Get Mystery Box with random crypto!

. መ-ቁ-ጠ-ሪ-ያ +========+========+========+ መቁጠሪያ በመሠረቱ | ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

. መ-ቁ-ጠ-ሪ-ያ
+========+========+========+
መቁጠሪያ በመሠረቱ ቃሉ መ-ቁ-ጠ-ሪ-ያ ነዉ ራሱ ቃሉ።
አባቶቻችን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስን 41 ጊዜ፣
በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስን 41 ጊዜ፣
ኪርያላይሶን ክርስቶስ 41 ጊዜ፣
አምላኬ አምላኬ 41 ጊዜ
ስምዓነ አምላክ 41 ጊዜ፣
አድኅነነ ከመዓቱ ይሰዉረነ በምሕረቱ በእንተ ማርያም ወላዲቱ 41 ጊዜ ይቆጥሩበታል።

በሁለተኛ መቁጠሪያ መግረፊያም ጭምር ነዉ።
በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያናችን ከሚገኙና ሰይጣን ዲያብሎስን ከምንዋጋበት መሳሪያዎቻችን መካከል አንዱ መቁጠሪያ ነዉ።

በአንተ ጠላቶቻችን እንዋጋቸዋለን በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።
መዝ.፵፫ (፵፬)፥፭
መቁጠሪያ ለሰዉ ልጅ በጣም በጸሎት ጊዜያት ከሚያስፈልጉት ዉስጥ አንዱ ነዉ።

ምክንያቱም ከዛሬ መቶ ሃያ አመት በፊት የነበሩ አባቶች በመቁጠሪያ ጸሎት በመጸለይ ኃይለ አጋንንትን በመቀጥቀጥ ድል ያደርጉ፤ ሥጋቸዉንም ለነፍሳቸዉ ያስገዙ ነበር።

መናፍስት በሕይወታቸዉ ዉስጥ እንዳይገባ ትከሻቸዉን፣ ጀርባቸዉን፣ ማጅራታቸዉን፣ ራሳቸዉን፣ እግራቸዉን፣ ባታቸዉን፣ ሆዳቸዉን፣ ክንዳቸዉን፣ በመቁጠሪያዉ ይመቱታል። ራሳቸዉን የሚመቱት ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወት ግንዛቤ ስላላቸዉ ነዉ።

የሚመቱት ክፉ መናፍስት ጸሎቶቻቸዉን እንዳያስታጉል ድካም እንዳያመጣባቸዉ እግራቸዉን እንዳይዝ ቁርጥማት እንዳይሆን የብርድ በሽታ እንዳይሆን ነርቭ እንዳይሆን ግንዛቤ ስላላቸዉ ነዉ።
አሁን ግን ይሄ መንፈሳዊ ዉጊያ ተረስቶ መቁጠሪያ ለቆራቢ ነዉ።

መቁጠሪያ ለምንኩስና የበቁ ሰዎች ነዉ እየተባለ ይገኛል። ይህ ፍጹም ስህተት ነዉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፱፥፳፯ ላይ ያለዉን ቃል እንመልከት።

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛለሁ።
@eotcy
እየጎሰምሁ ሲል እየተንቀጠቀጥኩ ማለቱ ግልጽ ነዉ። ስለዚህም መቁጠሪያን በመጠቀም ከዉስጥ ያደፈጠ ጠላት መያዝና ማቃጠል ከሰዉነታችንም እንዳይገባባ ማስጨነቅ እና ማባረር እንችላለን።
@eotcy