Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
የሰርጥ አድራሻ: @etconp
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.50K
የሰርጥ መግለጫ

🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
📨ሃሳብ እና ኣስተያየት @Philemona7 ፃፉልን
📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp
📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ:- @ETCONpDigitalLibrary_Bot

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-02 19:16:26 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በተሻለ ሁኔታ ለመምራት በሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ የጋራ ውይይት ተደረገ

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር፣ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አዋጅ እና በኮንስትራክሽን ግዥና ውል አስተዳደር ረቂቅ መመሪያ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የጋራ ውይይት በአዳማ ከተማ አካሄደ፡፡ 

በውይይት መድረኩ ላይም  የሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል አመራሮች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ የሙያ ማህበራትና ሌሎች የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መድረኩን በክብር እንግድነት ተገኝተው በንግግር የከፈቱት ክቡር ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር፣ የመሠረተ-ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የመድረኩን መዘጋጀት አስፈላጊነት ሲገልጹ እንደተናገሩት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ወጥነት ባለው መንገድ ለመምራት ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ በዋናነት በህግ ማዕቀፎች ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻል የመጀመሪያው ስራ እንደሆነ በማመን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አዋጅን በረቂቅ ደረጃ ለማዘጋጀት ተችሏል ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በማያያዝ የኮንስትራክሽን ግዥና ውል አስተዳደር መመሪያን በተመለከተም አስካሁን ባለው ሂደት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ወጥነት ባለው መንገድ የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ ስላልነበረው በሀገር አቀፍ ደረጃ ኢንዱስትሪው የሚመራበት ስርዓት አልተዘረጋም ነበር፡፡

ስለሆነም ወጥና ምቹ የሆነ ሜዳ  በመፍጠር ሁሉንም ተዋንያን በእኩል ደረጃ የሚያስተናግድ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ የግዥና ውል አስተዳደር ረቂቅ መመሪያን ማዘጋጀት ተችሏል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ለውይይት የቀረቡት ሠነዶች በረቂቅ ደረጃ ላይ የቀረቡ በመሆናቸው ግብኣት ለመሰብሰብና የመጨረሻ ቅርጽ ለማስያዝ ለውይይት የቀረቡ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ከተሳታፊዎች የነቃ ተሳትፎ የሚጠበቅ እንደሆነና በአፈጻጸም ሂደት ቅሬታ በማያስነሳ ሁኔታ ሠነዱን ማዳበር እንደሚያስፈልግ በመግለጽ መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የእርሳቸውን የመክፈቻ ንግግር ተከትሎ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ረቂቅ አዋጅ የውይይት መነሻ ሠነድ ያቀረቡት የኮንስትራክሽንና መሠረተ-ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ መዲና አህመድ በገለጻቸው እንደተናገሩት የኮንስትራክሽን ዘርፉ ሚና ትልቅ መሆኑንና በመንግስት ከፍተኛ በጀት የሚመደብለት፣ የግሉ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስበት ዘርፍ በመሆኑ አዋጁ እናት ህግ ሆኖ እንዲያገለግል ከሁሉም የዘርፉ ተዋንያን ብዙ እንደሚጠበቅ በመግለጽ የተዘጋጀውን 9 ክፍሎች እና 86 አንቀጾች ያሉትን የረቂቅ አዋጅ ሠነድ አቅርበዋል፡፡
ከእርሳቸው በመቀጠል የኮንስትራክሽን ግዥና ውል አስተዳደር ረቂቅ መመሪያን በተመለከተ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የዲዛይን ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍሬው በቀለ አቅርበዋል፡፡

አቶ ፍሬው መመሪያውን በተመለከተ ሲገልጹ እንደተናገሩት በ13 ክፍሎች ተከፍሎ የቀረበው መመሪያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተላከውን የተሻሻለውን የግዥ አዋጅ፣ እንዲሁም በገንዘብ ሚኒስቴርና በግዥ ኤጄንሲ የወጡ የህግ ማዕቀፎችን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት መነሻ የውይይት ሠነዶች ላይ በመመስረት በርካታ በግብአትነት የሚያገለግሉ ሀሳብና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ቀርበው በዘርፉ ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎችና መነሻ የውይይት ሠነዱን ባቀረቡት አካላት ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶ መድረኩን በመሩት በዕለቱ የክብር እንግዳ በተሰጠ የማጠቃለያ አስተያየትና ቀጣይ አቅጣጫ መድረኩ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

Via ስለሺ ዘገዬ

@etconp
2.4K viewsItoophiyaa‍ , edited  16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 13:43:01 እስቲ ዛሬ ከ ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮች ጋ የተያያዘ እንዳስስ

​​ ብዙ ጊዜ ሶፍትዌር ስንገዛ crack የተደረጉ ናቸው። ይሄም የሆነው አንድም original የመግዛት አቅም ስለሌለን ሁለትም online ግብይት በኛ ሀገር ስላልተጀመረ ነው።

⇶crack
crack የተደረገ ማለት የ የሶፍትዌር አምራቾች የሚያወጡትን original ሶፍትዌሮች ሀከሮች ሀክ በማድረግ ያለ ክፍያ መጠቀም ማስቻላቸው ነው።

አንዳዴም ሀከሮች ለመልካም ነገር ይጠቅሙናል የሚባለው ለዚህ ነው። እነዚህን ሶፍትዌሮች ለመጫን ግን ብዙ ጊዜ ስንቸገር እንታያለን።

ለዛሬም የተወሰኑ ነገሮችን ለማየት እንሞክራለን።
በመጀመሪያ ደረጃ ከ crack በተጨማሪም keygen እና patch የተሰኙ መንገዶች መተዋል። ከዚህ ሌላም ሊኖሩ ይችላሉ።
 
       ◉ step one_1↹

⇶Internet
⇒በመጀመሪያ ደረጃ internet ማጥፋታችንን ማረጋገጥ አለብን። ብዙ ጊዜ የሶፍትዌር ካምፓኒዎች originalityውን validate የሚያደርጉት በዚህ ስለሆነ ነው። ቀጥሎ አንቲ ቫይረስ ካለን disable ማድረግ አለብን አለበለዚያ crack ፋይላችንን ሊበላው ይችላል።

      ◉ step Two_2↹

⇶Run
⇒ሶፍትዌራችንን run አርገነው ከጫንን በኋላ launch/ መክፈት/ የለብንም መመሪያውም ላይም  tick ተደርጎ ከሆነ untick ማድረግ ይገባናል።


      ◉ step three_3↹

⇶Crack file
⇒በ crack መልክ የመጣ ሶፍትዌር ከሆነ crack ፋይል ውስጥ ያሉትን ፋይሎች copy አድርገን ሶፍትዌራችንን የጫንበትን location ከፍተን paste ማድረግ በዚ ሰአት ተመሳሳይ ነው overwrite ላርገው የሚል ምርጫ ሲመጣልን የስ/yes/ እንለዋለን።(ብዙ ጊዜ ሎኬሽኑ የሚገኘው local C/program file 86/ ውስጥ ነው አልያም የጫነው ሶፍትዌር icon ላይ right click በማድረግ open location የሚለውን መምረጥ።)

      ◉ step four_4↹

⇶Keygen
⇒ሶፍትዌራችን በዚህ መልክ ከሆነ ደሞ ሶፍትዌራችንን patch ማድረግ አለብን። patcher በመጠቀም ያገኘነውን key ሶፍትዌሩ ላይ መሙላት ። አንዳንዴ ደሞ በ ጽሁፍ መልክ ይመጣል በዚህ ሰአት ከፍተነው የምናገኘውን key copy አድርገነው ከዛ ሶፍትዌሩን run ስናደርገው የሚጠይቀን ቦታ ላይ እናስገባዋለን።

↹ ለምሳሌ office 2007 እና window xp በዚህ መልክ ነው የሚጫነው።
ነገር ግን keygen ከመጠቀማችን በፊት patching የሚያስፈልገው ከሆነ ቀጥሎ ያለውን step ይጠቀሙ።

      ◉ step five_5↹

⇶Patch
⇒በዚህ መልክ ሲመጣ ደሞ patch ፋይሉን Run as Administration በሚለው እንከፍተዋለን right click አድርገን።
በዚህ ሰአት በ administrator account መግባታችንን ልብ ልንል ይገባል።

በላይ በገለጽናቸው መንገዶች ተጠቅመን activate ካደረግን በኋላ መስራቱን ቼክ አድርገን internet ከመክፈታችን በፊት firewall ውስጥ ገብተን የጫነው ሶፍትዌር access እንዳያደርግ block ብናደርግ ይመረጣል አለበለዚያ የተጭበረበረ መሆኑን ካወቀ መልሶ deactivate ሊያደርግብን ስለሚችል።

N.B ! ሶፍትዌር የያዘውን ፍላሽ ከመሰካታችን በፊት anti virus ሳችንን disable ማድረግ አለብን በተለይም እንደ smadav auto run የሆኑትን።

◉ ከዚህ ሌላ መንገዶች ሊኖሩ ይችላል ምክንያቱም በየቀኑ ሴኪሪያቲያቸውን እያጠናከሩ ስለሚመጡ በዛው መጠን crack ለማድረግ ፈታኝ እና ኮምሌክስ እየሆኑ ነው የሚመጡት ለዚህ ARCI GIS ጥሩ ማሳያ ነው።

Via Yirhe

@etconp
2.4K viewsItoophiyaa‍ , 10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 10:42:01 ትብብርን ሰለመጠየቅ

ለ BSc ፕሮግራም ጥናታዊ ጽሁፍ የሚሆን መጠይቅ እንድትሞሉልኝ ስል በትህትና እጠይቃለው።

Hello there, i'm a student at AAU, EiABC and i am conducting a Bsc thesis research, i'm here to ask you a favor to post a link of google form to ETCONp Members 

Here is the link
https://forms.gle/HF8DvFWuHTzDLVgg6

Thanks in advance
2.3K viewsItoophiyaa‍ , 07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 08:01:25
ታሪክን የኋሊት

ከጣልያን በፊት የተሰራ የአዲስ አበባ ካርታ፡፡

እኤአ 1909 ማለትም ከጣልያን መግባት 27 አመት ገደማ በፊት በፈረንሳይኛ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ ካርታ ምስል ተያይዟል፡፡

በስተሰሜን በኩል የስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ የራስ ተፈሪ የነበረ መሆኑንና ሱ በስተምስራቅ ተቃራኒ ደግሞ የልጅ እያሱ ግቢ መሆኑን ያመላክተናል፡፡ የቀድሞው የልጅ እያሱ ግቢ የአሁኑ የጀርመን ባህል ማእከል ወይም ጎተ ኢንስቲትዩት መሆኑን እንረዳለን፡፡ የፒያሳው የአድዋ ጎዳና የራስ መኮንን መንገድ እንደሚባል፣ በደቡብ ያለው የባቡር ጣብያ የሚወስደው መንገድ ሩ ዴ ላጋር ወይንም የባቡር ጣብያ መንገድ እንደሚባልም እንመለከታለን፡፡ በካርታው በስተምስራቅ ደግሞ ዳግማዊ ምኒልክ በወንዞች ላይ ድልድይ እንዲሰሩ አስበው እና ከከተማ ውጭ መሆናቸውን ገምተው ለጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ሩስያ እንዲሁም እንግሊዝ ለኤምባሲዎች ሰፋፊ ቦታ መስጠታቸውን እንረዳለን፡፡
በደቡብ ምስራቅ የኡራኤል ቤተክርስትያን ፈንጠር ብሎ መገንባቱም ይታያል፡፡

በተከታታይ ከጣልያን በፊት፣ በጣልያን ግዜ፣ በ1960ዎቹ እንዲሁም ከዛን ወዲህ በደርግ ግዜ የተሰሩትን የአዲስ አበባ ካርታዎች በዚህ የቴሌግራም ጣብያ ማያያዛችን ይታወሳል፡፡

@etconp
2.2K viewsItoophiyaa‍ , 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 07:30:28
#ADVERTISEMENT

ታምራት ፦ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ ድርጅት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት ከ 1 ሚሜ - 40 ሚሜ በፈለጉት Size ቆርጠን በስተን

ጄ ቦልት ከ ባለ 12 - 32 ሚሜ በፈለጉት ቁመት ጥርስ አውጥተን አጥፈን እናስረክባለን።

ሌሎች ከ ብረታ ብረት ጋር የተያያዙ ስራዎች ማለትም ላሜራ፣ፊያቶ፣ ፌሮ፣ስታፋ፣ቱቦላሬ፣አንከርቦልት ወዘተ

በተጨማሪም ማናኛውንም ብረታብረት እንገዛለን እንሸጣለን።

ስልክ:- 0994941706
ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
ቴሌግራም ላይ ፦ https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦ ቁ.1 ጭድተራ ከፍብሎ
               ቁ.2 አየር ጤና ያግኙን
2.2K viewsItoophiyaa‍ , 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 19:31:04
ዛሬ የተመረቀው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የገበታ ለሀገር

ሐላላ ኬላ ሪዞርት ይህንን ይመስላል

በ ምስል ይመልከቱት

ውብ ምሽት ተመኘን

@etconp
2.5K viewsItoophiyaa‍ , 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 15:50:34 በመጀመሪያ ለምታደርጉልን ትብብር እያመሰገንን ለ msc ፕሮግራም ጥናታዊ ጽሁፍ የሚሆን መጠይቅ እንድትሞሉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ።

  ADDIS ABABA SCIENCE AND TECHNOLOGY UNIVERSITY
COLLEGE OF ARCHITECTURE AND CIVIL ENGINEERING DEPARTMENT OF CIVIL ENGINEERING; CONSTRUCTION TECHNOLOGY AND MANAGEMENT

Questionnaire Survey for MSc Thesis on the title of; Assessment of challenges on sustainable construction practices in building construction projects in Addis Ababa.

https://docs.google.com/forms/d/1wpBgBvIx5Nze2gRqN-a1uiiSTFbGuqq_t25gRWv6gUk/edit
2.6K viewsDawit, 12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:20:11 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ።

በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር በጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ዳርቻ የሚገኘው የሀላላ ካብ በ'ገበታ ለሀገር' ኮይሻ ኮሪደር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሃላላ ኬላ ሪዞርት ውስጥ ተካቶ የለማ ድንቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀላላ ኬላ ሪዞርት ከመዝናኛ ስፍራነቱ በተጨማሪ ታሪካዊና ባህላዊ ሙዚየሞችና የምርምር ማዕከላትን ያካተተ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የዳውሮ ዞን ለአይን የሚማርኩ መልከዓ ምድር፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ባለቤት ስለመሆኑም አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያን ለብዙ ስራዎች አእምሯችሁ እንዲከፈት የህዝብና አካባቢ ሰላም በእጅጉ በሚገኝበት የዳውሮ ዞን በመምጣት አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍለቅና ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት እንዲጎበኙም ጥሪ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሸትን በማለባበስ እውነት ማድረግ እንደማይቻልና ውሸትን ቀባብቶ እውነት ለማስመሰል መሞከር እንደ ሐላላ ኬላ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለመፍጠር አያስችልም ሲሉም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊት የብዙ ባህልና ቋንቋዎች መገኛ ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ብዘኃነት እንደራስ መቀበልን መለማመድ ያስፈልጋል ብለዋል።

እንደ ዋልታ ዘገባ፤ ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ሀገር ናት የምንለው በባህልና ቋንቋ ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮም እጅግ ማራኪ ሕብረ ብሔራዊ ቀለማትን በውስጧ የያዘች ሀገር መሆኗን መረዳት ያስፈልጋል፤ በዚህም አንዱ አካባቢ ከሌላው የተለየ የራሱ ተፈጥሯዊ ገፀ በረከቶችን የያዘ በመሆኑ በአግባቡ በማልማት መጠቀም እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በመጨረሻም የዳውሮ ማህበረሰብ የሐላላ ኬላ ሪዞርት እንደቀደሙ አባቶች ቅርስ በመጠበቅ ለትውልድ እንዲያሸጋግርና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል።

@etconp
2.6K viewsItoophiyaa‍ , 11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 13:14:45
Happy International May day

@etconp
2.1K viewsItoophiyaa‍ , 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 12:28:29 USES OF CEMENT @COTMp
.
Cement is used widely for the construction of various structures. Some of them are listed below:
Cement slurry is used for filling cracks in concrete structures.
Cement mortar is used for masonry work, plastering and pointing.
Cement concrete is used for the construction of various structures like buildings, bridges, water tanks, tunnels, docks, harhours etc.
Cement is used to manufacture lamp posts, telephone posts, railway sleepers, piles etc.
For manufacturing cement pipes, garden seats, dust bins, flower pots etc. cement is commonly used.
It is useful for the construction of roads, footpaths, courts for various sports etc.

@etconp
2.1K viewsItoophiyaa‍ , 09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ