Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል በኢራን ላይ ልትወስድ ባሰበችው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገለጸች ኢራን ሶ | ETHIO-MEREJA®

እስራኤል በኢራን ላይ ልትወስድ ባሰበችው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገለጸች

ኢራን ሶሪያ በሚገኘው የቆንስላ ፅህፈት ቤቷ ላይ ለተቃጣባት ጥቃት ቅዳሜ ሌሊት እስራኤል ላይ 300 ሚሳኤሎችና ድሮን ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ እስራኤል ለምትወስደው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገልጻለች።

አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ ፕሬዝዳንት ጆው ባይደን እስራኤል ልትወስደው ያሰበችው የአጸፋ እርምጃን በጥንቃቄ እንድታጤነው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ማሳሰባቸው ነው የተገለጸው።

ፕሬዝዳንት ባይደን እስራኤል ከኢራን የተቃጣባትን ጥቃት በአሸናፊነት መወጣቷን የጠቀሱ ሲሆን በዋናነት በአሜሪካና አጋሮቿ እገዛ 99 በመቶ የሚሆኑት ጥቃቶች በሚሳኤል መከላከያ መክሸፋቸውን በማሳያነት አቅርበዋል።

የአሜሪካ የብሔራዊ ጸጥታ ቃል አቀባዩ ጆን ኪርቢ በበኩላቸው አገራቸው በቀጣናው ግጭቱ እንዳይስፋፋ ለእስራኤል አቋሟን ግልፅ ስለማድረጓን ገልጸዋል።

አሜሪካ ለኢራንም በተዘዋዋሪ የዲፕሎማሲያዊ መረጀ ልውውጥ ተመሳሳይ መልዕክት እንዳስተላለፈች ነው የተነገረው። የእስራኤል የጦር ካቢኔ በኢራን ላይ ሊወሰድ ስለሚገባው የአጸፋ እርምጃ ዙሪያ ተወያይቶ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መበተኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja