Get Mystery Box with random crypto!

ገፅ 3 የአርክቴክት ኃይሌ ሚና ምን ነበር? አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ ከዓመታት በፊት በመሠረተው | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

ገፅ 3

የአርክቴክት ኃይሌ ሚና ምን ነበር?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ ከዓመታት በፊት በመሠረተው ድርጅቱ አማካይነት በዚህ ፕሮጀክት እና በሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ከተሳተፉት አካላት መካከል ነው።

‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ የተባለው የእርሱ ድርጅት እና ሌላ ‘ስታዲያ ኢንጂነሪኒግ’ የተባለው ድርጅት በጥምረት የእነዚህን ፕሮጀክቶች ዲዛይን በመሥራት እንዲሁም ቁጥጥር በማድረግ ተሳትፈዋል።

“እነዚህን በክላስተር የተከፈሉትን ዲዛይኖች ‘ኮንሰፕት ዲዛይን’ ከማዘጋጀት ባለፈ የዲዛይን ቁጥጥር እና ክትትል እንድንሰራ ነው ኮንትራት የገባነው” ይላል።

እንደ ግሉ ደግሞ ኃይሌ የአርክቴክቸራል ቡድን መሪ በመሆን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳትፎ ማድረጉን ይናገራል።
“እድሜዬ 31 ነው፤ ዛሬ ደረስኩባቸው ብዬ የማስባቸው ነገሮች፣ ፍላጎቴን እና ጥረቴን አንድ ላይ አጣምሬ ሳያቸው ትንሽ የዘገየሁ ይመስለኛል” በማለት በራስ መተማመን በዚህ ፕሮጀክት ላይ መሳተፉን ይናገራል።

“ትልቁ ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው” የሚለው ይህ ወጣት፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ለአርክቴክቸር ትምህርት፣ ፍቅር እና ልዩ የሆነ ፍላጎት ማሳደሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ለመብቃት ረድቶታል።

አርክቴክት ኃይሌ በትምህርት እና በሥራው ላይ ከመበርታቱ ባሻገር በዚህ ዘርፍ በተቻለው መጠን ሌሎች ቦታዎች ያሉ ተሞክሮዎችን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል።

“ይህንን ፕሮጀክት ከማግኘቴ በፊት ኬንያ እና ታንዛኒያ ሄጄ ነበር። የእኛ አገር ፓርኮች እንዴት መልማት አለባቸው የሚለውን ተሞክሮ ለመውሰድ ማሳይ ማራ እና ሰረንጌቲ ፓርኮችን ጎብኝቻለሁ።”

ከዚህ በተጨማሪም እንደሀገር ተይዞ እየተሠራ ያለውን በአማራ ክልል የሚገኘውን የጎርጎራ የቱሪዝም ልማት መዳረሻ ዲዛይንንም እንደሠራ ጠቅሷል።
አርክቴክት ኃይሌ የዚህን ፕሮጀክት ዲዛይንንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት በኮይሸ ተገኝቶ ማቅረቡንም ተናግሯል።

ቀጣይነት ያለው ዲዛይን አርክቴክት ኃይሌ ስለ ወደፊት ህልሙ እና አሁን እየሠራው ስላለ ሥራ ሲጠየቅ ቀጣይነት ስላላቸው ፕሮጀክቶች በተደጋጋሚ ይናገራል።

“አባቶቻችን ማንኛውንም ልማት ሲሰሩ ከተፈጥሮ ጋር እንዲስማማ አድርገው ነው። ተፈጥሮን የሚጎዳ ማንኛውንም ነገር አያበረታቱም” የሚለው ኃይሌ፣ ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ ዓለማችን ፈተና እየገጠማት እንደሆነ ያስታውሳል።
አክሎም “ቀጣይነት ባላቸው ነገሮች እሳቤ ከዚህ በፊት የተበላሸው ወደኋላ እንዲመለስ፣ እንዲሁም ዛሬ እየተገነባ ያለው ደግሞ ተሻሽሎ አንዲገነባ ይታሰባል።”

ነገር ግን እሱ እንሚታዘበው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ አይነት ግንባታዎች የተበላሸውን ለማስተካከል፣ የወደፊተንም ለመጠበቅ መደረግ ያለበትን ማዕከል ያደረጉ አይደሉም።
“ፕሮጀክቶች ያለጥናት ይታቀዳሉ። ይገነባሉ። መጀመሪያ እና መጨረሻቸው አይታወቅም። ወደፊት ለምትሄደው ዓለምም እየሠራን አይደለም። አባቶቻችን ያወረሱንንም ያህል እየሠራን አይደለም። እንደ አገር መካከል ላይ [ተንጠልጥሎ] የቀረ ነገር አለን።”

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ እንደሚለው በኦሮሞ አባቶች ባሕል መሠረት “. . . አምስቱ ኦዳዎች በማለት ለእኛ እንዳወረሱን፣ እኛም ደግሞ ለመጪው ትውልድ መቆየት የሚችሉ ቀጣይነት ያላቸው ግንባታዎችን ማቆየት አለብን የሚል ፍላጎትም ተስፋም አለኝ::

ተፈፀመ

Via BBC Amharic

@etconp