2022-07-01 20:44:17
*********************
#የወር_አበባ በድጋሚ የተለቀቀ
በውስጥ መስመር በተደጋጋሚ የመጡ ጥያቄዎች
ለህቶቻቻችን ይዳረስ ዘንድ ያጋሩልን
#በወር_አበባ_ጊዜ_መስቀል_መሳለም_መጽሐ_ቅዱስ_እና_ሌሎች_ጸሎት_መጽሀፍትን_ማንበብ_ይቻላል
እንዲሁም ወደ ቤተክርስትያን መሄድ ይቻላል የወር አበባ በሴቶች ላይ በየወሩ የሚታይ የደም መፍሰስ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን
አስተምህሮ “
ደመ ጽጌ፣ አበባ ደም” በመባል ይጠራል፡፡አሰያየሙም የወንድ ዘር
ካላገኘ ከማህጸን ግድግዳ ፍራሽ ጋር በደም መልክ ስለሚፈስና የኋለኛው
ማንነቱ ደምነት ስለሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት አገልግሎቱን የጨረሰ፣
ያረጀ፣ ቆሻሻማለት ነው፡፡ ይህ በየወሩ ዑደትን ተከትሎ የሚሄደው የዘር ፍሳሽ በስነ ህይወት
ትምህርት ኦቫሪ (ከዘር ከረጢት) የሚለቀቅ የወንድ ዘር ካላገኘ ኦቫ (ሴቴ ዘር)
ጋር እየተቀላቀለ የሚወርድ ነው፡፡
የወር አበባ #በቤተክርስቲያን አስተምህሮ በሁለት ከፍለን ነው መመልከት ያለብን፤
በዘመነ ኦሪትና ዘመነ ሐዲስ ኪዳን በማለት፡፡
በርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ ለዚህም
ማስረጃነት በመጽሃፍ ቅዱስ
ዘሌ 18÷19፣ 20÷18 ያሉ ጥቅሶች “በመርገምዋ
ርኩሰት ሳለች” እና “#ባለ_መርገም_ሴት” በማለት ሲገልጸው፤ ባንጻሩ ደግሞ
ከወር አበባዋ ነጻ የሆነችውን ሴት “#ከርኩሰትዋ_ነጽታ” በማለት የወር አበባ
የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑን ይጠቁማል፡፡
በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑ ቀርቷል፡፡
ርኩሰት አይደለም፤ ርኩስም አያሰኝም፡፡ በብሉይ ኪዳን አዳምና ሄዋን በገነት
በነበሩ ጊዜ ዕጸ በለስን በልተው #እግዚአብሔርን በደሉ፤ እግዚአብሔርም ሄዋንን
ደመ ዕጸ በለስን አፍስሰሻልና “ወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕጽ ከማሁ
ድምዊ ለለወርኁ፡፡” በማለት ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ፈረደባት፡፡ ስለዚህ
የሄዋን ደም መፍሰስ መነሻው መርገም ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈጸመው #ቤዛነት መርገምነቱና ርኩስነቱ
ተወግዷል፡፡
የወር አበባ በዚህ ዘመን ርኩሰት ወይም መርገም ባይሆንም
እድፍ (ቆሻሻ) ነው፡፡
እድፍና ርኩሰት ልዩነት አላቸው፡፡
ርኩሰት ውስጣዊ ነው፤ በንስሃ እንጂ በውሃ አይጠራም፡፡ እድፍ ደግሞ ግዘፍ
አካል ያለው፣ የሚታይና ውሃ የሚያነጻው ነው፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህሪ ሳለ
እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም፣ ከሰውነት ሲወገድ ግን ይቆጠራል፡፡ ይህንን
ለማስረዳት ምሳሌ መሆን ከሚችሉት ውስጥ ዛህል (ንፍጥ)፣ ሽንት፣ ምራቅ፣
ዓይነምድርና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡
#ያስተውሉ
ወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ቤተክርስቲያን ከመሔድ፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን
ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡
ነገር ግን ከሩካቤ፣ ከመጠመቅ፣ ከመቁረብና ቤተ መቅደስ ከመግባት ይከለክላል፡፡
#ከሩካቤ :-
ሩካቤ በወር አበባ ጊዜ ከሚከለከሉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ በወር አበባ ጊዜ
የሚደረግ ግንኙነት የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀር ለአባላዘር፣ ለልዩ ልዩ
በሽታዎችና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እንደሚችል በመናገር እንዳይፈጸም
ይመክራሉ፡፡
በመንፈሳዊው አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር #ቅዱስ በሆነው #በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ፣ ይህንን የተከበረ ዘር፣ እዳሪ
ወይም ቆሻሻ ከሆነ ደም ጋር ማዋሃድ ኃጢያት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
#በመጽሐፍ_ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ እንዳለች የሚፈጸምን ሩካቤ
“
እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ እርሷ
አትቅረብ” ዘሌ 18÷19፣ ዘሌ 20÷18።በዚህም ምክንያት በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በኦሪትም ይሁን በአዲስ
ኪዳን ክልክል ነው፡፡
#
ከመጠመቅ:-
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ “
ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ
አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር በጎ
ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1ኛ ጴጥ 3÷21 በማለት ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ጥምቀት
ሥጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ፣ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው እንጂ ከእድፍ
ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ የወር አበባም ከላይ
እንደተመለከተው ከሰውነት ሲወጣ እድፍ (ቆሻሻ) በመሆኑ፣ ከዚህ #የቤተክርስቲያን ስርዓት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
#ቤተመቅደስ_መግባት ፡-
ሴት በወር አበባዋ ጊዜ የምትከለከለው ነገር #ቤተመቅደስ መግባትን ነው፡፡ይህም
የሆነው በርኩሰት ምክንያት ወይም በኦሪት ሕግ ምክንያት ሳይሆን #በቤተመቅደስ_መፍሰስ ያለበት_ደም_አማናዊ_የሆነውየክርስቶስ_ደም_ብቻ_በመሆኑነው
ይህ ስርዓት #ለሴቶች #ብቻ ሳይሆን #ለወንዶችም ነው፡፡
#አንድ_ወንድ_እየነሰረው_ወይም_የሆነ_ነገር_አካሉን_ቆርጦት_ደም_እየፈሰሰው_ከሆነ_ወደ_ቤተ_መቅደስ_መግባት_የለበትም
ዝንየት (ህልመ ለሊት) ቢያጋጥመው ከ፩ቀን ከቤተ መቅደስ መራቅ
#ምክንያቱም በቤተ መቅደስ ከ #ክርስቶስ ደም ውጪ ሌላ ነገር መፍሰስ ስለሌለበት ነው፡፡
አስተውሉ
**በወር አበባ ላይ ሳለች ሴት #ወደ_ቤተመቅደስ_አትግባ_ማለትቤተ_ክርስቲያን_አትሂድ_ማለት_ሳይሆን_ወደ_ቤተክርስቲያን_ሄዳ_የመጀመሪያውን_ቅጽር ( #አጥር ) #ከገባች_በኋላ_በመጠለያ_ውስጥ_በመሆን_ትጸልይ_ትማር ወይም ማንኛውንም
አይነት መንፈሳዊ ስራዎችን ሰርታ ትመለስ ማለት ነው፡፡
#ከመቁረብ፡-
ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ #ሥጋ_ወደሙ መቀበል አይችሉም፡፡
ይህንን ስርዓት ተላልፈው ወደ ሥጋ ወደሙ እንዲቀርቡ ያደረገ ዲያቆንም ይሁን ቄስ ከክህነቱእንዲሻር #ፍትሕ_ነገስት ይደነግጋል፡፡ “ከግዳጅዋ ያልነጻችውን ሴት በደሟ ወራት
#ከቤተ_ክርስቲያን_አግብቶ_ሥጋውን_ደሙን_ያቀበለ_ከክህነቱይሻር፡፡” ፍትነገ 6፣
ዘሌ 7፡19
#
ይህ_ሥርዓት_በሴቶች_ላይ_ብቻ_ሳይሆን_ወንዶችም_ህልመ_ለሊት
በሚያጋጥማቸው ሰዓት እንዳይገቡ ይከለከላል፡፡ቤተ ክርስቲያን የገነት ምሳሌ ናት፡፡ ሔዋን ከአዳም ጋር በገነት ለሰባት ዓመታት
ስትኖር የወር አበባ አታይም ነበር፡፡ ቤተ መቅደስ የገነት ምሳሌ መሆኗ የተሟላ
እንዲሆን የወር አበባ የምታይ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትገባም፡፡
........የተወደደችው ሰዓት አሁን ነው ፤ የሐዳን ቀን አሁን ነው
1ኛ ቆሮ 6÷2
ይህን የእናት ቤተክርስቲያን ትምህርት ለሌሎቹም እህቶቻችን ሼር በማድረግ
እናካፍላቸው፡፡
@eotcy
@eotcy
@eotcy
531 views𝔟𝔢𝔫𝔬𝔫 𝙗𝙚𝙣𝙖, edited 17:44