Get Mystery Box with random crypto!

ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት! የቺካጎ የግንባታ ኤክስፖ (CHICAGO | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት!

የቺካጎ የግንባታ ኤክስፖ (CHICAGO Build Expo) እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 11 – 12 ቀን 2023 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በሀገረ አሜሪካ በቺካጎ ከተማ ይካሄዳል፡፡ ማኅበራችንም በዚህ ኤክስፖ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ አባላቱን ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉበትን የሥራ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

በዚሁ መሠረት በዚህ ግዙፍ በሆነ የግንባታ ኤክስፖ ላይ ተሳታፊ ለመሆን የምትፈልጉ የማኅበራችን አባላት ከግንቦት 4 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ብቻ እንድትመዘገቡ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡

1) ከኤክስፖው አዘጋጆች በተጣለብን ግዴታ መሠረት መመዝገብ የምትችሉት አባሎቻችን ከደረጃ 1 – 4 የምትገኙ ብቻ ናችሁ፤

2) አመልካቾች ባለትዳር የሆኑና ለዚህም ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

3) አመልካቾች በባለቤትነት በሚያስተዳድሯቸው ድርጅቶቻቸው ውስጥ 5 ያህል ቋሚ ሠራተኞች ቀጥረው የሚያሰሩ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

4) ዓለም አቀፍ የሆኑ የጉዞ ታሪክ ያላቸው አመልካቾች የተሻለ ዕድል እንዳላቸው ይታመናል፤

5) በቪዛ ማመልከቻ ወቅት መቅረብ የሚገባቸውና እንደ ሂሳብ መግለጫ ሰነዶች፣ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነዶች እና የመሣሠሉት አስፈላጊ ጉዳዮች እነድታቀርቡ ስትጠየቁ ብቻ የምታቀርቧቸው ይሆናሉ፤

6) ማኅበራችን ይህንን ሥራ ኤምባሲው ዕውቅና ሰጥቶት በዚህ ሥራ ላይ የተሠማራ ወኪል መጠቀም የግድ ስለሚሆንበት ይኽው ሙያተኛ የሚጠይቀውን ክፍያ፣ የቪዛ ቀጠሮ ለማመቻቸት የሚረዳውን የኤግዝቢሽኑን መግቢያ ክፍያ በአሜሪካን ዶላር ለመፈፀም እና ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለማከናወን የሚረዳና ተመላሽ የማይደረግ ብር 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) ከዚህ በታች በሚገኙት የማኅበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ገቢ በማድረግ ማረጋገጫ ማቅረብ ከአመልካቾች ይጠበቃል

6.1) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዑራኤል ቅርንጫፍ፣ ሂሳብ ቁጥር 1000336931197

6.2) ንብ ባንክ፣ ዑራኤል ቅርንጫፍ፣ ሂሳብ ቁጥር 7000001116358

7) ለአሜሪካ ኤምባሲ የሚከፈለው የኮቴ እና የቪዛ ከፍያ በእራሱ በአመልካቹ የሚፈፀም ሲሆን፤ የመክፈያ ጊዜው ሲደርስ ማኅበራችን ለአመልካቾች ያሳውቃል፤

8) የምዝገባ ቅፁን ለመሙላት በዚሁ ሥራ ላይ ለተሠማሩ ሰዎች የሚከፈለውን ክፍያእራሱ አመልካቹ የሚከፍለው ይሆናል፤

9) የአሜሪካን ሀገር ቪዛ ተሳክቶላቸው ያገኙ አመልካቾች ኤክስፖውን መጎብኘታቸው በኤምባሲው በኩል እንዲታወቅ ስለሚያስፈልግ አመልካቾች ይህንኑ አስቀድማችሁ የምታሳውቁን እንዲሆን እየጠየቅን ለዚህም የቡድን የጉዞ ቲኬት እና በኤክስፖው ከተማ የቡድን ማረፊያ ለማመቻቸት እንደሚያግዘን አስቀድመን ለማሳወቅ እንወዳለን፤

10) ምዝገባውን በማኅበራችን ፅ/ቤት ለማከናወንም የታደሰ ፓስፖርት፣ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ አስፈላጊ ነው፤

11) በማኅበራችን በኩል ለቪዛ ቃለ-ምልልስ የሚያግዝ መረጃ፣ ለዚሁ ቃለ-ምልልስ የሚያግዝ የቪዲዮ መግለጫ፣ ከቃለ-ምልልሱ በፊት ለሚያስፈልግ የልምድ ማካፈል አገልግሎቶችን ማኅበራችን ይሠጣል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

@etconp