Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜናዊ ጅቡቲ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ በጅ | ETHIO-MEREJA®

በሰሜናዊ ጅቡቲ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አልፏል።

በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ ጎዶሪያ በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ 60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ 38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን በጅቡቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።