Get Mystery Box with random crypto!

ገፅ 2 አርክቴክት ኃይሌ ማን ነው? አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

ገፅ 2

አርክቴክት ኃይሌ ማን ነው?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በግንደ በረት ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ካቺሲ ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው።

የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም ተምሮ ያጠናቀቀው በትውልድ አካባቢው ነው።

በኋላም በወለጋ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸር የትምህርት ዘርፍ አምስት ዓመት ካጠና በኋላ በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል።

ከተመረቀ በኋላም ለሁለት ዓመታት በሐዋሳ እና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት አገልግሏል።

ከዚያም የሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸራል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፍ አጠናቅቋል።

ተመርቆ እንደጨረሰም የራሱን የግል ድርጅት ‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ በሚል ስያሜ በማቋቋም እየሠራ መሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

“ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ውስጥ ነው” የሚለው ኃይሌ፣ በኮንታ አካባቢ ያለው የተፈጥሮ ውበት እንደሚማርከው ይናገራል።

“የአፍሪካ ተራራዎች ተሰብስበው ዳውሮ ከትመዋል ይላሉ ሰዎች” በማለት አካባቢው በተፈጥሮ ሀብት የታደለ መሆኑን ይገልጻል።

በሌላ በኩል የዳውሮ ሕዝብ ያለው ባህል፣ ትውፊት እና ሕግጋት ከዚህም ባሻገር በአካባቢው ያለው ሰላም አስተማማኝ መሆኑንም ይጠቅሳል።
ከዚህ በተጫመሪ ሕዝቡ ለእንግዳ የሚያደርገው አቀባበል የተለየ መሆኑ አካባቢው ለጎብኚ ምቹ እና ሁሉን የያዘ እንደሆነ ይመሰክራል።

አርክቴክት ኃይሌ እንደሚለው ለእነዚህ ፕሮጀክቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በቅርበት የሚደረገው ክትትል እና የአካባቢው ሰላም ሥራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ አድርጓል።

Via BBC amharic

@etconp