Get Mystery Box with random crypto!

የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ በኢትዮጵ | ETHIO-MEREJA®

የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ የተሽከርካሪ ድጋፉን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስረክበዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፤ ከጃፓን መንግስት በድጋፍ የተገኙ ተሽከርካሪዎች፤ ኮሚሽኑ በተለያዩ ክልሎች የሚያከናውናቸውን የመስክ ስራዎች ለማቀላጠፍ ያግዛሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ መሰረታዊ በሚባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የዝግጅት ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኗንሠ ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው እንደገለጹት ጃፓን ለኮሚሽኑ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች።(ኢዜአ)

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja