Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @eotcy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.36K
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ
@EOTCY
ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት?
➢ የተለያዩ ትምህርቶችን
➢ መጣጥፎችን
➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን
➢ ተከታታይ ትምህርቶችን
➢ ብሒለ አበው
➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን
አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇
@EOTCY

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-25 21:44:41

እርግጠኛ ነኝ ይህን ጽሁፍ ካነበባችሁ በኋላ የሚሰማችሁ የመንፈስ እርካታን ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያቅትም።


በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጎድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣምም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለተ አልቻለም፡፡ አህያዋም ብዙ ያገለገለችና ያረጀች ስለሆነች እንዲሁም ሌሎች እንስሳትም ወደ ጉድጓዱ እንዳይገብበት በማሰብ ጉድጓዱ ውስጥ ሊቀብራት ወሰነ፡፡
@eotcy
ጎረቤቶቹንም አስተባብሮ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ፡፡ አህያዋ ይህን ስትመለከት እየቀበራት መሆኑነ ተረዳችና በሰቀቀን አለቀሰች፡፡ይሁን እንጂ አህያዋ አፈር ሲደፋባት አንድ ነገር ታደርግ ጀመር፡፡ አፈሩ በተደፋባት ቁጥር አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ጀመር፡፡በተደጋጋሚ ከሚደፋባት አፈር ላይ መቆምም ትጀምራለች፡፡በሂደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች ከፍ እያለች በመጨረሻም ጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ቻለች፡፡በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ሰዎች በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈፅማል!!!!!!!
ከእግዚአብሔር አይምጣ እንጂ ከሰው የመጣ እሱ ይመልሰዋል !!!!!! አሜን !!!!!!!!!! ! ካነበብኩት!
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»

@eotcy
535 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 22:04:11
+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+
...
በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል:: የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
እግዚአብሔርም :- "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው። አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው። ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ። ጥቂትም እንደተጔዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው:: ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ። በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት ቀድሞ ያየውን ጥላ አጣው። ከዚያም ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላ፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው :- "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ:: ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት። ለምን ተውከኝ ?" ::

እግዚአብሔርም :- "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም። ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት።

ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው። እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም። እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም።

ጌታ ሆይ ስንት ዘመን ተሸክመኸኝ ምነው ተውከኝ ብዬህ ይሆን? ደካማው ልጅህን ይቅር በለኝ።

https://t.me/eotcy
476 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , edited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:34:00 . መስቀል ለምን እንሳለማለን

መስቀል ስንሳለም ምዕመኑ ይፍቱኝ ይባርኩኝ ብለን በፍጹም ትህትና በእምነት ሆኖ ወደ ካህኑ እንቀርባለን ካህኑም በመስቀሉ የላይኛው ክፍልና በታችኛው ክፍል ግንባራችንና አፋችንን አሳልመው ይባርኩናል።
@eotcy
ግንባሩን ማስነካታቸው በአዕምሮ የተሰራውን ከንፈሩን ማስነካታቸው በመናገር የተሰራውን ኃጥያት እግዚአብሔር ይተውላችሁ ማለታቸው ነው።ቀዳሲያኑ ለቅዳሴ መምህሩ ለማስተማር ዘማሪው ለመዘመር ሲነሱ በማዕረግ ከፍ ካሉት ካህን መስቀል የሚሳለሙት።
ኃጢያት በሶስት መንገድ ይሰራል
፩. በገቢር (በመስራት)
፪.በነቢር (በመናገር)
፫.በኅልዩ (በማሰብ)
@eotcy
ታዲያ በገቢር በመስራት የተፈጸመውን ኃጢአት ለማስተሰረይ ጊዜ ሰጥቶ ወደ ንስሐ አባት ቀርቦ በኑዛዜ ቀኖና መቀበልና ቀኖናውን መፈፀም ይገባል። ለዚህ ነው አሁን አሁን በከተሜው ዘንድ እምብዛም ባይታይም ወንጌሉ የገባቸው ክርስቲያኖች ካህን ባዩ ቁጥር መስቀል ለመሳለም የሚጓጉት። ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ማድረጋችሁን አትዘንጉ
እያወቅን በድፍረት ሳናውቅ በስሕተት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር ይበለን
@eotcy
564 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , edited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:33:39
474 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 14:37:20 ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል።

ደንግል ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።

ልዑሉን የወለድሽ ልዕልት ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ።

ድንግል ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። #ትንሣኤሽን #የሚያምን ሁሉ #አሜን ይበል።

ምልጃሽ ኢትዮጵያን ይታደግ። ለዓለም ምህረት ይሁን ።

@eotcy
@eotcy
@eotcy
605 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 06:49:44
"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ ባንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡"

በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
@eotcy
508 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 06:22:09
የፈጣሪ ቸርነት ተነግሮ አያልቅም
፤ ለምሳሌ አንዱ የዛሬዋን ቀን ማየታችን ነው ምክንያቱም ይቺን ቀን ለማየት ያልታደሉ ብዙ አሉና።
ሁሌም ከእንቅልፍ ስንነሳ ከፈጣሪ ቸርነት ቀጥሎ ማሰብ ያለብን የምንኖርለትን የህይወት አላማ ነው። መቼም ማንኛውም ፕሮጀክት ያለ አንዳች አላማ አይጀመርም፤ እህቴ ያንቺ ትልቁ ፕሮጀክት ደግሞ የምትኖሪለት የህይወት ግብ ነው። አይ እኔ አሁን የምትለውን ነገር አስቤበት አላውቅም ካልሽ፤ በይ አሁን ማሰብ ጀምሪ፤ ምን ማሳካት የት መድረስ ምን መጨበጥ እንደምትፈልጊ ማወቅ ወሳኝ ነው።
ሌላውን ትተህ አለምን የሚያሸብሩ ሰዎችና ቡድኖች እንኳን አላማ አላቸው፤ ወዳጄ አሁንም ቢሆን አልረፈደም መዳረሻህን አሁን ማሰብ ጀምር! ግን ግልፅና ሁሌም ስታየው ሀይል የሚጨምርልህ መሆን አለበት፤ ከሰው የህይወት አላማ ኮርጀህ ከፃፍክ ለጊዜው ሙቀት ይሰጥሀል እንጂ የምትፈልገውን የመንፈስ ጥንካሬ አይፈጥርልህም። ስለዚህ የራስህን ማሳካት የምትፈልገውን የስኬት ጫፍ ማወቅ አለብህ።

እንደ ሁሌውም ቀኑትን በጸሎት ይጀምሩ

ግሩም ሰንበት ተመኘንላችሁ

Https://t.me/eotcy
Https://t.me/eotcy
878 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , edited  03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 08:38:44 ይህን ያውቁ ኖሯል

አርፈው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን

፩..ሊቀ ነቢያት ሙሴ
፪..ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
፫..ጻድቁ ዮሴፍ (አረጋዊው ዮሴፍ)
፬..መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
፭..የቅዱስ ዮሐንስ አባት (ካህኑ ዘካርያስ)
፮..ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ

እስከ አሁን በሕይወት በብሔረ ሕያዋን ያሉ እና ሞትን ያልቀመሱ ግን ወደፊት የሚሞቱ ተሰውረው ያሉ አባቶች።

፩..ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል)
፪..አብነ አረጋዊ ዘሚካኤል (ጥቅምት 14 ቀን ተሰውሯል
፫..ርዕሰ አበው ሄኖክ (ሐምሌ 25 ቀን ተሰውሯል)
፬..ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ (ጥር 6 ቀን ተሰውሯል)
፭..ነቢዩ እዝራ
፮..ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ፣ ነባቤ መለኮት (ጥር 4 ቀን ተሰውሯል)
፯..ንጉሥ ነአኩቶ ለአብ (ሕዳር 3 ቀን ተሰውሯል)
፰..አቡነ ክፍለ ማርያም ዘትግራይ (የካቲት 20 ቀን ተሰውረዋል)
፱..አቡነ ገሪማ ይስሐቅ (ሰኔ 17 ቀን ተሰውረዋል)
፲..አቡነ አፍጼ (ግንቦተ 29 ቀን ተሰውረዋል)
፲፩..አቡነ ሊቃኖስ (ሕዳር 28 ቀን ተሰውረዋል)
፲፪..የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ልጅ ዳግማዊ ቂርቆስ (ታኅሣሥ 12 ተሰውረዋል)
፲፫..አባ ገብረ ሕይወት በአስቦት ገዳም (በ1945 ዓ.ም ተሰውረዋል)
፲፬..አባ በላይ ወ/ሚካኤል በአስቦት ገዳም (ሐምሌ 7 ቀን ዓ.ም (ተሰውረዋል)

በዚህ በተጨማሪ ስማቸው ያልተጠቀሱ እናንተ የምታውቋቸው የተሰወሩ ቅዱሳን ካሉ በኮሜንት መስጫው ላይ ጻፉልን!

የቅዱሳን ምልጃቸው በረከታቸው ከሁላችን ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን
Https://t.me/eotcy
608 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 19:51:32
" በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። " ማቴ 17÷ 2

እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
https://t.me/eotcy
https://t.me/eotcy
https://t.me/eotcy
876 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , edited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 20:35:57 ደጉ ሳምራዊ

ደጉ ሳምራዊ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ሳምራዊ ማለት ሀገር ጠባቂ ማለት ነው ኢየሱስ ክርስቶስም እረኛችን ጠባቂያችን ነው፤ ዮሐ 10፥11 1ኛ ጴጥ 2፥24
ሀገር ጠባቂ ሀገርን የሚጠብቀው ራሱን አሳልፎ በመስጠት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስም እኛን በነፍስም በስጋም የጠበቀን ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ሰጥቶ ነው፤ ደጉ ሳምራዊ ቁስለኛውን በሩቅ አይቶ አዘነለት፣ ቀርቦም በቁስሉ ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰለት

ወይኑ የቊስሉን ደም እንድያቆምለት እንዲያደርቅለት ነው።
ቊስል ቶሎ የሚደርቀው ከላይ ነው፤ ወዲያውኑ እየተሰነጣጠቀ ያሰቃያል፤ ለዚህም መከላከለያ እንዲያለሰልስለት ዘይቱን አፍስሶለታል።
ጌታችንም በሩቅ ማለትም በሰማይ መንበሩ ተቀምጦ ቊስለኛውን አዳም በዓይኑ ምሕረት አየው ገጸ ምሕረቱን መለሰለት ቀረበውም ባሕርዩን ባሕርይ አደረገ
የባሕርዩ መመኪያ ከሆነች ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ተዋሕዶ ሰው ሆኖ ተወለደ።
ወይን እንደማፍሰስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰለት ደሙን አፈሰሰለት። ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ወይኑን በጽዋ አድርጎ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈውስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው ያለው ለዚህ ነው። ማቴ 26፥27

እንደ ዘይት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሰጥቶታል። ይኽንን በተመለከተ
ቅዱስ ዳዊት ወይን የክርስቶስ ደሙ የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፤ ዘይትም ፊትን ያበራል መንፈስ ቅዱስ ሰውን ብሩኅ መልአክ ያስመስለዋል እህልም የክርስቶስ ስንዴ ሥጋው) የሰውን ጉልበት (ነፍሱን) ያጠነክረዋል። ብሏል
መዝ 103፥15

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም
እናንተ ከቅዱሱ ተቀብላችኋልና ሁሉንም ታውቃላችሁ፡፡ ያለው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ነው፡፡
ደጉ ሳምራዊ ከአህያው ወረደ ቊስለኛውን ማስቀመጡ የሚያመለክተው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መንበሩ መውረዱንና አዳምን በሰማይ መንበሩ ማስቀመጡን ነው።

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ
#በኢየሱስ_ክርስቶስ በሰማያዊ ሥፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ያለው ይኽንን ምስጢር ይዞ ነው። ኤፌ 2፥7
ምክንያቱም በተዋሕዶ አምላክ የሆነ ሥጋ በሰማይ የእሳት መንበር ተቀምጧልና።

#ደጉ_ሳምራዊ
ያከመውን ቊስለኛ ለእንግዶች ቤት ጠባቂ ማስረከቡ
ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት ያከማቸውን ምዕመናን ለመምህራን የማስረከቡ ምሳሌ ነው።

#ቅዱስ_ጴጥሮስን
ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጎቼን አሠማራ ያለው ለዚህ ነው። ዮሐ 21፥15።

ሁለት ዲኖሮች ደግሞ የሁለቱ ማለትም የብሉይና ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ምሳሌ ናቸው።

የሰው ሕይወቱ የሚጠበቀው በእነዚህ ነውና።

በሁለት ዲናር የተመሠሉ ቅዱሳን መጻሕፍት ምግበ ነፍስ ናቸውና። ቅዱስ ዳዊትም "ቃልህ ለጉሮሮየ ጣፋጭ ነው ከማር ይልቅ ጣፈጠኝ። ብሏል መዝ 118፥103

ደጉ ሳምራዊ የእንግዳ ቤት ጠባቂውን ከሁለት ዲናር በላይ ብታወጣ እኔ በተመለስኩ ጊዜ እከፍልሃለሁ አለው እንጂ ዋጋ የለህም አላለውም።

ይህ የሚያመለክተው መምህራን የተሰጣቸውን ሁለት ዲናር
ብሉይ ኪዳንን እና
ሐዲስ ኪዳንን ይዘው የምዕመናንን ሕይወት ለመጠበቅ ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትን ቢጽፉ ጌታ ሲመጣ የድካማቸውን ዋጋ እንደሚከፍላቸው ነው።)
@eotcy
ቅዱሳት ሊቃውንት
መጽሐፍ ቅዱስን ለማብራራት ንባቡን በመተርጎም ምስጢሩን በማራቀቅ አያሌ መጻሕፍትን ጽፈዋል። እነዚህም አዋልድ መጻሕፍት ይባላሉ። የቅዱሳን መጻሕፍት ልጆች ማለት ነው። የገድል የድርሳን እና የተአምር መጻሕፍት ቊጥርም ከአዋልድ መጻሕፍት ነው። እነርሱም የእግዚአብሔር ሰዎች #የእግዚአብሔርን ቃል እንደት እንደፈጸሙ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚያሳይ ነው።))
@eotcy
መጻፍ ማጻፍም መስማት ማሰማትም ዋጋ አለው። እንዲህ በተሰጡን ሁለት ዲናሮች ሥራ እንድንሠራ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍት በመጻፍና በማጻፍ እንድንመክርና እንድንመሰክር የተሰጠንን አደራ እንድንጠብቅ በዚህ ዓለም ተዋርደን ምእመናን የሚከብሩበትን ግብር ይዘን እንድንገኝ የሚያዝን ልቦና እንዲሰጠን የምናቆስል ሳይሆን የቆሰሉትን የምናክም እንዲያደርገን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን!

የሚያሳርፈን የእግዚአብሔርን ቃል እንማማር.......
@eotcy
556 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ