Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
የሰርጥ አድራሻ: @etconp
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.50K
የሰርጥ መግለጫ

🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
📨ሃሳብ እና ኣስተያየት @Philemona7 ፃፉልን
📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp
📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ:- @ETCONpDigitalLibrary_Bot

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-12 17:30:44 ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት!

የቺካጎ የግንባታ ኤክስፖ (CHICAGO Build Expo) እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 11 – 12 ቀን 2023 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በሀገረ አሜሪካ በቺካጎ ከተማ ይካሄዳል፡፡ ማኅበራችንም በዚህ ኤክስፖ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ አባላቱን ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉበትን የሥራ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

በዚሁ መሠረት በዚህ ግዙፍ በሆነ የግንባታ ኤክስፖ ላይ ተሳታፊ ለመሆን የምትፈልጉ የማኅበራችን አባላት ከግንቦት 4 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ብቻ እንድትመዘገቡ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡

1) ከኤክስፖው አዘጋጆች በተጣለብን ግዴታ መሠረት መመዝገብ የምትችሉት አባሎቻችን ከደረጃ 1 – 4 የምትገኙ ብቻ ናችሁ፤

2) አመልካቾች ባለትዳር የሆኑና ለዚህም ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

3) አመልካቾች በባለቤትነት በሚያስተዳድሯቸው ድርጅቶቻቸው ውስጥ 5 ያህል ቋሚ ሠራተኞች ቀጥረው የሚያሰሩ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

4) ዓለም አቀፍ የሆኑ የጉዞ ታሪክ ያላቸው አመልካቾች የተሻለ ዕድል እንዳላቸው ይታመናል፤

5) በቪዛ ማመልከቻ ወቅት መቅረብ የሚገባቸውና እንደ ሂሳብ መግለጫ ሰነዶች፣ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነዶች እና የመሣሠሉት አስፈላጊ ጉዳዮች እነድታቀርቡ ስትጠየቁ ብቻ የምታቀርቧቸው ይሆናሉ፤

6) ማኅበራችን ይህንን ሥራ ኤምባሲው ዕውቅና ሰጥቶት በዚህ ሥራ ላይ የተሠማራ ወኪል መጠቀም የግድ ስለሚሆንበት ይኽው ሙያተኛ የሚጠይቀውን ክፍያ፣ የቪዛ ቀጠሮ ለማመቻቸት የሚረዳውን የኤግዝቢሽኑን መግቢያ ክፍያ በአሜሪካን ዶላር ለመፈፀም እና ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለማከናወን የሚረዳና ተመላሽ የማይደረግ ብር 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) ከዚህ በታች በሚገኙት የማኅበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ገቢ በማድረግ ማረጋገጫ ማቅረብ ከአመልካቾች ይጠበቃል

6.1) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዑራኤል ቅርንጫፍ፣ ሂሳብ ቁጥር 1000336931197

6.2) ንብ ባንክ፣ ዑራኤል ቅርንጫፍ፣ ሂሳብ ቁጥር 7000001116358

7) ለአሜሪካ ኤምባሲ የሚከፈለው የኮቴ እና የቪዛ ከፍያ በእራሱ በአመልካቹ የሚፈፀም ሲሆን፤ የመክፈያ ጊዜው ሲደርስ ማኅበራችን ለአመልካቾች ያሳውቃል፤

8) የምዝገባ ቅፁን ለመሙላት በዚሁ ሥራ ላይ ለተሠማሩ ሰዎች የሚከፈለውን ክፍያእራሱ አመልካቹ የሚከፍለው ይሆናል፤

9) የአሜሪካን ሀገር ቪዛ ተሳክቶላቸው ያገኙ አመልካቾች ኤክስፖውን መጎብኘታቸው በኤምባሲው በኩል እንዲታወቅ ስለሚያስፈልግ አመልካቾች ይህንኑ አስቀድማችሁ የምታሳውቁን እንዲሆን እየጠየቅን ለዚህም የቡድን የጉዞ ቲኬት እና በኤክስፖው ከተማ የቡድን ማረፊያ ለማመቻቸት እንደሚያግዘን አስቀድመን ለማሳወቅ እንወዳለን፤

10) ምዝገባውን በማኅበራችን ፅ/ቤት ለማከናወንም የታደሰ ፓስፖርት፣ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ አስፈላጊ ነው፤

11) በማኅበራችን በኩል ለቪዛ ቃለ-ምልልስ የሚያግዝ መረጃ፣ ለዚሁ ቃለ-ምልልስ የሚያግዝ የቪዲዮ መግለጫ፣ ከቃለ-ምልልሱ በፊት ለሚያስፈልግ የልምድ ማካፈል አገልግሎቶችን ማኅበራችን ይሠጣል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

@etconp
2.0K viewsItoophiyaa‍ , 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 15:43:36 የመካነ-እየሱስ/እስቴ - ስማዳ 50.5 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በፍፃሜ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

አሁን ላይ ከአጠቃላይ የግንባታ ሥራው 86 በመቶው ተከናውኗል። ቀሪ ሥራዎቹን በሚቀጥሉት አምስት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው።

ከጠቅላላው የመንገዱ ክፍል 47 ኪሎ ሜትሩን አስፋልት ማልበስ ተችሏል። በተጨማሪም የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ፣ የሾልደር፣ የውኃ መፋሰሻ፣ የድልድይ እንዲሁም የማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡

ግንባታውን ዓለም አቀፉ 'ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ' እያከናወነ ይገኛል።

ለግንባታው የሚውለው 1,925,451, 264.41 (አንድ ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ) ብር በፌደራል መንግስት ነው የሚሸፈነው። 'ፕሮሚናንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ' ግንባታውን የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ እየሠራ ይገኛል።

አካባቢው ካለው በርካታ አገራዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡

በፕሮጀክቱ የከተማ ክልል ላይ ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ችግር በግንባታ ሥራው ላይ እክል ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም፥ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከወረዳ የመስተዳድር አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሩን መፍታት ተችሏል፡፡

ከዚህም ባለፈ የአካባቢው አስቸጋሪ የመልካ-ምድራዊ አቀማመጥ እንዲሁም የግንባታ ዕቃዎች የግብዓት ዕጥረት እና የዋጋ መናር በግንባታው ወቅት የገጠሙ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡

የእስቴ-ስማዳ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ 657 ኪ.ሜ ርቀት እስቴ ከተማ ላይ ጀምሮ ወገዳ ከተማ ድረስ ይዘልቃል፡፡

ፕሮጀክቱ ዕውን ሲሆን በሥፍራው የሚገኙትን ትንንሽ መንደሮች ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በማገናኘት ወደ ከተማ የሚያድጉበትን ምቹ ዕድል ይፈጥራል፡፡የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን በማሳለጥም የተለያዩ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን ያጠናክራል፡፡

በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ሽንብራ፣ ኑግ፣ ባቄላ፣ ጓያ፣ ድንች እና መሰል የግብርና ምርቶች ገበያ በፍጥነት እና በጥራት ማድረስ ያስችላል፡፡

Via ERA

@etconp
1.9K viewsItoophiyaa‍ , edited  12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 15:43:08
1.7K viewsItoophiyaa‍ , 12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 14:30:52
የስብሰባ ጥሪ ለአክሱም ዩኒቨርስቲ የ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮችና አማካሪዋች በሙሉ!

ተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ይጠይቁ።

+251901297308
+251901297308
+251914744015
+251914292159

@etconp
1.8K viewsItoophiyaa‍ , edited  11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 12:32:01
Reinforcement steps of concrete columns by injection concrete jacket method in order to increase the bearing capacity

@etconp
1.9K viewsItoophiyaa‍ , 09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:20:07
የንድፍ ውድድር አንደኛ አሸናፊ
ኤም ኤ ኢ አማካሪ ብርሀን ባንክ ያሰናዳውን የንድፍ ውድድር አንደኛ ወጥቶ አሸንፏል፡፡

አማካሪ ድርጅቱ በ2015 እኤአ በመስራቹና በዋና ስራ አሰኪያጁ በህንጻ ነዳፊው በምስክር አግዘው የተመሰረተ ነው፡፡

የውድድር ህንጻው የሚቆምበት መሬት ስፋት 5400 ካሬ ሜትር ሲሆን የውድድር ዳኞቹም

1 አቶ አለበል ደስታ (ህንጻ ነዳፊ)
2 አቶ ጌታቸው ማንደፍሮ (ህንጻ ነዳፊ)
3 አቶ ኪሩብ ገብረየሱስ (ህንጻ ነዳፊ) እንዲሁም
4 አቶ ኬንሞስ ተስፋዬ (የመዋቅር መሀንዲስ) ነበሩ፡፡

በአጠቃላይ 16 ንድፎች ለውድድር መቅረባቸው ታውቋል፡፡

ምስል ምንጭ ብርሀን ባንክ እና በይነ መረብ

@etconp
2.1K viewsItoophiyaa‍ , 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:18:02
የንድፍ ውድድር አሸናፊ

ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንፃ ግንባታ ዲዛይን ለማሠራት ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመሰጠውን ዲዛይን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ላይ 16 ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ካቀረቧቸው ዲዛይኖች መካከል አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሠረት ባንኩ በሰንጋ ተራ አካባቢ በተረከበው 5400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ህንፃ MAE ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ በተባለው ድርጅት የቀረበው ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል።

በተመረጠው ዲዛይን መሠረት የሚገነባው የባንኩ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ከ 51 በላይ ወለሎች እንደሚኖሩት ታውቋል።

በዴጃው ኮንሰልቲንግ የተሰራው የህንፃ ዲዛይን ሁለተኛ ደረጃ አሸናፊ ሲሆን ፣ በአዲስ መብራቱ ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ የቀረበው ዲዛይን ደግሞ ሦስተኛ ወጥቷል።

Via Ethiopian Reporter

@etconp
1.3K viewsItoophiyaa‍ , 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 18:01:59
የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃ እና የሲኒማ ኮምፕሌክስ 4B+G+8 ግንባታዎችን ቀሪ ስራዎች ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

ቀድሞ ግንባታውን ያከናውን የነበረው ስራ ተቋራጭ እቴቴ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶቹ በተለያየ አፈፃፀም ደረጃ ላይ እያሉ አቋርጦ በመውጣቱ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መነሻ ሆነው የቆዩት የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ግንባታዎች አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡

ጉዳያቸው በፍርድቤት በመያዙ እንዲሁም በጨረታ ሂደቶች ምክንያት ለ16 ወራት ገደማ ተቋርጠው የቆዩት እነዚህ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጨረታውን ካሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ጋር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ውለታ የማሰር ስነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃን ከ833 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ቀሪ ስራዎች ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የፕሮጀክት ውል መጠን ጨረታውን ያሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ስራዎቹን አጠናቆ ለማስረከብ የ6 ወራት ዕድሜ የተሰጠው ሲሆን ከፕሮጀክቱ አንገብጋቢነት አንፃር የሚሰጠው ቅድመ ክፍያ በጥምር ሂሳብ / Joint Account / የሚተዳደር ሆኖ ለግብዓት ግዢ ብቻ የሚውል መሆኑን ከስራ ተቋራጭ ጋር መግባባት ላይ እንደተደረሰና ይህም ወደፊት ሊከሰት ከሚችል የግብዓት ዋጋ ንረት እንደሚታደግ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል::

@etconp
400 viewsItoophiyaa‍ , 15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:30:23 የጠቅላይ ሚንስትሩ የቤተመንግሥት ፕሮጀክት ለሦስት ተቋራጮች ተሰጠ

የ”ጫካ” ፕሮጀክት የሚል ስያሜ ላለው እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርበት ለሚከታተሉት የአዲስ ቤተ መንግስት ግንባታ ተጨማሪ ሶስት ተቋራጮች መቀጠራቸው ተሰምቷል። ከቤተ መንግስት በተጨማሪ ፣ የቅንጡ መኖርያ እና መዝናኛ መንደርን የሚያካትተው ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ፣ የካ ተራራን ታኮ የሚሰራው ፕሮጀክት እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግዙፍነቱ የሚመዘገብ መሆኑ ሲነገርለት የቆየ ነው።

503 ሄክታር መሬት ላይ በሚያርፈው በዚህ ፕሮክጀክት እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የ29 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ እየተሰራ ሲሆን አብዛኛው የመንገድ ስራ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል።

የ”ጫካ” የሚል ስያሜ ባለው ፕሮጀክት ውስጥ ሶስት ሰው ሰራሽ ሀይቆች የሚኖሩ ሲሆን ፣ እነዚህ ሰው ሰራሽ ሀይቆች ኢ ቶሎ በተባለ ተቋራጭ እየተሰሩ መሆናቸውን መረዳት ችለናል። ከሶስቱ ሀይቆች ውስጥም የአንዱ ሀይቅ የመሰረት ስራ መጠናቀቁን ከምንጮቻችን አረጋግጠናል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ደግሞ በዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሳተፉ ተጨማሪ ሶስት ተቋራጮች መቀጠራቸውን ዋዜማ ሰምታለች።

መንግስታዊው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮስኮ) የዋናውን ቤተ መንግስት ግንባታ እንዲያከናውን ውል ተሰጥቶታል። የቻይናው መንግስታዊ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲሲሲ ደግሞ በፕሮጀክቱ የሚካተተውን የቅንጡ ሆቴል ግንባታን ያከናውናል። ሆቴሉም “ስካይ ቪው” የሚል ስያሜ እንደሚኖረው ተነግሯል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ደግሞ ከቤተ መንግስቱ እስከ የካ አባዶ የሚገነባውን መንገድ በተቋራጭነት ይሰራል። ይህ ግዙፍ ግንባታ በቀጣይ ተጨማሪ ተቋራጮች ይሳተፉበት እንደሁ ማረጋገጥ አልቻልንም።

የ”ጫካ” ፕሮጀክት ወጪ በትክክል ባይታወቅም ፣ 49 ቢሊየን ብር እንደሚያወጣ በስፋት ሲነገር ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከወራት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ፕሮጀክቱ እንደሚባለው የ49 ቢሊየን ብር ብቻ ሳይሆን ከ300 እስከ 400 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የ”ስማርት ሲቲ” ልማት አንዱ አካል ነው ሲሉ ማብራሪያ መስጠ ታቸው ይታወሳል።

የምዕራቡ ዓለም የዲፕሎማቲክ ምንጮች በበኩላቸው የጫካ ፕሮጀክት አሁን ባለው የምንዛሪ ተመን ከ850 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑን እየተናገሩ ነው።

የገንዘቡን ምንጭ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍንጭ አልሰጡም ። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርብ ክትትል የሚሰራው ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር የቅደም ተከተል ጥያቄ በተደጋጋሚ ሲነሳበት ቆይቷል።

ለግንባታው በአቅራቢያው የነበሩ ነዋሪዎች እንዲነሱ የተደረጉ ሲሆን ፣ በስፍራው መንግስት የሚያስቀምጠውን የቅንጡ መኖርያዎች ዲዛይንን አሟልተው ግንባታ ማከናወን የሚችሉ ግለሰቦች ብቻ መኖርያ ቤት መስራት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የጫካው ፕሮጀከት ከዚህም ሲያልፍ በሚሰራበት የየካ ተራራ አካባቢ በአቅራቢያ ካለችው እንቁ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ጋር የወሰን ይገባኛል ጥያቄ ክርክር ውስጥ ገብቶ ፍርድ ቤት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ፈርዷል።

Via ዋዜማ ሬዲዮ

@etconp
1.0K viewsItoophiyaa‍ , 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:30:48 Design Of Concrete

This PDF includs

Design of Concrete Structures and Fundamental Assumptions
Flexural Analysis and Design of Beams
Shear and Diagonal Tension in Beams
Short and Slender Columns
Analysis, Idealization, and Preliminarily Design of Reinforced Concrete Beams and Frames
Analysis and Design of One-Way and two-way Slabs
Footings and Foundations
Retaining Walls and Strut-and-Tie Method
Design of Reinforcement at Joints
Concrete Building Systems
Seismic Design

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

@etconp
1.5K viewsItoophiyaa‍ , 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ