Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
የሰርጥ አድራሻ: @etconp
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.50K
የሰርጥ መግለጫ

🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
📨ሃሳብ እና ኣስተያየት @Philemona7 ፃፉልን
📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp
📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ:- @ETCONpDigitalLibrary_Bot

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-09 19:31:01
በጅማ ከተማ እየተሰራ የሚገኘው ፓርክ

በኦሮሚያ ክልል የጅማ ከተማ መስተዳደር በከተማው ፓርክ እየገነባ እንደሆነ አስታወቀ ፓርኩ በውስጡ የሚይዘው Artificial lake, walk way, children playground, water fountain, water pond, cafe, shops በውስጡ እንደሚያካትት ተገልፇል።

@etconp
2.5K viewsItoophiyaa‍ , 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 17:30:13
የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ

የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ማዘጋጃ ቤት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት አዲስ ባወጣው የከተሞች የተቀናጀ ፕላን፤ የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ በሦስት ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በአስር ወረዳዎች እንድትደራጅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድርግ በተሰራው ሥራ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 46 አዲስ ፕሮጀክቶች እና 26 ነባር በድምሩ 72 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ኀላፊ ገብሬ ዳቢ ተናግረዋል፡፡

እነዚህም የመንገድ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ ፣የጋር መኖሪያ ቤቶች፣ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የውሀ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙባቸው ተናግረዋል፡፡

አብዛኞቹ ሥራዎች በዚህ ዓመት ተጠናቀው አገልግሎት እንደሚጀምሩ የገለጹት ኀላፊው፤ ፕሮጀክቶቹ በመንግሥት በጀት፣ባለ ሀብቶች በሚያደርጉት ልገሳ እንዲሁም በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተሰሩ እንደሚገኙም በመጠቆም፤ ከተጠናቀቁ በሁዋላ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እና ማራኪ ማድረግ፣ ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የሕብረተሠብን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እንዲሁም የነዋሪውን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

ለፕሮጀክቶቹ ተሰጥቶ እየተሠራ ያለው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ወደፊት ከተማዋን በምሥራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
2.5K viewsItoophiyaa‍ , 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 08:02:03
የኢትዮጵያ ኪነ-ህንፃ እድገት ግስጋሴ ወደኋላ ነዉ ሲሉ የአርክቴክትር ባለሙያዎች ተናገሩ

የኢትዮጵያ ቀደምት ስነ-ህንጻዎች የሀገሪቱ የስልጣኔ ማሳያ ተደርገው ቢወሱም እርሱን ማስቀጠል አለመቻሉን ከአራዳ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡

አሁን ያሉ ግዙፍ ህንጻዎች በአይነታቸው ቢበዙም በታሪክ፣ ባህል እና ፍልስፍና ያላቸው ውክልና ግን አናሳ ነው፤ ይህም የኢትዮጵያ ኪነ-ህንፃ እድገት ግስጋሴ ወደኋላ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

ባለሙያዎቹ አክለውም ይህን ለማሻሻል ከተፈለገ የኪነ-ህንጻ ትምህርቱን ሙሉ በሙሉ ከዉጭ ባለመቅዳት ከእኛ አዉድ ጋር እንዲጣጣም ማሻሻል፣ ለማስተር ፕላን መገዛት፣ በአርክቴክት ዙሪያ የህብረተሰብ አስተሳሰብ ማስተካከል ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

@etconp
271 viewsItoophiyaa‍ , 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 07:30:55
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ ድርጅት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት any Size & thickness
ጄ ቦልት

ሌሎች ከ ብረታ ብረት ጋር የተያያዙ ስራዎች [modefic] እንሰራለን።

ብረታብረት እንገዛለን እንሸጣለን።

ስልክ 0994941706 ወይም 0910379303 ደውለው ያግኙን
ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦ ቁ 1.መርካቶ
ቁ.2 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት
401 viewsItoophiyaa‍ , 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 18:25:27
አቡ ዳቢ የ2023 የመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪካ "ስማርት" ከተማ ተባለች

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከተማዋ አቡ ዳቢ ከመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪካ ሀገራት አንደኛ ስማርት ከተማ ሆናለች።

በስዊዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ልማት ኢንስቲትዩት ባወጣው የ2023 የስማርት ከተማ መለኪያ መሰረት ነው አቡ ዳቢ ቀዳሚውን ደረጃ የያዘችው።

@etconp
1.7K viewsItoophiyaa‍ , 15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 15:30:18 ሸጎሌ ስለሚገኘው አዲሱ የኢቢሲ ኮምፕሌክስ ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ በዚህ ወር መጨረሻ ይመረቃል !
...
የሰፈር ስያሜ ፤ ሼህ ኦጀሌ ( ሸጎሌ )
ሼህ ኦጀሌ የቤንሻንጉል ጉሙዝን አከባቢ ሲያስተዳድሩ የነበሩ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጅ ነበሩ። እኝህ ሰው ከአፄ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ለማዕከላዊው መንግስት ታማኝ ሆነው አከባቢውን ከጠላት ወረራ ሲከላከሉ ኖረዋል። በዚህም የተነሳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ሸጎሌ የሚባለው አከባቢ ቤተ-መንግስት አላቸው። በዚህም ምክንያት ሰፈሩ በስማቸው ሼህ ኦጀሌ ተባለ፤ በጊዜ ብዛትም ወደ ሸጎሌ ሊለወጥ ችሏል።
...
አጠቃላይ መረጃ

- ጠቅላላ የቦታ ስፋት 10 ሺ ሄክታር
- ስፍራው የሜቴክ የነበረ
- 1983 ዓ/ም የሸጎሌ ፍንዳታ የተከሰተበት
- ዘጠኝ የሬዲዮና ቲቪ ስቱዲዮና ቢሮ የያዙ ሁለት ህንፃዎች ፣ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ፣ ክበብ ፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ፣ ግራር ጋርደን ፣ አንፊ ትያትር ፣ የአራት ኪ/ሜ የመንገድ ኔትወርክ ፣ የያዘ
- ከተጀመረ አንድ ዓመት አካባቢ ሆኖታል
...
የዲዛይን ፍልስፍና

- ምቹ የስራ ከባቢ ግቢ
- የቀረፃ አማራጭ እና የከተማ ግብርናን ያቀናጀ ሀይቅ ፤ ለውበት ለዓሳ እርባታ ፣ ለፕሮግራም ቀረፃ
- ስፖርት ፊልድ ፣ ኮንሰርት ፣ ለሰራተኞች መዝናኛ ግቢ አቀናጅቶ የያዙ
- በሀገር ውስጥ ማቴሪያልና ኮንትራክተሮች የተሰራ
...
ስቱዲዮና ህንፃ

- የኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክን የሚያሳይ ሙዚዬም
- ግልፅና አርጎኖሚክ የቢሮ አደረጃጀት
- ማንበቢያ ፣ ኢዲቶሪያል ሩም ፣ ኤዲቲንግ ወርክስቴሽንና ስቱዲዮ ( all in one news studio Design) ሴትአፕ የያዙ
- ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ
- ብሉንበርግ ዲዛይን ወርክስቴሽን ቴብል
...
የሬዲዮ ፣ መዝናኛ እና ቋንቋዎች ህንፃ
- ሦስት የሬዲዮ ስቱዲዮ ፣ ሁለት ሃይብሪድ ስቱዲዮና ሁለት የቴሌቪዥን ስቱዲዮ
- የሚድያ ኮንቨርጀንስን ታሳቢ ያደረገ የሬዲዮና ሃይብሪድ ዲዛይን
- ምቹና ሳቢ የሃላፊዎች ቢሮ
- መንትያ የቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች (ስምንት ሜትር ቁመት ፣ ሦስት ደረጃ ሳውንድ ፕሩፍ )
- ከተፈጥሮ ጋር የተዋሃዱ
- በቅርቡ ተመርቆ መደበኛ ስርጭቱን የጀመረው የልጆች ዓለም የቴሌቪዥን ጣቢያ ያካተተ
...
የስፖርት ፊልድ

- የእግር ኳስ ሜዳ አራት ደረጃ ያለው ፣ ለኮንሰርት በሺዎች የሚቆጠሩ ታድሚያንን ማስተናገድ የሚችል
- ስድስት መቶ ሰዎችን የሚይዝ አንፊ (የሜዳ ቴኒስ ፣ ባስኬት ቦልና የእጅ ኳስ )
...
ግራር ጋርደን

- በተፈጥሮ ድንጋይ ፣ ፋውንቴንና አበባዎች ያሸበረቀ ለኢንተርቪውና ውይይት ፣ ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን ምቹ ቦታ
...
የተፈጥሮ ሀይቅ

- ስምንት ሺ ካሬ ስፋት
- ከጉለሌ እፅዋት ማዕከት ተራራ ምንጭን በማጎልበት የተሰራ የተፈጥሮ ሀይቅ
- ድልድይ ፤ አንድ መቶ ሃምሳ ሰው የሚይዝ አንፊ ትያትር ያለው
- ዙሪያው በእግር መንገድ የተከበበ
- አሳዎች እየረቡበት ያለ
...
የሰራተኞች ክበብ

- ለቀረፃና ለመዝናናት የሚሆን
- የእፅዋት ማዕከሉ ጫካ ጥሩ እይታ
- የጓሮውን ምርቶች የሚጠቀም
- ከተቋሙ በጡረታ የወጡ ባለሙያዎች የሚያስተዳድሩት

Via FM Addis 97.1

@etconp
1.9K viewsItoophiyaa‍ , 12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 12:31:02
TODAY TIP
.
  ላፕ ሌንግዝ (lap length) - ተፈላጊ የብረት (ፌሮ) ርዝመት ውጥረትን (stresses) ከአንድ ብረት ወደሌላ የሚተላለፍበት
.
.
ደቨሎፕመንት ሌንግዝ (Development length) -ተፈላጊ የብረት ርዝመት ውጥረትን (stresses) ከብረቱ ወደ ኮንክሪቱ የሚተላለፍበት
.
.
አንኮሬጅ ሌንግዝ (Anchorage length) - ይህ ርዝመት አይነት በቂ የሆነ ደቨሎፕመንት ሌንግዝ (development length ) በሌለባቸው በ Support / fixed ends ላይ provide የምናረገው ርዝመት ነው

Like | comment | Share

@etconp
2.0K viewsItoophiyaa‍ , 09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 09:39:02 የምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ G+7 ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ እያከናወናቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል የሚጠቀሰውና በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታ ስራው ተጓቶ የቆየው የምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ G+7 ህንፃ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ ይውል ዘንድ የቢሮው ማኔጅመንት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ችግሮቹ ተፈተው ወደስራ በመመለስ ከውሳኔው በኋላ በነበረው 1 ወር በተሰሩ ስራዎች ፍሬያማ ውጤቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

በምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በ567.2 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ ያረፈውና በቢ.ጂ.ኤም ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ኤ.ቲ.ኤም አርክትክቶችና ኢንጂነሮች አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘው ይህ ባለ 8 ወለል ሕንፃ ባለፈወ 1 ወር በተሰሩ ስራዎች የሴራሚክ ወለል ንጣፍ ስራ፣የመጨረሻ ወለል የስርገት መከላከያና የሴራሚክ ስራ፣የሳኒተሪ ስራዎች፣የሴፕቲክ ታንክ ስራዎች፣የአርምስትሮንግ ኮርኒስ ስራዎች  እና ሌሎችንም ስራዎች ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢ ኖሮት አምራችና ስኬታማ ትውልድ ማፍራት በሚያስችለው የጥራት ልክ እንዲጠናቀቅ የህንፃው ውጫዊ አካል እጅግ ውብ እና ማራኪ ገፅታን የመፍጠር ዓቅም ባለው   Calla Contextra   የቀለም ቅብ ስራ በ5 እጅ  እየተከናወነለት የሚገኝ ሲሆን የግራናይትና የአልሙኒየም ስራዎችም ደረጃቸውን ጠብቀው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

የሳይት ስራ፣የሊፍት ገጠማ ፣የውሀ ፓምፕ ገጠማ፣የበር ገጠማ፣የመስኮት መስታወት ገጠማ፣የህንፃው የውስጥ ቀለም ስራ፣የጀነሬተር እና የመሳሰሉት ዋና ዋና ስራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት በቀጣይ የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

በተቋሙ ከፍተኛ አመራር ያላሰለሰ ክትትል እየተደረገለት የሚገኘውና ሲጠናቀቅ በክህሎት፣በዕውቀት እንዲሁም በስነምግባር የላቀ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ማሕበራዊ ፋይዳ የሚኖረው ይህ ፕሮጀክት ከ1 ወር ባነሰ ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይውል ዘንድ በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ቢ.ጂ.ኤም ኮንስትራክሽን ተመሳሳይ ንድፍ ያለውን የተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አውቶሞቲቭ ዎርክሾፕ ከቢሮው ጋር በነበረው ውል መሰረት ባሳለፍነው በጀት ዓመት አጠናቆ ለአገልግሎት ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

@etconp
2.1K viewsItoophiyaa‍ , 06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 09:29:36
ታምራት ፦ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ ድርጅት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት ከ 1 ሚሜ - 40 ሚሜ በፈለጉት Size ቆርጠን በስተን

ጄ ቦልት ከ ባለ 12 - 32 ሚሜ በፈለጉት ቁመት ጥርስ አውጥተን አጥፈን እናስረክባለን።

ሌሎች ከ ብረታ ብረት ጋር የተያያዙ ስራዎች ማለትም ላሜራ፣ፊያቶ፣ ፌሮ፣ስታፋ፣ቱቦላሬ፣አንከርቦልት ወዘተ

በተጨማሪም ማናኛውንም ብረታብረት እንገዛለን እንሸጣለን።

ስልክ
0994941706
0911016833 ደውለው ያግኙን
ቴሌግራም ላይ ፦ https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦ ቁ.1 ጭድተራ ከፍብሎ
ቁ.2 አየር ጤና
1.9K viewsItoophiyaa‍ , 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 09:17:05 Urgent

Required professional labor
structure engineer =1
Geologist =1

Can contact us @etconpworks
or dial +251923763281

contracts work for contractor who is able to work
Asphalt maintenance =350m2

Can contact us @etconpworks
or dial +251923763281

@etconp
1.5K viewsDawit, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ