Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @eotcy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.36K
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ
@EOTCY
ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት?
➢ የተለያዩ ትምህርቶችን
➢ መጣጥፎችን
➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን
➢ ተከታታይ ትምህርቶችን
➢ ብሒለ አበው
➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን
አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇
@EOTCY

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-06-30 20:44:27
ምን ልታይ ትወዳለህ

ዘኬዎስ የሚባለው ሰው በዘመኑ ምርጥ የተባለለት ሀብታም, በሰው ዘንድ የተከበረ ነበር ይህ ሰው በኛ ቋንቋ ሚሊየነር ይባል ነበር

ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ። ይላል የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር:: ባንድ እጁ ስልጣን ባንድ እጁ ባለጠግነትን ይዞ ነበር

ነገር ግን ጌታችን ወደ ኢያሪኮ እንዲያልፍ በሰማ ጊዜ አስደናቂ ነገር አደረገ በልቡ ጌታን ሊያይ ወደደ ግን አጭር ሰው ነበር ግርግሩ ሌላ ነው ግፊያው ሌላ ነው ስለዚህም ይህ የተከበረ ሰው ራሱን ያዋርድ ዘንድ ወደደ አንቱ የተባለው ዘኪዎስ ለብዙዎች አለቃ የሆነው ይህ ሰው ሁሉ የሞላለት ሰው ከዛፍ ላይ ወጥቶ ተንጠለጠለ ስድቡንም ዘለፋውንም ትችቱንም ሳይፈራ ከሾላ ዛፍ ላይ ወጣ አንድ ማየት የናፈቀው ነገር ነበር ሁሉ የሞላለት ሰው ቢሆንም መንፈሱ ግን ጎዶሎ ነበር ውስጡ ባዶ ነበር አምላኩን ጌታውን ማየት እጅግ ናፍቆ ነበር ጌታም አይቶ ወደደው ወደ እልፍኙ ገብቶ አብርቶ ማዕድን ቆረሰ ጌታችንም እንዲህ አለ :-የሉቃስ 19:9፤ ኢየሱስም አለው፦ "ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል" ይህ ሰው ብዙ ብር ቆጥሮዋል መዳን ግን አልሆነለትም ነበር ይህ ሰው የስልጣን ማማ ጫፍ ላይ ወጥቶዋል መዳን ግን አልሆነለትም እውነተኛ የሕይወት እርካታ የሆነውን ጌታ ሲያይ ግን ዳን እንደውም እጁ ላይ ያለውን ሀብታ ናቀ በስግብግብነት የሰበሰበውን እኩሌታውን ለድሆች አካፍላለው ከማንም ደግሞ በግፍ ወስጄ ቢሆን እጥፍ እመልሳለው አለ ልቡ በክርስቶስ ፍቅር ተነደፈ እኛስ ምን ማየት ናፍቀን ይሆን???
Https://t.me/eotcy
Https://t.me/eotcy
Https://t.me/eotcy
445 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, edited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 02:01:08 23,23,23,23,23,23,23

#የቅዱስ_ጊዮርጊስ ታሪክ ባጭሩ

#ጊዮርጊስ ማለት 《ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ》 ማለት ነው፡፡ #ሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሀገሩ ፍልስጤም ልዩ ስሟ ልዳ ሲሆን የተወለደው በ277 ዓ.ም ጥር 20 ቀን ነው፡፡
አባቱ ዞሮንቶስ ወይም አንስጣስዮስ የልዳ መኳንንት ሆኖ ተሹሞ ይኖር ነበር፤
እናቱ ቴዎብስታ ወይም አቅሌስያ #ከቅዱስ_ጊዮርጊስ ሌላ ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ አሳደገው፡፡ መስፍኑም በጦር ኃይል አሰለጠነው፡፡ ፳ ዓመትም በሞላው ጊዜ መስፍኑ የ15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ጌታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ፡፡

#ቅዱስ_ጊዮርጊስም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሀገር ሄደ፡፡ በቤሩት ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጆቻቸውን ይገብሩለት ስለነበር ሰማዕቱ ደራጎኑን በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል፡፡

ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግስቱ ገብቶ በከሃዲያኑ ሰባው ነገሥታት ፊት ክርስቲያን መሆኑን በመመስከር የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡
ዱድያኖስም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ ‹‹አንተማ የኛ ነህ በዐሥር አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ›› አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ‹‹ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም›› አለው፡፡

በዚህ ጊዜ ዱድያኖስ እጅግ ተናዶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ጌታችንን ‹‹ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት›› በማለት መከራውን ይታገስ ዘንድ ለመነው፡፡

#እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ፈቃዱን ይፈጽምለት ብዙ በመከራው ሁሉ ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ ሦስት ጊዜም ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡

በመጀመሪያም ዱድያኖስ በእንጨት ላይ ካሰቀለው በኋላ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው፡፡ #ጌታችንም #ቅዱስ_ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡

ዳግመኛም በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ ሥጋውንም በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነሰነሰበት፡፡ ሥጋውም ተቆራርጦ መሬት ላይ ወደቀ፡፡

#ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ከፈወሰውና ‹‹ገና ስድስት ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛውም ታርፋለህ›› ካለው በኋላ በመከራውም ሁሉ እርሱ እንደማይለየው ነገረው፡፡

ዱድያኖስ #ቅዱስ_ጊዮርጊስን ከዚያ ካደረሰበት አሠቃቂ መከራዎች ሁሉ ድኖ ፍጹም ጤነኛ መሆኑን በተመለከተ ጊዜ እጅግ ደንግጦ 《የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ብዙ ወርቅ እሰጠዋለሁ》 ብሎ ተናገረ፡፡

አትናስዎስ የተባለ መሰርይ《ጠንቋይ》 አንዲትን ላም በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ስትሞት ለንጉሡ አሳየውና ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሚያሸንፍ ምልክት አሳየ፡፡ ንጉሡም ያሸንፍልኛል ብሎ ደስ አለው፡፡ መሰርይውም ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞበት እንዲጠጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው።

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ ግን ስመ #እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል፡፡ በዚህም ጊዜ ጠንቋዩ ማረኝ ብሎ ከእግሩ ሥር ወደቀ፡፡

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ ግን በመንኰራኩር አስፈጭቶ ከትልቅ ጉድጓድ ጥሎት ደንጊያ ዘግቶበት አትሞበት ሄደ፡፡ #ጌታችንም የተፈጨውን #የቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥጋ በእጁ ዳስሶ ፈውሶታል፡፡

ወደ ከሃዲውም ንጉሥ ተመልሶ ‹‹ #አምላኬ_ከሞት_አዳነኝ›› በማለት መሰከረ፡፡ ንጉሡም ዳግመኛ በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አነደደበት ነገር ግን እሳቱ ደሙ ሲንጠባጠብበት ጠፍቷል፡፡ ጌታችንም ፈወሰው፡፡

ከዚህም በኋላ ዱድያኖስ #ቅዱስ_ጊዮርጊስን ‹‹ #ኢየሱስ_አምላክ መሆኑን አሳየኝ›› ቢለው የለመለሙትን ዕፅ አድርቆ፣ የደረቁትን ደግሞ አለምልሞ፣ ከሞቱ 430 ዓመት የሆናቸውን ሙታንን አስነሥሰቶ አሳይቶታል፡፡

ነገር ግን ንጉሡ ልቡ ክፉ ነውና በርኃብና በጽም ይሙት ብሎ ምንም ከሌላት መበለት ቤት አሳስሮታል። እርሷም የሚቀመስ ስትፈልግ ቤቷን በእህል አትረፍርፎ የታሰረበትን ግንድ ማለትም የቤቱን ምሰሶ አለምልሞታል፡፡ ልጇም ጆሮው የማይሰማ ነበርና ፈወሰላት፡፡ መበለቲቷንም ከነልጆቿ አጥምቆአቸው #መልአኩ_ቅዱስ_ሚካኤል ከእስራቱ ፈትቶት ተመልሷል፡፡

ዳግመኛም ንጉሡ ዱድያኖስ ጭፍሮቹን ‹‹በመንኰራኩር ፈጭታችሁ አጥንቱን ደብረ ይድራስ ተራራ ላይ ወስዳችሁ ዝሩት›› ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም #የቅዱስ_ጊዮርጊስን ሥጋ በመንኰራኩር ፈጭተው ወስደው በተራራው ላይ ቢረጩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ ‹‹ #ጊዮርጊስ_ቅዱሱ #ለእግዚአብሔር፣ #ጊዮርጊስ_ሰማዕቱ #ለእግዚአብሔር›› እያሉ አመስግነዋል፡፡

አሁንም #ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣውና ሥጋውን ፈጭተው በተራራም ላይ ሥጋውን በትነውት ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ ደረሰባቸውና ‹‹ቆዩኝ ጠብቁኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት ‹‹አምላኬ ከሞት አዳነኝ›› አላቸው፡፡

ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ስር ወድቀው ይቅር በለን ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውሃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል፡፡

እነርሱም በንጉሣቸው ፊት ሄደው ስለጌታችን በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ አጥንቱ ተፈጭቶ በደብረ ይድራስ ተራራ በመንኮራኩር ተፈጭቶ ሰማትነትን ተቀብሏል።
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዛሬ ወርሐዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
አ አ አ
ሜ ሜ ሜ
ን ን ን
@eotcy
@eotcy
@eotcy
3.2K views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, edited  23:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 01:44:57
892 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, 22:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ