Get Mystery Box with random crypto!

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃ እና የሲኒማ ኮምፕሌክስ 4B+G+8 ግንባታዎችን ቀሪ ስራዎች ለ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃ እና የሲኒማ ኮምፕሌክስ 4B+G+8 ግንባታዎችን ቀሪ ስራዎች ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

ቀድሞ ግንባታውን ያከናውን የነበረው ስራ ተቋራጭ እቴቴ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶቹ በተለያየ አፈፃፀም ደረጃ ላይ እያሉ አቋርጦ በመውጣቱ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መነሻ ሆነው የቆዩት የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ግንባታዎች አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡

ጉዳያቸው በፍርድቤት በመያዙ እንዲሁም በጨረታ ሂደቶች ምክንያት ለ16 ወራት ገደማ ተቋርጠው የቆዩት እነዚህ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጨረታውን ካሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ጋር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ውለታ የማሰር ስነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃን ከ833 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ቀሪ ስራዎች ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የፕሮጀክት ውል መጠን ጨረታውን ያሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ስራዎቹን አጠናቆ ለማስረከብ የ6 ወራት ዕድሜ የተሰጠው ሲሆን ከፕሮጀክቱ አንገብጋቢነት አንፃር የሚሰጠው ቅድመ ክፍያ በጥምር ሂሳብ / Joint Account / የሚተዳደር ሆኖ ለግብዓት ግዢ ብቻ የሚውል መሆኑን ከስራ ተቋራጭ ጋር መግባባት ላይ እንደተደረሰና ይህም ወደፊት ሊከሰት ከሚችል የግብዓት ዋጋ ንረት እንደሚታደግ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል::

@etconp