ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በ Mix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :- [1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ . አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን። . [2] - መኮማተር (Shrinkage ) . ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking) ያስከትላል ። መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ። . [3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ . Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል። . [4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ . ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል። . [5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing ) . ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት። ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ መጠጣት አለበት ። «ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች . [6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን . በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል። . [7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም። @etconp 1.9K viewsItoophiyaa , 17:35