ይህን ያውቁ ኖሯል አርፈው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን ፩..ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፪..ጻድቁ አ | ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

ይህን ያውቁ ኖሯል

አርፈው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን

፩..ሊቀ ነቢያት ሙሴ
፪..ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
፫..ጻድቁ ዮሴፍ (አረጋዊው ዮሴፍ)
፬..መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
፭..የቅዱስ ዮሐንስ አባት (ካህኑ ዘካርያስ)
፮..ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ

እስከ አሁን በሕይወት በብሔረ ሕያዋን ያሉ እና ሞትን ያልቀመሱ ግን ወደፊት የሚሞቱ ተሰውረው ያሉ አባቶች።

፩..ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል)
፪..አብነ አረጋዊ ዘሚካኤል (ጥቅምት 14 ቀን ተሰውሯል
፫..ርዕሰ አበው ሄኖክ (ሐምሌ 25 ቀን ተሰውሯል)
፬..ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ (ጥር 6 ቀን ተሰውሯል)
፭..ነቢዩ እዝራ
፮..ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ፣ ነባቤ መለኮት (ጥር 4 ቀን ተሰውሯል)
፯..ንጉሥ ነአኩቶ ለአብ (ሕዳር 3 ቀን ተሰውሯል)
፰..አቡነ ክፍለ ማርያም ዘትግራይ (የካቲት 20 ቀን ተሰውረዋል)
፱..አቡነ ገሪማ ይስሐቅ (ሰኔ 17 ቀን ተሰውረዋል)
፲..አቡነ አፍጼ (ግንቦተ 29 ቀን ተሰውረዋል)
፲፩..አቡነ ሊቃኖስ (ሕዳር 28 ቀን ተሰውረዋል)
፲፪..የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ልጅ ዳግማዊ ቂርቆስ (ታኅሣሥ 12 ተሰውረዋል)
፲፫..አባ ገብረ ሕይወት በአስቦት ገዳም (በ1945 ዓ.ም ተሰውረዋል)
፲፬..አባ በላይ ወ/ሚካኤል በአስቦት ገዳም (ሐምሌ 7 ቀን ዓ.ም (ተሰውረዋል)

በዚህ በተጨማሪ ስማቸው ያልተጠቀሱ እናንተ የምታውቋቸው የተሰወሩ ቅዱሳን ካሉ በኮሜንት መስጫው ላይ ጻፉልን!

የቅዱሳን ምልጃቸው በረከታቸው ከሁላችን ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን
Https://t.me/eotcy
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

@eotcy
8.19K ተመዝጋቢዎች
ያልተመደበ ምድብ
መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ . @EOTCY. ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት?. ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን. ➢ መጣጥፎችን. ➢ መን...