Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና!፡ የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግ | ETHIO-MEREJA®

ሰበር ዜና!፡
የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል።

" ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው በከተማ ተገድለው ተጥለው ነው የተገኙት " ተብሏል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ታስረው በ100 ሺህ ብር በዋስ ከእስር ተለቀው ነበር። ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይተ ተመተው ተገድለዋል። ፓርቲያቸው እስካሁን ስለግድያው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja