ወይም ከPlay Store ያውርዱ፤ ወይም ወደ 8610 ይደውሉ።

መተግበሪያወን በማውረድ ከመጀመሪያዎ 3 ጉዞዎች ላይ 30% ቅናሽ ያግኙ!
14.9K views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ