Get Mystery Box with random crypto!

የመንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎ | ETHIO-MEREJA®

የመንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው #የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ልዑክ ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ።

የልዑካን ቡድኑ ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጄቫ፣ ከአለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የምስራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ሃላፊ ቪክቶሪያ ክዋክዋ፣ ከዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የአይዳ ሃላፊ ከሆኑት አኪህኮ ኒሺዮ እና ከሌሎች የዓለም ባንክ እና የአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መገናኘቱ ተጠቁሟል።

በተደረጉ ውይይቶችም ላይ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል፣ ስለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታና የወደፊት ተስፋ፣ የተረጋጋ አገራዊ ጥቅል ኢኮኖሚ ለማምጣት እየተሰራ ስላለው የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትና የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ምርታማነትን ማሳደግ እና የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚን ለማሳለጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መሆናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሁለቱም ተቋማት ኢትዮጵያ እየወሰደቻቸው ያሉትን እርምጃዎች ማለትም ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ለመቅረፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁለተኛ ምዕራፍ ሀገር አቀፍ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አድንቀዋል ሲል ሚኒስቴሩ በመረጃው አካቷል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja