Get Mystery Box with random crypto!

ንጉስ ሰሎሞን እና ጉንዳኗ ንጉስ ሰሎሞን ለተፈጥሮ ባለው ፍቅር ይታወቃል እርሱ በየጊዜው በአትክል | ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

ንጉስ ሰሎሞን እና ጉንዳኗ

ንጉስ ሰሎሞን ለተፈጥሮ ባለው ፍቅር ይታወቃል እርሱ በየጊዜው በአትክልት ስፍራዎቹ በወንዝ ዳርቻዎችና በተራራዎች ላይ ይዘዋወር ነበር።

እርሱ እንስሳትን ወፎችን ዓሳዎችንና ነፍሳትን በፍላጎት በመመልከትና በደመ ነፍሳቸው ውስጥ የተገለጠውን የጥበባቸውን ጠባይ በማየት እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን እንክብካቤ ያረጋግጥ ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ትኩረቱ በአንዲት ትንሽ ጉንዳን ላይ ያርፋል። ጉንዳጊቱ ከእርሷ ክብደት ብዙ እጥፍ የሚበልጠውን የጥሬ ግማሽ ተሸክማ እየሄደች ነበር። ጉንዳኗ ይህን የጥሬ ስባሪ ተሸክማ የምትጓዘው በጉንድጓዷ ውስጥ ለማከማቸት ነበር።
@eotcy
በዚህ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ስለተደነቀ ይህቺን ጉንዳን ለምንድን ነው የማላስደስታት ይላል። እርሱ ይህን ያለው ያላትን ጉልበት ሁሉ ከዚህ የጥሬ ድቃቂ ላይ ስታጠፋ ስለተመለከተ ነበር።
"እግዚአብሔር ይህን ያህል ታላቅ ሃብት ለእኔ የሰጠኝ ደስታን ለህዝቤ ብቻ እንድሰጥ ሳይሆን ለእንስሳትም ለወፎችም ለነፍሳት ጭምር እንድሰጥ ነው።
@eotcy
ንጉሡ ይህን ብሎ ጉንዳኒቱን ካነሳ በኋላ ውስጡ እጅግ ለስላሳ በሆነ ሐር የተነጠፈ የወርቅ ሳጥን ውስጥ ያስቀምጣታል። ከእርሷ ጋር በወርቅ ሳጥኑ ውስጥ አንድ የስንዴ ቅንጣት ካስቀመጠላት በኋላ ከፈገግታ ጋር በየዕለቱ ምንም ሳትደክሚ የምትበይውን የስንዴ ቅንጣት ስለምሰጥሽ ከእንግዲህ በኃላ አትደክሚም በጎተራዬ ውስጥ የተትረፈረፈው ጥሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እንስሳትን ወፎችንና ነፍሳትን የሚመግብ ነው አላት።

ንጉሡ እንዲህ ያለውን መልካም እንክብካቤ ለእርሷ ስላደረገላት ጉንዳኒቱ ታመሰግለዋለች።
@eotcy
በሚቀጥለው ቀን ንጉሡ ወደ ጉንዳኒቱ ተመልሶ ሲመጣ የተመገበችውን የአንዱን ቅንጣት ስንዴ ግማሽ እንደሆነ ሲመለከት እጅግ ይደነቃል። ሌላ አንድ የስንዴ ቅንጣት አስቀምጦላት በሚቀጥለው ቀን ተመልሶ ሲመጣ ጉንዳኗ ግማሹን ቅንጣት ተመግባ ግማሹን እንዳስቀመጠች ይመለከታል።

ይህ ሁኔታ እየተደጋገመ መሄዱን የተመለከተው ንጉሥ ሰሎሞን ጉንዳኗን ለምንድን ነው ሁል ጊዜ የአንዱን ቅንጣት ስንዴ ግማሽ የምታስቀልጭው? በማለት ይጠይቃታል።
@eotcy
ጉንዳኒቱም እንዲህ በማለት መለሰችለት እኔ በየዕለቱ የስንዴውን ግማሽ የማስቀምጠው ለመጠባበቂያ ነው አንተ ለእኔ ምን ያህል እንክብካቤ እንዳደረክልኝና በጎተራዎችህ ውስጥ ምን ያህል የበዛ ጥሬ እንዳለህ አውቃለሁ ይሁን እንጂ አንተ ሰው ስለሆንክ በየዕለቱ የምትከውነው የስራህ ብዛት እኔን እንድትረሳኝ ያደርገሃል ይሄ በሚሆንበት ጊዜ ያስቀመጥኳትን የስንደ ቅንጣት ከረሃብ ትታደግልኛለች ምግቤን በድካሜ እንዳገኝ የተወኝ እግዚአብሔር አይረሳኝም አንተ ግን ልትረሳኝ ትችላለህ።

በዚህ ጊዜ ንጉሡ ጉንዳኗን ወደ ቀደመ ሕይወቷ ተመልሳ ኑሮዋን እንዴትቀጥል ይለቃታል
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያስቀመጠውን ነገር ለእርሷ እንደሰጣት ተገንዝቧልና።

ፈጥሮ የማይጥል ወዶ የማይጠላ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ክርስቲያኖች ሰው እንደተሰባሪ ብርጭቆ ነው።
እግዚአብሔርን የተመረኮዘ አይወድቅም።

.......የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነው
-2ኛ ቆሮ6÷2

@eotcy
@eotcy
@eotcy