2023-04-07 11:07:41
የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የፈረንጅ ሱፍ እና ሰሊጥ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ECWCT/NCB/SG-113/2015
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በቃሊቲ መጋዘን የሚገኘውን የፈረንጅ ሱፍ እና ሰሊጥ ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት መረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ስዓት ከዋናው መ/ቤት የሃገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከፍተኛ ዋጋ የሚያቀርበው ሲሆን የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
3. ተጫራቾች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሚያዝያ 03 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡3ዐ ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
4. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር አስር በመቶ /10%/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በኢንሹራንስ ቦንድ /በሌላ መልክ የሚቀርብ ማንኛውም ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 03 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጠዋት 05፡00 ሰዓት ጉርድ ሾላ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት ቅጥር ግቢ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ለበለጠ መረጃ በሚከተለው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አድራሻ ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ አለፍ ብሎ
አንድነት ት/ቤት ፊት ለፊት
የኮርፖሬት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና መምሪያ
የፖ.ሣ.ቁጥር 21952/1000
የስልክ ቁጥር 0118-13-45-27 /011-8-72-29-58
1.1K views08:07