Get Mystery Box with random crypto!

ECWC/ኢኮሥኮ/

የቴሌግራም ቻናል አርማ ecwccom — ECWC/ኢኮሥኮ/ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ecwccom — ECWC/ኢኮሥኮ/
የሰርጥ አድራሻ: @ecwccom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.23K
የሰርጥ መግለጫ

Official ECWC Telegram Channal
.የኮርፖሬሽኑ ዜናዎች
.የጨረታና የሥራ ማስታወቂያዎች
. በየወሩ የሚታተመው የዜና መጽሄት
. ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮች
.በየ 6ወሩ የሚታተመው የኮርፖሬሽኑ ዕይታ መጽሄት እና የኮርፖሬሽኑ ፕሮፋይል በዚህ ገጽ ላይ በየጊዜው ይቀርባል፡፡

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-05 14:10:32
2.0K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 10:32:34 https://vm.tiktok.com/ZM2uBXGUp/
2.4K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 08:41:44 https://fb.watch/lyKseumULp/?mibextid=RUbZ1f
2.4K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 11:09:12
3.0K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 11:08:46
3.0K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 11:08:33
2.9K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 11:08:12 አትሌቱ ውድድሩ አበረታች እንደነበር ገለፀ
በአዲስ አበባ የአትሌቲክስ ስፖርት ክለቦች መካከል በተካሄደው 1ኛው የፔፕሲ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የሜዳ ላይ ተግባራት የመዝጊያ የሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የስፖርት ክለብ የአትሌቲክስ ቡድንን በመወከል በ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ የተሳተፈው የክለቡ አትሌት ሀብቱ ሞላ ውድድሩ ወደፊት ለሚደረጉ ውድድሮች ተስፋ የሚሰንቅ እና የሚያበረታታ እንደነበር ገልጿል፡፡
የመሰናክል ሩጫ ውድድሩ ፈታኝ እና ከፍተኛ ፉክክር የነበረበት እንደነበር የገለፀው አትሌት ሀብቱ ሞላ ርቀቱን 9 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት አንደኛ የወጣውን የመቻሉን ሯጭ አትሌት ኪዳነ ማርያም ደሴን በ4 ሴኮንድ ልዩነት ተከትሎ በመግባት ሁለተኛ በመውጣቱ ከፍተኛ ደስታ፣ ተስፋና መበረታታት እንደፈጠረበት ተናግሯል፡፡
ከውድድር አስቀድሞ ደረጃ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ጠብቆ የነበረው አትሌት ሀብቱ ሞላ በመሰናክል ውድድሩ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ለክለቡ እና ለራሱ የብር ሜዳሊያ በማስገኘቱ ብሎም የራሱን እና የክለቡን ስም ከፍ በማድረጉ ከፍተኛ ደስታ፣ ኩራት እና መበረታታት እንደተሰማው ገልጿል፡፡
በ12 አትሌቶች መካከል በተካሄደው በዚህ የመሰናክል የሩጫ ውድድር የተሳተፈው አትሌት ሀብቱ ሞላ ከዚህ በፊት የተሳተፈባቸው የሩጫ ውድድሮች እና የወሰዳቸው ስልጠናዎች ደረጃ ውስጥ እንዲገባ እንዳስቻሉት ገልጿል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ክለብ ወደ ኢኮሥኮ የስፖርት ክለብ ተዛውሮ በከፍተኛ ፍቅር የተዛወረበትን ክለብ በመወከል በመካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድሮች እየተሳተፈ ያለው አትሌት ሀብቱ ሞላ ወደ ፊት ታላቅ ሯጭ የመሆን ራዕይ እንዳለውና ለዚህም ስኬት ጠንክሮ እንደሚሠራ ገልጿል፡፡
የመሰናክል ሩጫ ውድድሩ ከሌሎች ውድድሮች ይልቅ ከባድና ፈታኝ እንደሆነ የገለፀው የኢኮሥኮ የአትሌቲክስ ስፖርት ክለብ ቡድን መሪ ደረጀ የኔአባት በበኩሉ በተደረጉ ውድድሮች አትሌት ሀብቱ ሞላ ወደ ፊት ታላቅ ሯጭ መሆን የሚችል ጠንካራ እና ተስፈኛ ልጅ እንደሆነ ተረድቻለሁ ብሏል፡፡
ቡድን መሪው የኢኮሥኮ የአትሌቲክስ ስፖርት ክለብ አትሌቶች በውድድሩ በተለያዩ ርቀቶች በመሳተፍ ለክለቡ የተሻሉ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻላቸውን የገለፀ ሲሆን ይህም ወደፊት ለሚደረጉ የሩጫ ውድድሮች መነቃቃትን የሚፈጥር፣ ተስፋ የሚሰጥ እና የሚያበረታ ነው ብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከሰኔ 22 እስከ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ቀናት በ12 የአዲስ አበባ የአትሌቲክስ ስፖርት ክለቦች መካከል የተካሄደው ይህ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የሜዳ ላይ ተግባራት የሩጫ ውድድር አትሌቶች ምን ዓይነት አቋም ላይ እንደሆኑና የሥልጠና ጊዜያቸውን እንዴት እንዳሳለፉ ለመረዳት ያለመ ነበር፡፡
2.8K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 09:21:03
2.8K views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 09:20:26
2.8K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 08:50:46
2.9K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ