Get Mystery Box with random crypto!

+ ብናምንስ + ፃድቁ ኢዮብን በመሰልነው + @eotcy ሰባት ወንዶች እንዲሁም ሦስት ሴቶች ልጆቹ | ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

+ ብናምንስ + ፃድቁ ኢዮብን በመሰልነው +
@eotcy

ሰባት ወንዶች እንዲሁም ሦስት ሴቶች ልጆቹን በቅጽበት ሲያጣ ፈጣሪውን ያላማረረ ጻድቁ ኢዮብን እስኪ ለአፍታ እናስበው፡፡ ልጆቻቸውን ያጡ ወይም የሚያጡ ብዙ ወላጆች ልጆቹ ከመሞታቸው በፊት የመጨረሻ ቃላቸውን የመስማት፣ እጆቻቸውን የማሻሸትና ጥልቅ በሆነ ቤተሰባዊ ፍቅር የመሳም፣ ከሞቱም በኋላ እንደ ሥርዓቱ ዓይኖቻቸውን የመክደን እና አስከሬናቸውን አጥቦ የመገነዝ እድል አላቸው። ጻድቁ ኢዮብ ግን ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እንኳን አላገኘም። ልጆቹ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ሲበሉና ሲጠጡ ድንገት ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ቤቱን ደርምሶ ስለ ገደላቸው እነርሱን ተንከባክቦ የማስታመም እድል አላገኘም። ነፍሳቸውም በወጣችበት ደቂቃ ዓይኖቻቸውን አልከደነም፡፡
@eotcy
የሞቱት ድንጋይ ተጭኗቸው ስለሆነና አስከሬናቸውን ለማውጣት በሚደረገው ቁፋሮ ወቅት አንዳንዶቹ ሕዋሳቶቻቸው በጣም ስለሚጎዱ ሙሉ አካላቸውን የመቅበሩ ነገር ያጠራጥራል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁሉ መከራዎች በአንድ ጊዜ ቢደራረቡበትም ጻድቁ ኢዮብ ግን ‹‹እግዚአብሔርን አልሰደበም፣ መላእክትን አልረገመም››። ይልቅ ወደ ምድር #ሰግዶ ‹‹እግዚአብሔር ሰጠ፣ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን›› ብሎ አምላኩን አመሰገነ።

ትንሣኤ ባልተሰበከበት፣ የሰው ተስፋ በቀጨጨበት፣ ሞት ጥላውን ባጠላበት በኦሪት ዘመን የነበረ ኢዮብ እነዚያን ሁሉ ልጆች በአንድ ጊዜ አጥቶ እንዲህ ካመሰገነ፣ ስለ ትንሣኤው የተማርንና "የሙታንን መነሣት ተስፉ እናደርጋለን" ብለን የምንጸልይ፣ የኢዮብን ሩብ ያህል እንኳን መከራ ያልደረሰብን እኛ የሐዲስ ኪዳን ምእመናን ምን ያህል አመስጋኞች ልንሆን በተገባን?

@eotcy