Get Mystery Box with random crypto!

ታሪክን የኋሊት ከጣልያን በፊት የተሰራ የአዲስ አበባ ካርታ፡፡ እኤአ 1909 ማለትም ከጣልያ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

ታሪክን የኋሊት

ከጣልያን በፊት የተሰራ የአዲስ አበባ ካርታ፡፡

እኤአ 1909 ማለትም ከጣልያን መግባት 27 አመት ገደማ በፊት በፈረንሳይኛ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ ካርታ ምስል ተያይዟል፡፡

በስተሰሜን በኩል የስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ የራስ ተፈሪ የነበረ መሆኑንና ሱ በስተምስራቅ ተቃራኒ ደግሞ የልጅ እያሱ ግቢ መሆኑን ያመላክተናል፡፡ የቀድሞው የልጅ እያሱ ግቢ የአሁኑ የጀርመን ባህል ማእከል ወይም ጎተ ኢንስቲትዩት መሆኑን እንረዳለን፡፡ የፒያሳው የአድዋ ጎዳና የራስ መኮንን መንገድ እንደሚባል፣ በደቡብ ያለው የባቡር ጣብያ የሚወስደው መንገድ ሩ ዴ ላጋር ወይንም የባቡር ጣብያ መንገድ እንደሚባልም እንመለከታለን፡፡ በካርታው በስተምስራቅ ደግሞ ዳግማዊ ምኒልክ በወንዞች ላይ ድልድይ እንዲሰሩ አስበው እና ከከተማ ውጭ መሆናቸውን ገምተው ለጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ሩስያ እንዲሁም እንግሊዝ ለኤምባሲዎች ሰፋፊ ቦታ መስጠታቸውን እንረዳለን፡፡
በደቡብ ምስራቅ የኡራኤል ቤተክርስትያን ፈንጠር ብሎ መገንባቱም ይታያል፡፡

በተከታታይ ከጣልያን በፊት፣ በጣልያን ግዜ፣ በ1960ዎቹ እንዲሁም ከዛን ወዲህ በደርግ ግዜ የተሰሩትን የአዲስ አበባ ካርታዎች በዚህ የቴሌግራም ጣብያ ማያያዛችን ይታወሳል፡፡

@etconp