Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etconp — Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
የሰርጥ አድራሻ: @etconp
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.50K
የሰርጥ መግለጫ

🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
📨ሃሳብ እና ኣስተያየት @Philemona7 ፃፉልን
📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp
📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ:- @ETCONpDigitalLibrary_Bot

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-17 07:31:02 ገፅ 3

የአርክቴክት ኃይሌ ሚና ምን ነበር?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ ከዓመታት በፊት በመሠረተው ድርጅቱ አማካይነት በዚህ ፕሮጀክት እና በሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ከተሳተፉት አካላት መካከል ነው።

‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ የተባለው የእርሱ ድርጅት እና ሌላ ‘ስታዲያ ኢንጂነሪኒግ’ የተባለው ድርጅት በጥምረት የእነዚህን ፕሮጀክቶች ዲዛይን በመሥራት እንዲሁም ቁጥጥር በማድረግ ተሳትፈዋል።

“እነዚህን በክላስተር የተከፈሉትን ዲዛይኖች ‘ኮንሰፕት ዲዛይን’ ከማዘጋጀት ባለፈ የዲዛይን ቁጥጥር እና ክትትል እንድንሰራ ነው ኮንትራት የገባነው” ይላል።

እንደ ግሉ ደግሞ ኃይሌ የአርክቴክቸራል ቡድን መሪ በመሆን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳትፎ ማድረጉን ይናገራል።
“እድሜዬ 31 ነው፤ ዛሬ ደረስኩባቸው ብዬ የማስባቸው ነገሮች፣ ፍላጎቴን እና ጥረቴን አንድ ላይ አጣምሬ ሳያቸው ትንሽ የዘገየሁ ይመስለኛል” በማለት በራስ መተማመን በዚህ ፕሮጀክት ላይ መሳተፉን ይናገራል።

“ትልቁ ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው” የሚለው ይህ ወጣት፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ለአርክቴክቸር ትምህርት፣ ፍቅር እና ልዩ የሆነ ፍላጎት ማሳደሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ለመብቃት ረድቶታል።

አርክቴክት ኃይሌ በትምህርት እና በሥራው ላይ ከመበርታቱ ባሻገር በዚህ ዘርፍ በተቻለው መጠን ሌሎች ቦታዎች ያሉ ተሞክሮዎችን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል።

“ይህንን ፕሮጀክት ከማግኘቴ በፊት ኬንያ እና ታንዛኒያ ሄጄ ነበር። የእኛ አገር ፓርኮች እንዴት መልማት አለባቸው የሚለውን ተሞክሮ ለመውሰድ ማሳይ ማራ እና ሰረንጌቲ ፓርኮችን ጎብኝቻለሁ።”

ከዚህ በተጨማሪም እንደሀገር ተይዞ እየተሠራ ያለውን በአማራ ክልል የሚገኘውን የጎርጎራ የቱሪዝም ልማት መዳረሻ ዲዛይንንም እንደሠራ ጠቅሷል።
አርክቴክት ኃይሌ የዚህን ፕሮጀክት ዲዛይንንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት በኮይሸ ተገኝቶ ማቅረቡንም ተናግሯል።

ቀጣይነት ያለው ዲዛይን አርክቴክት ኃይሌ ስለ ወደፊት ህልሙ እና አሁን እየሠራው ስላለ ሥራ ሲጠየቅ ቀጣይነት ስላላቸው ፕሮጀክቶች በተደጋጋሚ ይናገራል።

“አባቶቻችን ማንኛውንም ልማት ሲሰሩ ከተፈጥሮ ጋር እንዲስማማ አድርገው ነው። ተፈጥሮን የሚጎዳ ማንኛውንም ነገር አያበረታቱም” የሚለው ኃይሌ፣ ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ ዓለማችን ፈተና እየገጠማት እንደሆነ ያስታውሳል።
አክሎም “ቀጣይነት ባላቸው ነገሮች እሳቤ ከዚህ በፊት የተበላሸው ወደኋላ እንዲመለስ፣ እንዲሁም ዛሬ እየተገነባ ያለው ደግሞ ተሻሽሎ አንዲገነባ ይታሰባል።”

ነገር ግን እሱ እንሚታዘበው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ አይነት ግንባታዎች የተበላሸውን ለማስተካከል፣ የወደፊተንም ለመጠበቅ መደረግ ያለበትን ማዕከል ያደረጉ አይደሉም።
“ፕሮጀክቶች ያለጥናት ይታቀዳሉ። ይገነባሉ። መጀመሪያ እና መጨረሻቸው አይታወቅም። ወደፊት ለምትሄደው ዓለምም እየሠራን አይደለም። አባቶቻችን ያወረሱንንም ያህል እየሠራን አይደለም። እንደ አገር መካከል ላይ [ተንጠልጥሎ] የቀረ ነገር አለን።”

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ እንደሚለው በኦሮሞ አባቶች ባሕል መሠረት “. . . አምስቱ ኦዳዎች በማለት ለእኛ እንዳወረሱን፣ እኛም ደግሞ ለመጪው ትውልድ መቆየት የሚችሉ ቀጣይነት ያላቸው ግንባታዎችን ማቆየት አለብን የሚል ፍላጎትም ተስፋም አለኝ::

ተፈፀመ

Via BBC Amharic

@etconp
1.4K viewsItoophiyaa‍ , 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:31:02 ገፅ 2

አርክቴክት ኃይሌ ማን ነው?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በግንደ በረት ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ካቺሲ ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው።

የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም ተምሮ ያጠናቀቀው በትውልድ አካባቢው ነው።

በኋላም በወለጋ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸር የትምህርት ዘርፍ አምስት ዓመት ካጠና በኋላ በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል።

ከተመረቀ በኋላም ለሁለት ዓመታት በሐዋሳ እና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት አገልግሏል።

ከዚያም የሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸራል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፍ አጠናቅቋል።

ተመርቆ እንደጨረሰም የራሱን የግል ድርጅት ‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ በሚል ስያሜ በማቋቋም እየሠራ መሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

“ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ውስጥ ነው” የሚለው ኃይሌ፣ በኮንታ አካባቢ ያለው የተፈጥሮ ውበት እንደሚማርከው ይናገራል።

“የአፍሪካ ተራራዎች ተሰብስበው ዳውሮ ከትመዋል ይላሉ ሰዎች” በማለት አካባቢው በተፈጥሮ ሀብት የታደለ መሆኑን ይገልጻል።

በሌላ በኩል የዳውሮ ሕዝብ ያለው ባህል፣ ትውፊት እና ሕግጋት ከዚህም ባሻገር በአካባቢው ያለው ሰላም አስተማማኝ መሆኑንም ይጠቅሳል።
ከዚህ በተጫመሪ ሕዝቡ ለእንግዳ የሚያደርገው አቀባበል የተለየ መሆኑ አካባቢው ለጎብኚ ምቹ እና ሁሉን የያዘ እንደሆነ ይመሰክራል።

አርክቴክት ኃይሌ እንደሚለው ለእነዚህ ፕሮጀክቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በቅርበት የሚደረገው ክትትል እና የአካባቢው ሰላም ሥራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ አድርጓል።

Via BBC amharic

@etconp
1.1K viewsItoophiyaa‍ , 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:31:02 ገፅ 1

ይህ የመዝናኛ ስፍራ ልማት የኮይሻ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ ልማት የሚባለው ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሲሆን በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ የሚገኝ ነው።

አካባቢው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ መገኛ ሲሆን፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችም መኖሪያ ነው።

በሚያዝያ ወር መጀመርያ ላይም በደቡብ ምዕራብ ክልል ውስጥ የሚገኘው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የሐላላ ኬላ ሪዞርት በይፋ ተመረቋል።
ገበታ ለሀገር በሚባለው ፕሮጀክት ስር የሆነው እና አዲስ በተመሠረተው ክልል ውስጥ የሚገኘው ይህ የመዝናኛ ስፍራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተመርቆ ተከፍቷል።

ይህ ሪዞርት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የህወሓት ተወካዮች ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት በመገናኘት የተነጋገሩበት ስፍራ ነው።

“ይህ ፕሮጀክት የአካባቢውን ታሪክ እና ባህል የተፈጥሮን እና የሰው ሰራሽ ሀብቶች አጣምሮ የያዘ ነው” ይላል ፕሮጀክቱን ዲዛይን ያደረገው አርክቴክት ኃይሌ።

በክልሉ እየተሰሩ ካሉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ውስጥ ትልቁ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ መሆኑን አርክቴክቱ አክሎ ይናገራል።

ከዚህም ባሻገር ረዥም እድሜ ያስቆጠረው እና ሰው ሰራሹ ልማት ሃላላ ኬላ የተባለው የድንጋይ ካብ እዚሁ ውስጥ ይገኛል።

“በዳውሮ ሕዝብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ የተገነባው የድንጋይ ካብ ወይንም ኬላ በግምት 1200 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ነው።

መጠሪያውንም ከመጨረሻው ንጉሣቸው ያገኘ ነው። እነርሱ ‘ካቲ ሃላላ ኬላ’ ይሉታል።”

በተጨማሪም የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ፣ እንዲሁም የኮይሻ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የዚሁ ትልቁ ፕሮጀክት አካል ናቸው።
በሃላላ ኬላ ፕሮጀክት ውስጥ በአምስተኛነት ደረጃ የታቀፈው ፕሮጀክት ጫራ የሚባል ማኅበረሰብን ማዕከል ያደረገ ነው።

“የጫራ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ ከአፈር ውስጥ ብረት የማውጣት እውቀት ያለው ሲሆን፣ እስከ ዛሬ ድረስም ይህንን ሙያ እየሰሩ ይገኛሉ። ይህ ማኅበረሰብ የራሱ የሆነ ባሕል እና ክህሎት ያለው ሕዝብ ነው።”
እነዚህ ልማቶች በአምስት ክላስተሮች በመክፈል ዲዛይኑን እንደሰሩ አክርቴክት ኃይሌ ይናገራል።

ከዚህ በተጨማሪ እነዚህን የልማት መዳረሻዎችን ደረጃ በደረጃ እስከ 25 ዓመታት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ ሠርቶ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ “በአጭር ጊዜው የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ውስጥ ሃላላ ኬላ እና ጨበራ ሪዞርቶች ይገኛሉ።”


Via BBC Amharic

@etconp
978 viewsItoophiyaa‍ , 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:30:36
ዛሬ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ይዘን መጥተናል

ETCONp አርኣያ ሰብ

በገበታ ለሀገር ከእየተገነቡ ካሉ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የሚገኝበት የኮንታ ዞን በተፈጥሮ ሀብቶች የታደለው ነው።

ኮንታ ግን በተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን በሙያቸው የተካኑ አርክቴክቶችም አግኝቷል።

በ እነዚህ አርክቴክቶች ዲዛይን የተደረገው እና በቅርቡ ተመርቆ ይፋ የተደረገው የሃላላ ኬላ ሪዞርት በርካቶችን አስደምሟል።

በደቡብ ምዕራብ ክልል፣ በኮንታ ዞን የኮይሻ ፕሮጀክት ይገኛል። ታድያ ከዚህ ፕሮጀክት ጀርባ እነማን አሉ? ቢቢሲ ከእነዚህ መካከል ወጣቱን አርክቴክት ኃይሌ ታደሰን አግኝቷል።

በቅድሚያ ግን ስለ ኮይሻ ፕሮጀክት ጥቂት ነገር እንበል።

Via BBC Amharic

@etconp
1.0K viewsItoophiyaa‍ , 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:01:02
#ADVERTISEMENTS

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ ድርጅት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት any Size & thickness
ጄ ቦልት

ሌሎች ከ ብረታ ብረት ጋር የተያያዙ ስራዎች [modefic] እንሰራለን።

ብረታብረት እንገዛለን እንሸጣለን።

ስልክ 0994941706 ወይም 0910379303 ደውለው ያግኙን

ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦ ቁ 1.መርካቶ
ቁ.2 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት
1.2K viewsItoophiyaa‍ , 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 20:35:37 ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በ Mix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :-

[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ
.
አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።
.
[2] - መኮማተር (Shrinkage )
.
ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking)   ያስከትላል ።
መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።
.
[3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ
.
Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።
.
[4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ
.
ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።

.
[5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )
.
ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ መጠጣት አለበት ።
«ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች
.
[6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን
.
በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።
.
[7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።

@etconp
1.9K viewsItoophiyaa‍ , 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 17:14:47 የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል እና በ ኢመይል አድራሻቹ አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ እንዲደርሳቹ ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።

ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ

እናመሰግናለን

@etconp
2.2K viewsItoophiyaa‍ , edited  14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 13:58:38 የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት አፓርትመንት ህንጻ ግንባታ አጠናቆ ለማስረከብ ማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል
****
መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የግንባታ ልምዱን ተጠቅሞ ከትርፍ ይልቅ
ለግንባታ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአነስተኛ ወጪ የግንባታ ሂደቱን ማጠናቀቅ የሚችል ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ ከያዛቸው የግንባታ ሥራዎች መካከል በድሬዳዋ ከተማ በሰባተኛ አየር ኃይል ካምፕ ውስጥ እየገነባ ያለው የሠራዊት የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት
ህንጻ ግንባታ አጠናቆ ለተጠቃሚዎች ለማስረከብ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር እንዳልካቸው ታዬ እንደገለጹት፣ የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት የአፓርትመንት ህንጻ ግንባታ በአንድ ምዕራፍ የሚገነባ ነው፡፡

20 ብሎኮችን የያዘው የጋራ መኖሪያ ቤት ባለ አንድ መኝታ አምስት ብሎኮች በአጠቃላይ 200 አባዎራዎችን ይይዛል፡፡

ባለሁለት መኝታ ስምንት ብሎኮች 288 አባወራዎችን ይይዛል፡፡ ባለ ሶስት መኝታ ሰባት ብሎኮቹ ደግሞ 280 አባዎራዎችን እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን በአጠቃላይ 768 አባዎራዎችን የሚይዝ ሲሆን ሁሉም ብሎኮች ባለ
አራት ወለል ናቸው፡፡

ከመኖሪያ ቤቶቹ በተጨማሪ ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ የጋራ መጠቀሚያ ቤቶች የተገነቡለት ሲሆን አፓርታማዎቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሥራ እየተሰራላቸው ነው፡፡

ሁሉም ብሎኮች ግባታቸው ማጠቃለያ ላይ ያሉ ሲሆን ቀሪው የፊኒሽንግ ሥራዎችን በመሰራት ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ በከፍተኛ ትኩረትና ፍጥነት በመከናወን ላይ በመሆኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታቸው ይጠናቀቃል ሲሉ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር እንዳልካቸው ታዬ ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ባለቤት በመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሆን ዲዛይንና ቁጥጥሩን የሚያከናውነው ደግሞ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
ነው፡፡

የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት በአፓርትመንት ህንጻ ግንባታ 300 ለሚደርሱ ዜጎች በቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡

@etconp
486 viewsItoophiyaa‍ , 10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 10:40:02 እዚህ ቻናል ላይ የተወያየንባቸውን ጉዳዮች በጥያቄ መልክ አቅርበናል... መልሶቹን እያንዳንዳቸው በቅርብ ቀን በ ሰፊው እንለቃለን...

ምን ያህሉን ይመልሳሉ??

መልስዎን በ @COTMp መወያያ Group ፃፉልን

1. Roller Compacted Concrete (RCC) ከኖርማሉ ኮንክሪት
በምን ይለያል?
.
2. Bending Moment ቢም ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚኖረው ምን
axis ላይ ነው? (x? y? ወይስ z? )
.
3. Centroid, Center of mass እና Center of gravity
ልዩነታቸው ምንድነው? አንድ ነጥብ ላይስ ሊያርፉ ይችላሉ?
.
4. Elastic እና Inelastic ማቴሪያሎች ልዩነታቸው ምንድነው?
Ductility ምንድነው?
.
5. Toughness ምንድነው?
.
6. Second Moment of Inertia ( Second moment of
Area) ምንድነው? ቢም ላይ የሚኖረው ተፅዕኖስ?
.
7. Mass moment of inertia እና Second Moment of
Inertia ልዩነታቸው ምንድነው?
.
8. Shear Force Diagram ምንድነው? Concentrated load
ሲሆን Constant, Linear ነው ወይስ Parabolic ቅርፅ
የሚኖረው? Distributed ሲሆንስ?
.
9. Bending Moment Diagram ምንድነው? Concentrated
load ሲሆን Constant, Linear ነው ወይስ Parabolic ቅርፅ
የሚኖረው? Distributed ሲሆንስ?
.
10. SFD ከፖዘቲቭ ወደ ኔጌቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይ
Moment Maximum ነው ወይስ Minimum ?ከኔጌቲቭ ወደ
ፖዘቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይስ?

11. አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል?? እንዴት??

12. Creep እና Fatigue
ምንድናቸው??

t.me/COTMp
934 viewsItoophiyaa‍ , 07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 10:24:09
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ ድርጅት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት any Size & thickness
ጄ ቦልት

ሌሎች ከ ብረታ ብረት ጋር የተያያዙ ስራዎች [modefic] እንሰራለን።

ብረታብረት እንገዛለን እንሸጣለን።

ስልክ 0994941706 ወይም 0910379303 ደውለው ያግኙን
ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦ ቁ 1.መርካቶ
ቁ.2 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት
925 viewsItoophiyaa‍ , 07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ