Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ

የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ማዘጋጃ ቤት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት አዲስ ባወጣው የከተሞች የተቀናጀ ፕላን፤ የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ በሦስት ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በአስር ወረዳዎች እንድትደራጅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድርግ በተሰራው ሥራ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 46 አዲስ ፕሮጀክቶች እና 26 ነባር በድምሩ 72 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ኀላፊ ገብሬ ዳቢ ተናግረዋል፡፡

እነዚህም የመንገድ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ ፣የጋር መኖሪያ ቤቶች፣ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የውሀ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙባቸው ተናግረዋል፡፡

አብዛኞቹ ሥራዎች በዚህ ዓመት ተጠናቀው አገልግሎት እንደሚጀምሩ የገለጹት ኀላፊው፤ ፕሮጀክቶቹ በመንግሥት በጀት፣ባለ ሀብቶች በሚያደርጉት ልገሳ እንዲሁም በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተሰሩ እንደሚገኙም በመጠቆም፤ ከተጠናቀቁ በሁዋላ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እና ማራኪ ማድረግ፣ ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የሕብረተሠብን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እንዲሁም የነዋሪውን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

ለፕሮጀክቶቹ ተሰጥቶ እየተሠራ ያለው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ወደፊት ከተማዋን በምሥራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp