Get Mystery Box with random crypto!

ማህበረ ቅዱን ምን እየሰራ ነው #ከ80 ሺ በላይ አዲስ አማኒያን ! ደስ የሚል ነገር ስለሆነ | ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

ማህበረ ቅዱን ምን እየሰራ ነው

#ከ80 ሺ በላይ አዲስ አማኒያን !

ደስ የሚል ነገር ስለሆነ ላካፍላቹ

"ማህበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎቱ ከ80ሺ በላይ ኢ አማንያንን አስተምሮ በማጥመቅ የሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለ4,556 ካህናት፣ 2,494 ሰባክያነ ወንጌል እና በሐዋርያዊ ተልዕኮ ጉልህ ድርሻ ላላቸው 379 የጎሳ መሪዎች በተለያዩ ርዕሶች ከአንድ ሳምንት እስከ አንድ ወር ድረስ ቆይታ ያላቸው ስልጠናዎች ተሰጥቷል፡፡ ለዚህም ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፡፡

የሐዋርያዊ ተልእኮን ተደራሽ በማድረግ በጋሞ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ከፋ፣ ቤች ሸኮ፣ ሸካና ምእራብ፣ ወላይታ፣ ጌደዎና በሌሎች አኅጉረ ስብከቶች 80,317 አዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት እንዲፈጸምላቸው ተረድጓል፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎቱም 8,126,008.00 ብር ወጪ ተደርጓል ፡፡
@eotcy
ሐዋርያዊ ተልእኮ በስፋት በሚፈጸምባቸው አካባቢዎች ለአዳዲስ አማንያን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ 19 አብያተ ክርስቲያናት ተገንብተው አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደርጓል ፡፡

አራት አብያተ ክርስቲያናት ግንባታቸው ተጠናቆ በቅርብ የሚመረቁ እና አገልግሎት የሚጀምሩ ይሆናል፡፡
@eotcy
ሐዋርያዊ ተልእኮ በሚፈጸምባቸው አካባቢዎች በካህናት እጥረት ተዘግተው የነበሩ 55 አብያተ ክርስቲያናት በመቅጠር እንዲከፈቱና ለምእመናን አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ፡፡

ከአዳዲስ አማንያን ጥምቀትና ድኅረ ጥምቀት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ 9 የስብከት ኬላ አዳራሾች 1,200, 000 ብር ወጪ ተደርጓል ፡፡
2 የሲዳምኛ አልበም ፣ 2 የክስታንኛ መዝሙራት እና 2 እንግሊዝኛ የዝማሬ አልበም ተዘጋጅተዋል ፡፡

እንዲሁም የነገረ ሃይማኖት ትምህርት በከንባትኛ፣ በቤችኛ ፣ በጋምኛ ፣ በኮንሶኛና በማሌኛ ቋንቋዎች መዘጋጀታቸውን በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡"

@eotcy