ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች — የቴሌግራም ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @eotcy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.20K
ተመሳሳይ ቻናሎች ያልተመደበ
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

የቻናል ስታትስቲክስ
34.2% የተሳትፎ መጠን
2,804 እይታዎች / ልጥፍ
0 ልጥፎች / ቀን

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

16 aug 2024
በጣም አስተማሪ  ታሪክ

ይነበብ

አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል ቀስ በቀስ ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡
ከዚያም ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡ ‹‹ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡
ከሞተሩ ጎን አንድ ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ጽሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይ ይህንን ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል ታዲያ አደራ አንተም እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡
በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ልጨምረው ወይስ ልጠጣው እዚጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው ስለዚህ ልጠጣውና ህይወቴን ላድን ፡ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም አሰበና በሃሳብ ተወጠረ በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ አለ ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ በፍፁም ‹‹ውሃውን ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዘለዓለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› አለ፡፡
ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ሞተር ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡ ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ የሚፈልገውን ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይ አካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ ሆነ ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ ጨመረበት ‹‹እመኑኝ በትክክል #ይሰራል›› አለ፡፡


እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለራስ ማሰብ በህይወት መኖር ነው ለሌላው ማሰብ ግን ሰው መሆን ነው ያለህን ሳትሰስት ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል፡፡ ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ  ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡
ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲ ይለናል 

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 1ኛ ቆሮንቶስ 13÷1-8

  መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት አለው፡፡ አንዳንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ

ምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በፍቅር ይሁን

መልካም ቀን

꧁  ይ ላ ሉ ꧂

https://t.me/eotcy
5.0K views༒︎𝔚𝔢𝔫ø𝔫 𝔚ℯ𝓃𝒶, 05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
20 aug 2022
ይህን ያውቁ ኖሯል

አርፈው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን

፩..ሊቀ ነቢያት ሙሴ
፪..ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
፫..ጻድቁ ዮሴፍ (አረጋዊው ዮሴፍ)
፬..መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
፭..የቅዱስ ዮሐንስ አባት (ካህኑ ዘካርያስ)
፮..ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ

እስከ አሁን በሕይወት በብሔረ ሕያዋን ያሉ እና ሞትን ያልቀመሱ ግን ወደፊት የሚሞቱ ተሰውረው ያሉ አባቶች።

፩..ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል)
፪..አብነ አረጋዊ ዘሚካኤል (ጥቅምት 14 ቀን ተሰውሯል
፫..ርዕሰ አበው ሄኖክ (ሐምሌ 25 ቀን ተሰውሯል)
፬..ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ (ጥር 6 ቀን ተሰውሯል)
፭..ነቢዩ እዝራ
፮..ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ፣ ነባቤ መለኮት (ጥር 4 ቀን ተሰውሯል)
፯..ንጉሥ ነአኩቶ ለአብ (ሕዳር 3 ቀን ተሰውሯል)
፰..አቡነ ክፍለ ማርያም ዘትግራይ (የካቲት 20 ቀን ተሰውረዋል)
፱..አቡነ ገሪማ ይስሐቅ (ሰኔ 17 ቀን ተሰውረዋል)
፲..አቡነ አፍጼ (ግንቦተ 29 ቀን ተሰውረዋል)
፲፩..አቡነ ሊቃኖስ (ሕዳር 28 ቀን ተሰውረዋል)
፲፪..የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ልጅ ዳግማዊ ቂርቆስ (ታኅሣሥ 12 ተሰውረዋል)
፲፫..አባ ገብረ ሕይወት በአስቦት ገዳም (በ1945 ዓ.ም ተሰውረዋል)
፲፬..አባ በላይ ወ/ሚካኤል በአስቦት ገዳም (ሐምሌ 7 ቀን ዓ.ም (ተሰውረዋል)

በዚህ በተጨማሪ ስማቸው ያልተጠቀሱ እናንተ የምታውቋቸው የተሰወሩ ቅዱሳን ካሉ በኮሜንት መስጫው ላይ ጻፉልን!

የቅዱሳን ምልጃቸው በረከታቸው ከሁላችን ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን
Https://t.me/eotcy
608 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች 8.20K ተመዝጋቢዎች ያሉት የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ ግምገማዎች፣ ደረጃ እና ዝርዝር ስታቲስቲክስ ይገኛሉ።
በዚህ ገጽ ላይ "ወደ ቻናል ይሂዱ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ወይም @eotcy ን በቴሌግራም መተግበሪያ ውስጥ ይፈልጉ። እንዲሁም የቻናሉን የተጠቃሚ ስም ገልብጠው በቴሌግራም መፈለጊያ ውስጥ መለጠፍ ይችላሉ።
አዎ፣ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ነፃ የቴሌግራም ቻናል ነው። ሁሉንም ልጥፎች ያለምንም ክፍያ መከታተል እና ማንበብ ይችላሉ።
የኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ቻናል በአሁኑ ጊዜ 8.20K ተመዝጋቢዎች አሉት። የተመዝጋቢዎች ቁጥር በመደበኛነት ይዘመናል።
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ይዘቱን በዋናነት በአማርኛ ቋንቋ ያትማል። መልእክቶቹን ለማንበብ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ ቻናሉን በቴሌግራም ይክፈቱ።
አዎ፣ ተመሳሳይ የያልተመደበ ቻናሎችን ከታች "ተመሳሳይ ቻናሎች" በሚለው ክፍል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። ተዛማጅ የቴሌግራም ቡድኖችን፣ ቦቶችን እና ተለጣፊዎችንም እናሳያለን።
መልእክቶቹ በቴሌግራም ውስጥ ይነበባሉ፦ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ን ይክፈቱ። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ የተመዝጋቢዎች ብዛት፣ ግምገማዎች እና ስታቲስቲክስ ያገኛሉ።
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች avatar
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች @eotcy
በቴሌግራም ይክፈቱ