2023-05-10 17:30:35
በሶማሌ ክልል ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሊገነባ ነው
በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ጉራዳሞሌ ወረዳ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንደሚገነባ ተገለጸ።
ፕሮጀክቱ ከ49 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ኮንትራት ውል ዛሬ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው ናቸው።
ፕሮጀክቱ ለድርቅ ተጋላጭ በሆነ አካባቢ የሚገነባ በመሆኑ በተቀመጠው የግንባታ ጊዜ ወቅቱን ጠብቆ በጥራት እንዲከናወን ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በተገባው ውል መሰረት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የፕሮጀክቱ ወጪ የሚሸፈነው ከዓለም ባንክ የአንድ ቋት የመጠጥ ውሃ፣ሳኒቴሽንና የሃይጂን (One WaSH) ፕሮግራም ብድር እንደሆነ ተጠቁሟል።
የባለብዙ መንደር የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ይችላል የተባለው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ከ49ሺ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
የውል ስምምነቱ አጠቃላይ የሲቪል ግንባታና አሌክትሮሜካኒካል ስራዎችን እንዲሁም የመስመር ዝርጋታን እንደሚያካትት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@etconp
2.4K viewsItoophiyaa , 14:30