Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ | ETHIO-MEREJA®

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

"በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና በታዋቂ ሰዎች ላይ የሚደረገው ግድያ ቀጥሏል " ያለው ኦነግ የታወቂውና ተወዳጁ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሳይረሳ እና ቤተሰቦቹ እስካሁን ፍትህ ሳያገኙ የበቴን ኡርጌሳን ግድያ መስማት እጅግ አሳዛኝ ነው ብሏል።

ጃል በቴ በተወለዱበት መቂ ከተማ #በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን በመግለጫው ላይ አመልክቷል። "ምንም እንኳን ሁኔታው ​​​​ለሁላችን እጅግ በጣም ከባድ ቢሆንም በግድያው ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረግን ነው " ሲል ገልጿል። "ሁሉም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች እና ሰላም ወዳድ ህዝቦች አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲያደርጉ " ጥሪ አቅርቧል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja