Get Mystery Box with random crypto!

ደጉ ሳምራዊ ደጉ ሳምራዊ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ሳምራዊ ማለት ሀገር ጠባቂ ማለት ነው | ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

ደጉ ሳምራዊ

ደጉ ሳምራዊ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ሳምራዊ ማለት ሀገር ጠባቂ ማለት ነው ኢየሱስ ክርስቶስም እረኛችን ጠባቂያችን ነው፤ ዮሐ 10፥11 1ኛ ጴጥ 2፥24
ሀገር ጠባቂ ሀገርን የሚጠብቀው ራሱን አሳልፎ በመስጠት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስም እኛን በነፍስም በስጋም የጠበቀን ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ሰጥቶ ነው፤ ደጉ ሳምራዊ ቁስለኛውን በሩቅ አይቶ አዘነለት፣ ቀርቦም በቁስሉ ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰለት

ወይኑ የቊስሉን ደም እንድያቆምለት እንዲያደርቅለት ነው።
ቊስል ቶሎ የሚደርቀው ከላይ ነው፤ ወዲያውኑ እየተሰነጣጠቀ ያሰቃያል፤ ለዚህም መከላከለያ እንዲያለሰልስለት ዘይቱን አፍስሶለታል።
ጌታችንም በሩቅ ማለትም በሰማይ መንበሩ ተቀምጦ ቊስለኛውን አዳም በዓይኑ ምሕረት አየው ገጸ ምሕረቱን መለሰለት ቀረበውም ባሕርዩን ባሕርይ አደረገ
የባሕርዩ መመኪያ ከሆነች ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ተዋሕዶ ሰው ሆኖ ተወለደ።
ወይን እንደማፍሰስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰለት ደሙን አፈሰሰለት። ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ወይኑን በጽዋ አድርጎ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈውስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው ያለው ለዚህ ነው። ማቴ 26፥27

እንደ ዘይት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሰጥቶታል። ይኽንን በተመለከተ
ቅዱስ ዳዊት ወይን የክርስቶስ ደሙ የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፤ ዘይትም ፊትን ያበራል መንፈስ ቅዱስ ሰውን ብሩኅ መልአክ ያስመስለዋል እህልም የክርስቶስ ስንዴ ሥጋው) የሰውን ጉልበት (ነፍሱን) ያጠነክረዋል። ብሏል
መዝ 103፥15

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም
እናንተ ከቅዱሱ ተቀብላችኋልና ሁሉንም ታውቃላችሁ፡፡ ያለው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ነው፡፡
ደጉ ሳምራዊ ከአህያው ወረደ ቊስለኛውን ማስቀመጡ የሚያመለክተው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መንበሩ መውረዱንና አዳምን በሰማይ መንበሩ ማስቀመጡን ነው።

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ
#በኢየሱስ_ክርስቶስ በሰማያዊ ሥፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ያለው ይኽንን ምስጢር ይዞ ነው። ኤፌ 2፥7
ምክንያቱም በተዋሕዶ አምላክ የሆነ ሥጋ በሰማይ የእሳት መንበር ተቀምጧልና።

#ደጉ_ሳምራዊ
ያከመውን ቊስለኛ ለእንግዶች ቤት ጠባቂ ማስረከቡ
ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት ያከማቸውን ምዕመናን ለመምህራን የማስረከቡ ምሳሌ ነው።

#ቅዱስ_ጴጥሮስን
ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጎቼን አሠማራ ያለው ለዚህ ነው። ዮሐ 21፥15።

ሁለት ዲኖሮች ደግሞ የሁለቱ ማለትም የብሉይና ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ምሳሌ ናቸው።

የሰው ሕይወቱ የሚጠበቀው በእነዚህ ነውና።

በሁለት ዲናር የተመሠሉ ቅዱሳን መጻሕፍት ምግበ ነፍስ ናቸውና። ቅዱስ ዳዊትም "ቃልህ ለጉሮሮየ ጣፋጭ ነው ከማር ይልቅ ጣፈጠኝ። ብሏል መዝ 118፥103

ደጉ ሳምራዊ የእንግዳ ቤት ጠባቂውን ከሁለት ዲናር በላይ ብታወጣ እኔ በተመለስኩ ጊዜ እከፍልሃለሁ አለው እንጂ ዋጋ የለህም አላለውም።

ይህ የሚያመለክተው መምህራን የተሰጣቸውን ሁለት ዲናር
ብሉይ ኪዳንን እና
ሐዲስ ኪዳንን ይዘው የምዕመናንን ሕይወት ለመጠበቅ ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትን ቢጽፉ ጌታ ሲመጣ የድካማቸውን ዋጋ እንደሚከፍላቸው ነው።)
@eotcy
ቅዱሳት ሊቃውንት
መጽሐፍ ቅዱስን ለማብራራት ንባቡን በመተርጎም ምስጢሩን በማራቀቅ አያሌ መጻሕፍትን ጽፈዋል። እነዚህም አዋልድ መጻሕፍት ይባላሉ። የቅዱሳን መጻሕፍት ልጆች ማለት ነው። የገድል የድርሳን እና የተአምር መጻሕፍት ቊጥርም ከአዋልድ መጻሕፍት ነው። እነርሱም የእግዚአብሔር ሰዎች #የእግዚአብሔርን ቃል እንደት እንደፈጸሙ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚያሳይ ነው።))
@eotcy
መጻፍ ማጻፍም መስማት ማሰማትም ዋጋ አለው። እንዲህ በተሰጡን ሁለት ዲናሮች ሥራ እንድንሠራ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍት በመጻፍና በማጻፍ እንድንመክርና እንድንመሰክር የተሰጠንን አደራ እንድንጠብቅ በዚህ ዓለም ተዋርደን ምእመናን የሚከብሩበትን ግብር ይዘን እንድንገኝ የሚያዝን ልቦና እንዲሰጠን የምናቆስል ሳይሆን የቆሰሉትን የምናክም እንዲያደርገን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን!

የሚያሳርፈን የእግዚአብሔርን ቃል እንማማር.......
@eotcy