Get Mystery Box with random crypto!

ECWC/ኢኮሥኮ/

የቴሌግራም ቻናል አርማ ecwccom — ECWC/ኢኮሥኮ/ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ecwccom — ECWC/ኢኮሥኮ/
የሰርጥ አድራሻ: @ecwccom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.23K
የሰርጥ መግለጫ

Official ECWC Telegram Channal
.የኮርፖሬሽኑ ዜናዎች
.የጨረታና የሥራ ማስታወቂያዎች
. በየወሩ የሚታተመው የዜና መጽሄት
. ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮች
.በየ 6ወሩ የሚታተመው የኮርፖሬሽኑ ዕይታ መጽሄት እና የኮርፖሬሽኑ ፕሮፋይል በዚህ ገጽ ላይ በየጊዜው ይቀርባል፡፡

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-01 16:50:18
1.6K views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 16:49:50 ኮርፖሬሽኑ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ሠራተኞች በየዓመቱ እ.ኤ.አ አቆጣጠር ማርች 8 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች በታላቅ ድምቀት አከበሩ፡፡ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ ጊዜ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ”፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ112ኛ ጊዜ "ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት" በሚሉ መሪ ቃሎች ተከብሯል፡፡እንደ ኮርፖሬሽንም የኮርፖሬሽኑን የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጡማ ጀማልን ጨምሮ የኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች፣ የሥራ መሪዎች እና የሠራተኛ ማህበር በተገኙበት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ  በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡በዕለቱ ዕለቱን የተመለከቱ አስተማሪ እና አዝናኝ የጥበብ ሥራዎች፣ ፅሁፎች፣ ድራማ፣ ጥያቄና መልሶች ቀርበዋል፡፡በዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ታሪካዊ ዳራ፣ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የበዓሉ አከባበር ምን እንደሚመስል እና የሚከበርበት ምክንያት፣ የሴቶችን ጥቃት ለማስቆም ምን መደረግ እንዳለበት፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሴቶች እንቅስቃሴ፣ ተሳትፎና አበርክቶ ምን እንደሚመስል ፅሁፍ ተዘጋጅቶ በፅሁፉ ላይ ገለፃ ተደርጓል፡፡ፅሁፉን ያቀረቡት በኮርፖሬሽኑ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ መምሪያ ሊድ የሥርዓተ-ፆታ ባለሙያ ወ/ሪት ቤዛዬ ታደሰ በኢትዮጵያ ሴቶች ሀገርን በመምራት፣ የሀገር ህልውናን በማስጠበቅ፣ ለሰላም ዘብ በመቆም እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች በርካታ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች የተፈጠሩና እየተፈጠሩ ያሉ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡በአገር አቀፍ ደረጃ የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ እንዲሁም እየደረሱባቸው ያሉ ችግሮችን/ጥቃቶችን ለማስቀረት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የገለፁት ባለሙያዋ፣ እንደ ኮርፖሬሽንም በኮርፖሬሽኑ ሥር ጉዳዩን የሚከታተልና የሚያስፈፅም ራሱን የቻለ መምሪያ ተዋቅሮ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ ማሳያም ኮርፖሬሽኑ ለሴት ሠራተኞች ነፃ የትምህርት ዕድል፣ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን፣ የሙያ ሥልጠናዎችን እና የሥነ-ልቦና ማማከር አገልግሎቶችን እያመቻቸ እና እየሰጠ መሆኑን፣ የሕፃናት ማቆያ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን እና የሥርዓተ-ፆታ ማካተቻ ጋይድላይን  እያዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ከቀረበው ፅሁፍ ጋር ተያይዞ የሕፃናት ማቆያው ምን ደረጃ ላይ እንዳለ እና መቼ ሥራ እንደሚጀምር፣ ክብረ-በዓሉን ሁሉም የኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች ማክበር እንዳለባቸውና ሁሉንም ሴቶች ማሳተፍ እንዳለበት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎች ወ/ሮ ፋጡማ ጀማል መልስ ሰጥተዋል፡፡ የህፃናት ማቆያውን በተመለከተ አገልግሎቱ ያልጀመረው በግዥ ሂደት መጓተት የህፃናቱ መጫወቻዎች ባለመሟላታቸው ምክንያት መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ፋጡማ ጀማል አገልግሎቱ መጫዎቻወቹ እንደተሟሉ የሚጀምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡በዕለቱ የኮርፖሬሽኑ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ መምሪያ ሥርዓተ-ፆታን በማስረፅ ሂደት ቀና ትብብር ላደረጉ፣ ለሴት ሠራተኞች እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለኮርፖሬሽኑ አንዳንድ መምሪያዎች እና ለኮርፖሬሽኑ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ የኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች በማህበራዊ  እና  በኢኮኖሚያዊ  ችግሮቻቸው/ጉዳዮቻቸው ላይ በየወሩ በመገናኘት የሚወያዩበት እና መፍትሔዎችን የሚያመነጩበት የሴቶች ፎረም የተቋቋመ ሲሆን ለዚህም ዓላማ ፎረሙን የሚመሩ አምስት ሴት አባላት ተመርጠዋል፡፡
1.8K views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 16:22:04
1.6K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 16:21:07 የዚምባቡዌ የልዑካን ቡድን የኮርፖሬሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
--------------------------
የዚምባቡዌ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ማምረቻ ማዕከልን፣ በተገጣጣሚ ህንፃ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የ5 ሺህ ቤቶች ግንባታንና በቅርቡ የተጠናቀቀውን የኮንስትራክሽን ሙያተኞች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንዳሉት ኮርፖሬሽኑ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የገበያ አድማሱን ለማስፋት በርካታ ሥራዎችን በሚሰራበትና የኢንተርናሽናሌይዜሽን ሪፎርምን ተግባራዊ እያደረግንበት ባለበት ወቅት የተደረገ የልምድ ልውውጥ ስለሆነ ጠቃሚ ልምዶችን የልዑክ ቡድኑ ከኮርፖሬሽኑ እንደሚያገኝ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ግድቦች፣ የመስኖ እና የውሀ አቅርቦት ሥራዎችን፣ የህንፃና ቤቶች ግንባታዎችን በማከናወን ትልቅ ልምድ ያለው ኩባንያ ስለሆነ የነበሩ ልምዶቻችንን እያጎለበትን በጋራ አፍሪካን እንደምንገነባ እምነቴ ነው ብለዋል፡፡

ከጉብኝቱ በተጨማሪ የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቀሴና ተልዕኮውን የሚያሳይ የ10 ደቂቃ ፕሮሞሽናል ዶክሜንታሪና የኮርፖሬሽኑን የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓት ልዑካን በድኑ እንዲመለከቱ ተደርጓል፡፡

በዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት እና ካቢኔ ጽህፈት ቤት የፖሊሲ ትንተና፣ ማስተባበር እና የልማት እቅድ ምክትል ዋና ጸሃፊ ሚስተር ሚላርድ ማኑንጎ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ የተገጣጣሚ ህንፃ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ እየሰራቸው ባሉ ሥራዎች፣ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓቱን ቀልጣፋና የመረጃ ልወውጡን ፈጣን ለማድረግና የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ አምርቶ ለመጠቀም እያደረገው ያለውን ጥረት አድንቀው በቀጣይ በጋራ ከኮርፖሬሽኑ ጋር እንሰራለን ብለዋል፡፡
1.8K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 12:01:25 https://www.facebook.com/100064451782216/posts/pfbid029Assk8o5CRQLAEneiKrZLEU4EaQQdJtYaZX5x7AL2EN5JxVknj7ykX7P77AH8XNbl/?app=
1.5K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 10:55:00
1.7K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 10:54:51
1.7K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 10:53:51 የኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች ታላቁ ሩጫ ላይ ተሳተፉ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ሴት ሠራተኞች በየዓመቱ እ.ኤ.አ አቆጣጠር ማርች 8 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት በአገር አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ በተካሄደው ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች ታላቁ ሩጫ ላይ ተሳተፉ፡፡
መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው እና ከ15 ሺህ በላይ እንስቶች በተሳተፉበት በዚህ የ5 ኪ.ሜ የመካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድር ወደ 200 የሚጠጉ የኢ.ኮ.ሥ.ኮ ሴት ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የሩጫ ውድድሩ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የገለፁት በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጡማ ጀማል ውድድሩ በየዓመቱ መካሄዱ ሴቶች አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ፣ በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ፣ ራሳቸውን እንዲያዝናኑ እና በሥነ-ልቦና እንዲያንፁ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም እንደኮርፖሬሽን ተቋማቸውን እንዲወዱና እንዲያስተዋውቁ እንዲሁም የሥራ ፍቅር እና ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ያስችላል ያሉት ወ/ሮ ፋጡማ ኮርፖሬሽኑ ይህንን ተረድቶ የሥራው አንዱ አካል እንዲያደርግ፣ ለሥርዓተ-ፆታ ትኩረትና እውቅና በመስጠት የመንግስትን ፖሊሲ እንዲያስፈፅም መምሪያው ክትትል ያደርጋል ብለዋል፡፡
መነሻውን ከቦሌ አትላስ ያደረገው የሩጫ ውድድሩ በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከዚያም በፍሬንድሺፕ አድርጎ መጨረሻውን ቦሌ አትላስ ላይ አድርጓል፡፡
የ2015 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር “ቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ-ሥላሴ፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ አትሌት ለተሰንበት ግደይን ጨምሮ ሌሎችም አትሌቶችና እንግዶች ተገኝተዋል።
1.7K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 10:49:59 Table 1 : Eligibility criteria
s/n Criterial Verification document Requirement
1 Nationality (Ethiopia or abroad) registration certificate Must meet
2 Having at least 7 Professionals and Technicians with 3 years and above experiences Certificate “
3 Company Experience on construction works Document “
4 Tax Payer Identification Number (TIN) Certificate “
5 VAT registration certificate or ToT Certificate “
7 Financially Profitable for the last two years Official Audit report “
8 Renewed licence of grade GC-6/BC-6 or higher Renewed certificate “
9 Company Competence certificate (if applicable) Certificate “
10 Procurement Agencey registration (if applicable) Certificate “


ANNEX: Company profile contents
TABLE 1 – GENERAL INFORMATION
 Name of the Company
 Address
 Phone Number
 Fax Number
 Email Address
 Address of Other Offices, if any
 Name and Designation of the Contact Person
 Legal Status (Provide certified copies of Registration)
 Registration number
 Place of Registration
 Principal place of business
 VAT Registration number
 Provide certified copies
TABLE 2 – COMPANY EXPERIENCE IN LAST THREE YEARS
 Starting Month/ Year
 Ending Month / Year
 Client
 Description of services
 Contract Amount
Remarks (Provide documentary evidence)
TABLE 3 – SIMILAR EXPERIENCE IN LAST THREE YEARS
 Year
 Client
 Description of works
 Contract Amount
 Remarks (Provide documentary evidence )
 Please include copies of completion certificates issued by former clients and / or
 performance appreciation / evaluation letters from former clients providing their
 contact details and approval to contact them.5
TABLE 4 – ONGOING COTRACTS ( If any)
 Client
 Description of Contracts
 Location
 Amount
 % of Completion (Provide documentary evidence)

TABLE 5 - ADEQUACY OF WORKING CAPITAL
 Source of credit line
 Amount
 Remarks (Provide documentary evidence)
Please provide proof of financial competency and audited financial statements for the
last three financial years.
TABLE 6 – LIST OF PERMANENTLY EMPLOYED STAFF
 Name
 Designation Qualification
 No. of Years of Experience
Provide an organizational chart and detailed CVs for key management and technical
Personnel in the Organization
TABLE 7 – LIST OF PLANT AND EQUIPMENT (OWNED AND HIRED)
Description whether Owned or Leased
 Year of Manufacture
TABLE 8 – ANY OTHER INFORMATION
In addition to the required information, Companies may provide brochures and other
Related documents
I, the undersigned, warrant that the information provided in this form is correct and, in
the event of changes, details will be provided as soon as possible:
______________________ __________________ ___________
Ethiopian Construction Works Corporation.
Gurd Shola behind Athletics federation building
and Infront of Andinet international College
Telephone 011 8 72 29 58/ 0118 13 45 27
Addis Ababa, Ethiopia
1.2K views07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 10:49:59 Prospective national and international companies who are legally registered are invited to participate in the Expression of Interest (EOI). The applicants shall not be backlisted in any governmental organization. Competent applications meeting all requirements should be submitted all necessary documents in sealed envelope by courier on 12 April 2023 to the following Address until 5:00 PM.
ECWC Head office, Gurd shola
Corporate procurement main Department office
Motuma Gelana , Executive Officer
Tel No.: 011 8 72 29 58/ 0118 13 45 27
4 Assignment Duration
The firms /companies shall commence the assignment within 15 days after contract is signed between the parties. The duration of the work will be dependant on the project’s peculiarities for which the subcontractor will be hired to.
5 Requirements for Submission of Expression of Interest (EOI)
The EOI shall contain following documents:
• A cover letter for submission of expression of interest
• If joint venture, legal documents for the joint venture formation shall be submitted by the companies,
• Registration by Procurement Agency (if applicable)
• Complete organization profile,
• Company capacity statement, Financial, Manpower and equipment
• Registration Certificate from the Government Authority
• License with latest renewal for the current fiscal year (The licence need to be either GC-6/BC-6 or higher)
• VAT Registration Certificate,
• Tax clearance certificate that works to date of the submission of the EoI
• Attorney for the certification of the Authority,
• Financial flow statement approved by official Auditing entity,
• A cover letter for EOI typed in organizations letter head with official seal. There should be a subject head, the reference no of EOI notice and clear indication of the name and address of the of the company.
6 Works contracting Process
Successful companies/firms will enter contractual agreement with the corporation and commence the assignment accordingly. The contract will cover start to end of the assignment including provision of the assigned construction work.
7 Minimum Eligibility Criteria
Firm’s service provider’s minimum eligibility criteria are as under:
1) Minimum 5 years of demonstarated experience in construction works.
2) The firm/company should have experienced and appropriate professionals in construction activities
3) The firm shall have the necessary equipments to undertake tasks
4) The firm should be profitable for last two Financial Years
5) The firm shall have local presence for which it is willing to express interest.
8 Evaluation Process, Criteria and Qualification Requirement,
8.1 Evaluation Process and Criteria
The evaluation criteria will mainly depend on relevant document submitted by the company/firm. ECWC will have the mandates to prepare the evaluation criteria and shortlist eligiable companies. Accordingly, successful and shortlisted company/firm will be communicated through official letter.
Qualification Requirements
Company’s /firm profile and required documents shall include: Description of the respondent, including number of employees and type of machineries (including capacity), highlight relevant experience, skills, and capabilities necessary to undertake the assignments, including, but not limited to demonstrated experiences. Furthermore, the company/firm has to demonstrate that it will have available technical personals, plant and equipment’s for implementation of the assignment compliant with national and international standards.
This Section contains all the criteria that the Procuring entity shall use to evaluate and determine qualify company. The company shall provide all the information as required by ECWC s indicated in the in the proceeding table.
1.1K views07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ