Get Mystery Box with random crypto!

የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት አፓርትመንት ህንጻ ግንባታ አጠናቆ ለማስረከብ ማጠቃለያ ምዕራ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት አፓርትመንት ህንጻ ግንባታ አጠናቆ ለማስረከብ ማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል
****
መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የግንባታ ልምዱን ተጠቅሞ ከትርፍ ይልቅ
ለግንባታ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአነስተኛ ወጪ የግንባታ ሂደቱን ማጠናቀቅ የሚችል ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ ከያዛቸው የግንባታ ሥራዎች መካከል በድሬዳዋ ከተማ በሰባተኛ አየር ኃይል ካምፕ ውስጥ እየገነባ ያለው የሠራዊት የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት
ህንጻ ግንባታ አጠናቆ ለተጠቃሚዎች ለማስረከብ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር እንዳልካቸው ታዬ እንደገለጹት፣ የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት የአፓርትመንት ህንጻ ግንባታ በአንድ ምዕራፍ የሚገነባ ነው፡፡

20 ብሎኮችን የያዘው የጋራ መኖሪያ ቤት ባለ አንድ መኝታ አምስት ብሎኮች በአጠቃላይ 200 አባዎራዎችን ይይዛል፡፡

ባለሁለት መኝታ ስምንት ብሎኮች 288 አባወራዎችን ይይዛል፡፡ ባለ ሶስት መኝታ ሰባት ብሎኮቹ ደግሞ 280 አባዎራዎችን እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን በአጠቃላይ 768 አባዎራዎችን የሚይዝ ሲሆን ሁሉም ብሎኮች ባለ
አራት ወለል ናቸው፡፡

ከመኖሪያ ቤቶቹ በተጨማሪ ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ የጋራ መጠቀሚያ ቤቶች የተገነቡለት ሲሆን አፓርታማዎቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሥራ እየተሰራላቸው ነው፡፡

ሁሉም ብሎኮች ግባታቸው ማጠቃለያ ላይ ያሉ ሲሆን ቀሪው የፊኒሽንግ ሥራዎችን በመሰራት ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ በከፍተኛ ትኩረትና ፍጥነት በመከናወን ላይ በመሆኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታቸው ይጠናቀቃል ሲሉ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር እንዳልካቸው ታዬ ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ባለቤት በመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሆን ዲዛይንና ቁጥጥሩን የሚያከናውነው ደግሞ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
ነው፡፡

የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት በአፓርትመንት ህንጻ ግንባታ 300 ለሚደርሱ ዜጎች በቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡

@etconp