Get Mystery Box with random crypto!

ሸጎሌ ስለሚገኘው አዲሱ የኢቢሲ ኮምፕሌክስ ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ በዚህ ወር መጨረሻ ይመረቃል ! | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

ሸጎሌ ስለሚገኘው አዲሱ የኢቢሲ ኮምፕሌክስ ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ በዚህ ወር መጨረሻ ይመረቃል !
...
የሰፈር ስያሜ ፤ ሼህ ኦጀሌ ( ሸጎሌ )
ሼህ ኦጀሌ የቤንሻንጉል ጉሙዝን አከባቢ ሲያስተዳድሩ የነበሩ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጅ ነበሩ። እኝህ ሰው ከአፄ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ለማዕከላዊው መንግስት ታማኝ ሆነው አከባቢውን ከጠላት ወረራ ሲከላከሉ ኖረዋል። በዚህም የተነሳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ሸጎሌ የሚባለው አከባቢ ቤተ-መንግስት አላቸው። በዚህም ምክንያት ሰፈሩ በስማቸው ሼህ ኦጀሌ ተባለ፤ በጊዜ ብዛትም ወደ ሸጎሌ ሊለወጥ ችሏል።
...
አጠቃላይ መረጃ

- ጠቅላላ የቦታ ስፋት 10 ሺ ሄክታር
- ስፍራው የሜቴክ የነበረ
- 1983 ዓ/ም የሸጎሌ ፍንዳታ የተከሰተበት
- ዘጠኝ የሬዲዮና ቲቪ ስቱዲዮና ቢሮ የያዙ ሁለት ህንፃዎች ፣ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ፣ ክበብ ፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ፣ ግራር ጋርደን ፣ አንፊ ትያትር ፣ የአራት ኪ/ሜ የመንገድ ኔትወርክ ፣ የያዘ
- ከተጀመረ አንድ ዓመት አካባቢ ሆኖታል
...
የዲዛይን ፍልስፍና

- ምቹ የስራ ከባቢ ግቢ
- የቀረፃ አማራጭ እና የከተማ ግብርናን ያቀናጀ ሀይቅ ፤ ለውበት ለዓሳ እርባታ ፣ ለፕሮግራም ቀረፃ
- ስፖርት ፊልድ ፣ ኮንሰርት ፣ ለሰራተኞች መዝናኛ ግቢ አቀናጅቶ የያዙ
- በሀገር ውስጥ ማቴሪያልና ኮንትራክተሮች የተሰራ
...
ስቱዲዮና ህንፃ

- የኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክን የሚያሳይ ሙዚዬም
- ግልፅና አርጎኖሚክ የቢሮ አደረጃጀት
- ማንበቢያ ፣ ኢዲቶሪያል ሩም ፣ ኤዲቲንግ ወርክስቴሽንና ስቱዲዮ ( all in one news studio Design) ሴትአፕ የያዙ
- ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ
- ብሉንበርግ ዲዛይን ወርክስቴሽን ቴብል
...
የሬዲዮ ፣ መዝናኛ እና ቋንቋዎች ህንፃ
- ሦስት የሬዲዮ ስቱዲዮ ፣ ሁለት ሃይብሪድ ስቱዲዮና ሁለት የቴሌቪዥን ስቱዲዮ
- የሚድያ ኮንቨርጀንስን ታሳቢ ያደረገ የሬዲዮና ሃይብሪድ ዲዛይን
- ምቹና ሳቢ የሃላፊዎች ቢሮ
- መንትያ የቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች (ስምንት ሜትር ቁመት ፣ ሦስት ደረጃ ሳውንድ ፕሩፍ )
- ከተፈጥሮ ጋር የተዋሃዱ
- በቅርቡ ተመርቆ መደበኛ ስርጭቱን የጀመረው የልጆች ዓለም የቴሌቪዥን ጣቢያ ያካተተ
...
የስፖርት ፊልድ

- የእግር ኳስ ሜዳ አራት ደረጃ ያለው ፣ ለኮንሰርት በሺዎች የሚቆጠሩ ታድሚያንን ማስተናገድ የሚችል
- ስድስት መቶ ሰዎችን የሚይዝ አንፊ (የሜዳ ቴኒስ ፣ ባስኬት ቦልና የእጅ ኳስ )
...
ግራር ጋርደን

- በተፈጥሮ ድንጋይ ፣ ፋውንቴንና አበባዎች ያሸበረቀ ለኢንተርቪውና ውይይት ፣ ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን ምቹ ቦታ
...
የተፈጥሮ ሀይቅ

- ስምንት ሺ ካሬ ስፋት
- ከጉለሌ እፅዋት ማዕከት ተራራ ምንጭን በማጎልበት የተሰራ የተፈጥሮ ሀይቅ
- ድልድይ ፤ አንድ መቶ ሃምሳ ሰው የሚይዝ አንፊ ትያትር ያለው
- ዙሪያው በእግር መንገድ የተከበበ
- አሳዎች እየረቡበት ያለ
...
የሰራተኞች ክበብ

- ለቀረፃና ለመዝናናት የሚሆን
- የእፅዋት ማዕከሉ ጫካ ጥሩ እይታ
- የጓሮውን ምርቶች የሚጠቀም
- ከተቋሙ በጡረታ የወጡ ባለሙያዎች የሚያስተዳድሩት

Via FM Addis 97.1

@etconp