Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኪነ-ህንፃ እድገት ግስጋሴ ወደኋላ ነዉ ሲሉ የአርክቴክትር ባለሙያዎች ተናገሩ የኢት | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የኢትዮጵያ ኪነ-ህንፃ እድገት ግስጋሴ ወደኋላ ነዉ ሲሉ የአርክቴክትር ባለሙያዎች ተናገሩ

የኢትዮጵያ ቀደምት ስነ-ህንጻዎች የሀገሪቱ የስልጣኔ ማሳያ ተደርገው ቢወሱም እርሱን ማስቀጠል አለመቻሉን ከአራዳ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡

አሁን ያሉ ግዙፍ ህንጻዎች በአይነታቸው ቢበዙም በታሪክ፣ ባህል እና ፍልስፍና ያላቸው ውክልና ግን አናሳ ነው፤ ይህም የኢትዮጵያ ኪነ-ህንፃ እድገት ግስጋሴ ወደኋላ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

ባለሙያዎቹ አክለውም ይህን ለማሻሻል ከተፈለገ የኪነ-ህንጻ ትምህርቱን ሙሉ በሙሉ ከዉጭ ባለመቅዳት ከእኛ አዉድ ጋር እንዲጣጣም ማሻሻል፣ ለማስተር ፕላን መገዛት፣ በአርክቴክት ዙሪያ የህብረተሰብ አስተሳሰብ ማስተካከል ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

@etconp