Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcy — ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @eotcy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.36K
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ
@EOTCY
ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት?
➢ የተለያዩ ትምህርቶችን
➢ መጣጥፎችን
➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን
➢ ተከታታይ ትምህርቶችን
➢ ብሒለ አበው
➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን
አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇
@EOTCY

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-17 22:14:17 [ደብረ ታቦር]
@eotcy

❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ክብር ይግባውና ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አሥነስቶ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን ብርሃኑ የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)
❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡
❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት
1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡
❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡
❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ሲኾን ሙሴና ኤልያስም ጌታቸው ፈጣሪያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በተራራው ላይ መስክረዋል፡፡
ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡
❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው።
❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡
❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡
❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦
1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት
2) ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመን የነቢያትንና የሐዋርያትን ክብርና ምልጃ እንደምታስተምር ለማሳየት ነው፡፡
3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ
4) መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት
5) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡
6) ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡
7) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨
8) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨
9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡
❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡
❖ ሌላው “ብሑዕ” ማለት የቦካ ማለትን ሲያመላክት በዚኽ ቀን የሚጋገረውን ሙሉሙል ዳቦ የሚያመለከክት ነው፡፡
❖ በዚህ በዓል የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ነሐሴ 12 ማታ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡
❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና የዚያ ምሳሌ ነው፡፡
[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡
[መልካም በዓል]

#አቤቱ ህዝብህን አድን
843 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , edited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 03:45:49 የእመቤታችን ተምሳሌት እና ስሞች #ከመጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ብቻ

1.የማክሰኞ እርሻ -ዘፍ 1:10-13
2.|የኖህ መርከብ-ዘፍ 7:2-23,ኩፍ 6:28
3.የኖህ እርግብ-ዘፍ 8:6
4.የኖህ ቀስተ ደመና -ዘፍ 9:8-15
5.የሴም ድንኳን - ዘፍ 9:27
6.የአብርሃም ድንኳን -ዘፍ 18:1-15
7.የአብርሃም እፀሳቤቅ - ዘፍ 22:9
8.የአብርሃም እርሻ -ዘፍ 23:17-20
9.የያዕቆብ መሠላል - ዘፍ 28:10-12
10.የሙሴ ሐመልማል - ዘፀ3:1-5
11.የሲና ተራራ -ዘፀ31:18
12.የሙሴ ታቦት -ዘፀ 32:1-2
13.የአሮን በትር -ዘሁ 17:1-8
14.የኢያሱ ሐውልት -ኢያ 24:25
15.የጌዲዎን ፀምር -መሣ 6:36-40
16.የሳሙኤል የሽቶ ቀንድ -1ኛ ሳሙ 16:13
17.የዳዊት መሠንቆ -1ኛ ሳሙ 16:14-23
18.የአሚናዳብ ሠረገላ - 2ኛሳሙ6:3-4
19.የኤልያስ ደመና -1ኛነገ15:41-46
20.የኤልሳዕ ማሠሮ - 2ኛነገ2:19-22
21.የኤልያስ መሶበወርቅ -1ኛነገ19:1-8
22.የሰሎሞን አክሊል - መኃ3:11
23.የሙሴ ደመና - ዘሁ16:41-50
24.ኢየሩሳሌማዊት ፅዮን - ኢሳ 2:3, መዝ 131:13
25.የእሴይ በትር - ኢሳ 11:1
26.የአቤል ደግነት - ዘፍ4:2
27.የኢሳያስ ደመና - ኢሳ 19:1
28.ኤዶምያስ - ኢሳ 63:1
30.የፍራን ተራራ - ዕን3:3
31.የዳዊት መስክ - መዝ 72:2
32.ሴት - ዘፍ3:15,ዮሐ2:2,ዮሐ19:25
33.ድንግል - ኢሳ 7:14
34.የኢየሱስ እናት - ዮሐ 2:2,ዮሐ19:25
35.ማርያም - ማቴ1:18
36.የጌታየ እናት/ እመቤቴ/ - ሉቃ 1:43
37.የጌታ ዙፋን - ኢሳ6:1
38.የወርቅ መሶቦወርቅ -ዕብ9:4
39.የእግዚአብሔር ከተማ - መዝ86:1,ኢሳ60:14
40.ሙሽራ - መዝ18:5
41.የክርስቲያኖች እናት -ዮሐ 19:25
ስለ እመቤታችን በጣም በጥቂቱ ይህችን አልኳቹ እናንተ ደሞ አስፍታችሁ እዩት

ማሳሰቢያ
በጸሎት የተጀመረ ቀን ብሩህ ነውና የጸሎት መንፈስ ይኑረን
መልካም ቀን

@eotcy
@eotcy
@eotcy
537 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , edited  00:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 03:44:50
478 viewsᵇᵉⁿᵒⁿ 🅸🅽 , 00:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:23:13

በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል.. ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት...፡፡

አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣ አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣ ወይንም አምስት መቶ ብር መክፈል...፡፡ ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ «ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው...፡፡

ቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት...፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፡፡ አልቻለም ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና፡፡ «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ
እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡

«እህሳ» አሉት ዳኛው «አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡

«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር
የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።



"አስቦ የሚራመድ ብዙ ርቀት ይጓዛል" ይላሉ አበው።
ክርስቲያን መንገዱን ሙሉ አስቦ ነው ሚራመደው አስቸዋይ እንሁን

" ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤ "
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:13)

" ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 21:16)


@eotcy @eotcy @eotcy
@eotcy @eotcy @eotcy
@eotcy @eotcy @eotcy
90 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, edited  19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:55:57 + ይህ ሕፃን ምን ይሆን? +

በመጥምቁ ዮሐንስ ልደት ዙሪያ ለአንድ መንፈሳዊ መጽሔት የሚሆን ጽሑፍ በአስቸኳይ እንዳዘጋጅ አንድ ወዳጄ ጠየቀኝ፡፡ ‘አደራ ያልታተመ አዲስ ጽሑፍ’ የሚል ማሳሰቢያም አከለበት፡፡ በመጥምቁ ዙሪያ በርከት ያሉ ጽሑፎች ቢኖሩኝም ሁሉም ወይ በመጽሔት ወይ በኢሚዲያ የታተሙ ናቸው፡፡ አዲስ ጽሑፍ ለመጻፍ ደግሞ የነበርኩበት ውጥረትና ጻፍ ጻፍ የሚል ውስጣዊ ግፊት ስላጣሁ ልጽፍ ‘ዮሐንስ’ የሚል የጽሑፍ ፋይል ከፍቼ ጀምሬ መንፈሳዊ ነገር በትግል አይሆንምና ተውሁት፡፡ በዓሉም ካለፈ ወዳጄም ካኮረፈ በኋላ ግን ‘ዮሐንስ...’ ብቻ ብዬ የተውኩትን ፋይል ዛሬ ስከፍተው አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ተደመምኩ፡፡

ስለ ዮሐንስ ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፈለት ማን ነው? የመጥምቁ ዮሐንስ ነገር በአራቱም ወንጌላት ተብራርቶ ሳይጻፍ በፊት ፣ በገድለ ዮሐንስ መጥምቅ ሳይዘረዘር በፊት ፣ ማሕሌት ሳይቆምለት ፣ ቅኔ ሳይዘረፍለት በፊት ስለ ዮሐንስ ለመጀመሪያ ጊዜ መጻፍ የተጀመረው መቼ ነበር? ስለ መጥምቁ ብዕሩን ያነሣው የመጀመሪያው ጸሐፊስ ማን ነበር? ምን ብሎስ ስለ እርሱ ጻፈ? የሚለውን አስታወስሁ፡፡

ስለ መጥምቁ ዮሐንስ የተጻፈው የመጀመሪያው ጽሑፍ በብራና ነበረ፡፡ ጸሐፊው ደግሞ አባቱ ዘካርያስ ነበር፦
‘ብራናም ለምኖ። ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ፡፡ ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤ የሰሙትም ሁሉ። እንኪያ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት’ ሉቃ. 1፡63

ጎረቤቶቹ ‘ይህ ሕፃን ምን ይሆን?’ አሉ፡፡ እውነታቸውን ነው ፤ ገና በተወለደ በስምንት ቀኑ ገድሉ በብራና መጻፍ የተጀመረለት ሕፃን እንደምን ያለ ነው? አፉን ሳይፈታ በእግሩ መሔድ ሳይጀምር ብራና የሚለመንለት ሕፃን እንደምን ያለ ነው? ነገሩን አልኩ እንጂ ዮሐንስ ገና ከማሕፀን ሳይወጣ ስግደት የጀመረ መናኝ ፣ የድንግል ማርያምን ድምፅ ከሌላ ሰው ድምፅ ለይቶ ሰላምታዋን ሲሰማ የሚዘል ሕፃን ነበርና የሱ ነገር ከሥር ከሥር ካልተጻፈ አይዘለቅም፡፡

አባቱ ስለ ዮሐንስ ብዙ አልጻፈም፡፡ ‘ስሙ ዮሐንስ ነው’ ብቻ ብሎ አበቃ፡፡ መጥምቁን ለማክበር ‘የእግዚአብሔር ጸጋ የእግዚአብሔር ሥጦታ’’ ብሎ ከመጥራት በላይ ምን ውዳሴ ሊቀርብ ይችላል፡፡ እርሱ ዮሐንስ ነው፡፡

ዘካርያስ የልጁን ስም በብራና ላይ ሲጽፍ የተዘጋ ‘አፉ ተከፈተ መላሱ ተፈታ’ ስሙን ብቻ ጽፎ የተዘጋ አፉ ከተከፈተ ጨምሮ ቢጽፍ ምን ይከፈትለት ይሆን? ‘የሚጮህ ሰው ድምፅ ነኝ’ ያለው ዮሐንስ ስሙ በመጻፉ ብቻ ለአባቱ ድምፅ ሠጠው፡፡ ዘካርያስ ስሙን ጽፎ እንዲህ አንደበቱ ከተከፈተ የዮሐንስን ገድሉን መልኩን የጻፉ ምስጋናውን የደረሱ ሰዎች ምን ይከፈትላቸው ይሆን?

መጥምቁ ዮሐንስ ሆይ ስለ አንተ ከፍቅር በቀር ምንም እውቀት የለኝም:: ምንም ቅኔ ምንም ምስጋና ባልጽፍልህ እንደ አባትህ ዘካርያስ ስምህን ብቻ መጻፌን አይተህ እዘንልኝ፡፡ አንደበቴ ባይዘጋም የተዘጋው ልቤን ክፈትልኝ ፤ ምላሴ ባይታሰርም በኃጢአት የታሰረች ነፍሴን ፍታልኝ፡፡ ለጌታ መንገድ የጠረግህ አንተ ለነፍሴ መንገድዋን ጥረግላት፡፡

በንስሓ ጥምቀትህ እጠበኝ ፤ ግራና ቀኝ እንዳላይ እነሆ ብለህ ኃጢአትን ወደሚያስወግደው ወደ እግዚአብሔር በግ አመልክተኝ ፤ በሔሮድያዳ ልጅ ትርዒት የታወረውን የልቤን ሔሮድስ እንደልማድህ ገሥጽልኝ፡፡

አንተ ለአባትህ ያደረግከውን አድርግልኝ እንጂ ፤ አንተ የተዘጉ ነገሮቼን ሁሉ ክፈትልኝ እንጂ ስምህን ደግሜ ደግሜ እጽፈዋለሁ፡፡ ዮሐንስ ዮሐንስ ዮሐንስ ዮሐንስ ዮሐንስ !

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/eotcy
807 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, 09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:15:02 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
የጌታችንን መንገድ የጠረገ
ጌታውን ያጠመቀና
ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::

ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

አባ ጌራን ሕንዳዊ

ዳግመኛ በዚህች ቀን ሕንድ ካፈራቻቸው ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አባ ጌራን ይታሰባሉ:: የእኒህ ቅዱስ ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ቅዱሱ በሕንድ ተወልደው: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድገው: ገና በወጣትነታቸው መንነው: ደሴት ውስጥ ወደሚገኝ አንድ በርሃ ገብተዋል:: ከገድላቸው ጽናት: ከቅድስናቸውም ብዛት የተነሳ በሃገረ ሕንድ ሰይጣን እንዳይገባ: ጠብ ክርክር እንዲጠፋ: ሰው ሁሉ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ማድረግ ችለው በጣም ተወዳጅ ነበሩ::

በዚህ የተበሳጨ ሰይጣን ግን ባልጠረጠሩት መንገድ መጣባቸው:: አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው መጥታ (የንጉሡ ልጅ ነኝ በሚል) አስጠግተዋት ነበር:: አንድ ሌሊት ላይ ግን አውሬ ያባረራት በመምሰል ሩጣ ወደ ቤታቸው ገብታ አቀፈቻቸው:: በዚያ ቅጽበት ፍጡር ደካማ ነውና ታላቁ አባ ጌራን ተሰነካከሉ:: ከአፍታ በሁዋላ የሆነውን ሲያውቁ ደም አለቀሱ::

ልብሳቸውን ቀደው: እንባቸው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አለቀሱ:: ራሳቸውን በትልቅ ድንጋይ እየቀጠቀጡት የጭንቅላታቸውና የደረታቸው አጥንቶች ተሰባበሩ:: እርሱ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይቅር ብሎ: የቅድስና ስም ሰጥቶ በዚሕች ቀን ወደ ገነት አሳርጉዋቸዋል:: ለዚህ ነው መጽሐፉ "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: ይነሣማል" ያለው:: (ምሳ. 24:16)

አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ አባ ጌራን በረከት ይክፈለን::

ሰኔ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ)
2.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ)
3.አባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ)
4.ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች)

ወርኀዊ በዓላት @eotcy

1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
@eotcy
ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው::(ሉቃ. 1:76)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@eotcy
315 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, edited  03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:14:58
240 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, 03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:43:52 እርግጠኛ ነሽ ግን ፀንሰሻል?!

ዝኆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ይፀንሳሉ ፡፡ ከ3 ወራቶች በኋላ ውሻዋ ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝኆኗ እንጸነሰች ከስድስት ወራት በኋላም ውሻዋ በድጋሚ ፀነሰችና ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡

. . . በ18ኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝኆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ÷ “እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ?! አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነን ነበር ፥ እኔ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ ። አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልልቅ ውሾች ሆነዋል : ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ የጤና ነው?"
@eotcy
ዝኆኗም መለሰች “ልታውቂው የሚያስፈልግሽ አንድ ነገር ÷ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝኆን ነውና በ2 ዓመት ውስጥ አንድ ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ አይደለም! ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፤ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል። የእኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ሁሉ የሚስብ ኃያል ነው።" ስትል፡፡
@eotcy
አንዳንዶች ምድራዊ በረከቶችን በመመልከት ታላላቅ ዋጋ የሚያሰጡን የበጎ ምግባራትና ትሩፋት ዋጋዎችን የምንቀበልበት ጊዜ ÷ በብዙ መቃተት የተሸከምናቸው ፈተናዎቻችንንም የምንገላገልበት ቀን ይዘገይብናል ÷ የፀሎት ልመናችን መልስ ይርቀናል ። ነገር ግን ፈጣሪያችን ቢዘገይ የሚቀድመው የሌለ ÷ የጊዜያት ቀመር ስንኳ ለእርሱ ውብ ሥራ ገደብ የሚሆኑበት አይደለምና በሚታይ አገልግሎት ውስጥ የማይታዩ መንፈሳዊ ጸጋዎችን ተስፋ ማድረግን ለዘወትር አንርሳ! ያን ጊዜ ያለ ማንጎራጎር በማመስገን እንኖራለን። ደሃውና ምስኪኑ አልአዛር ስለ ድኅነቱ ቢመረር እንኳ ባለማማረሩ በአብርሃም እቅፍ እንደገባ እግዚአብሔር የሁላችንን ዋጋ አይረሳምና!

'በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር እኩል ናቸው!'

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@eotcy
278 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:32:20 #ካልባረከኝ_አለቅህም

ከመጽሐፍ ቅዱስ ቅምሻ
@eotcy

ዘፍጥረት 32፥26

#እንዲህም አለው፡— ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። #እርሱም፡— ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም፡ አለው።
@eotcy
ያዕቆብም ወደ እናትና አባቱ ምድር ሲመለስ ላሞችንም አህዮችንም በጎችን ወንዶች ባሪያዎችንም ሴቶች ባሪያዎችንም ሚስቶችና ልጆችን ሁሉ ይዞ ተመለሰ ግን ዔሳው እንዳይገድለው ፈራ።
ያዕቆብም እጅግ ፈርቶ ተጨነቀ፤ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች መንጎችንም ላሞችንም ግመሎችንም በሁለት ወገን ከፈላቸው፤
#እንዲህም አለ፡— ዔሳው መጥቶ አንዱን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀረው ወገን ያመልጣል።
በዚያች ሌሊትም ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ባሪያዎቹን አሥራ አንዱንም ልጆቹን ወስዶ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
ያዕቆብ ኑሮው ሀብቱና ብቸኝነቱ ተቀይሯል እንጂ ማንነቱና ስሙ አልተለወጠም ነበር።
ያዕቆብም ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።
እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤
#እንዲህም አለው፡— ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። #እርሱም፡— #ካልባረክኸኝ_አልለቅቅህም፡ አለው። አይገርምም ይህን ሁሉ ሀብትና ሰው ሰጥቶት አሁንም በረከትን ይፈልጋል ምክንያቱም አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲሱ አቁማዳ ነው።
#እንዲህም_አለው፡— ስምህ ማን ነው? እርሱም፡— ያዕቆብ ነኝ፡ አለው።
#አለውም፡— #ከእንግዲህ_ወዲህ_ስምህ_እስራኤል_ይባል_እንጂ_ያዕቆብ_አይባል_ከእግዚአብሔር_ከሰው_ጋር_ታግለህ_አሸንፈሃልና።ብሎ በዚያም ስፍራ ባረከው።
#ያዕቆብም፡— እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች አለ ይህን ሲል ያዕቆብ እያነከሰ ነበር ታዲያ እያነከሰ እንዴት ሰውነቴ ድና ቀረች ይላል?
ያዕቆብ በመነካቱ የተለወጠው ድሮ ሲወጣ የነበረው አጭበርባሪው ማንነቱ ሲሆን ፤ ሌላው ደግሞ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቶ በህይወት የሚኖር የለምና እኔ ግን ድኛለው አለ። ወንዙን ባለፀጋ በመሆን ብቻ ሳይሆን እስራኤል ተብሎ የተመረጠ የእግዚአብሔር ህዝብ አባት ሊሆን ተሻገረ። ዔሳውም ጋር በሰላም ተገናኘ ምክንያቱም አሁን የትናንቱ ያዕቆብ አይደለም።
እኛም አመታትን ስናስቆጥር በቁስ ብቻ መለወጥ ሳይሆን የትናንቱ ጉድፍ ማንነት ከኛ ላይ እንዲወድቅና ስማችንን እንዲቀይር አዲስን ማንነት እንዲሰጠን ሁሉን ቻይ ነውና እግሮቹ ስር ወድቀን ካልባረከን አንለቅህም እንበለው።
@eotcy
360 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, edited  04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:32:17
298 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ