Get Mystery Box with random crypto!

ECWC/ኢኮሥኮ/

የቴሌግራም ቻናል አርማ ecwccom — ECWC/ኢኮሥኮ/ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ecwccom — ECWC/ኢኮሥኮ/
የሰርጥ አድራሻ: @ecwccom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.23K
የሰርጥ መግለጫ

Official ECWC Telegram Channal
.የኮርፖሬሽኑ ዜናዎች
.የጨረታና የሥራ ማስታወቂያዎች
. በየወሩ የሚታተመው የዜና መጽሄት
. ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮች
.በየ 6ወሩ የሚታተመው የኮርፖሬሽኑ ዕይታ መጽሄት እና የኮርፖሬሽኑ ፕሮፋይል በዚህ ገጽ ላይ በየጊዜው ይቀርባል፡፡

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 45

2022-07-13 13:55:08
2.7K views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:54:54
2.5K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:54:46
2.4K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:54:33
2.4K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:54:17 መምሪያው ዓለም አቀፍ የሕፃናት ቀንን በማስመልከት አምባ የሕፃናት ማዕከልን ጎበኘ
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ መምሪያ ዓለም አቀፍ የሕፃናት ቀንን በማስመልከት በየካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9 የሚገኘውን ኤምፓ አምባ የበጎ አድራጎት የህፃናት ማዕከልን ጎበኘ፡፡
በኮርፖሬሽኑ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጡማ ጀማልን ጨምሮ ሌሎች የመምሪያው ሠራተኞች ማዕከሉን ሐምሌ 05 ቀን 2014 ዓ.ም የጎበኙ ሲሆን በጉብኝት ወቅት የሕፃናቱን የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መፅሐፍት፣ የኮምፒዩተር ክፍሎች፣ የመመገቢያ ክፍሎች፣ የመኝታ ክፍሎች እና ሌሎችንም ፋሲሊቲዎች ተመልክተዋል፡፡





ማዕከሉን ያስጎበኙት እና ስለ ማዕከሉ ዝርዝር መረጃ የሰጡት የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሌብ ፀጋዬ በአሁኑ ሠዓት ከ3 ዓመት ከስድስት ወር እስከ 8 ዓመት የዕድሜ ክልል ላሉ ለችግር የተጋለጡ አካል ጉዳተኛ እና በአስከፊ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 200 ሕፃናት ነፃ የትምህርት ዕድል፣ የምገባ፣ የአልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና የሥነ-ልቦናና የክህሎት ሥልጠና ድጋፎች እያደረጉ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ማዕከሉ ከተመሠረተበት 2001 ዓ.ም ጀምሮ ለ900 ሕፃናት ድጋፍ መድረጉን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለችግር የተጋለጡ ነጠላ ቤተሰቦችንም በልዩ ልዩ ክህሎት በማሰልጠን የልጆቻቸው ደጋፊ እና ዓላማ ተጋሪ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
በጉብኝት ወቅት “በራስ ተነሳሽነት እና በበጎ ፍቃድ ዘርፈ-ብዙ የሕብረተሰብ ችግሮች ላይ የምትሠሩት ከፍተኛ ሥራ የሚበረታታ እና የሚደነቅ ነው” ያሉት የመምሪያው ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጡማ ጀማል “ልጆች መቀረፅ ባለባቸው ትክክለኛ ዕድሜ ላይ ነው እየሠራችሁ ያላችሁ; በእኛ በኩል የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር ጉዳዩ ከሚመለከተው የሥራ ክፍል ጋር በመነጋገር ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ሌሎች የመምሪያው ሠራተኞች እየተሠራ ያለው ሥራ እጅግ የሚመሰገን እና የሚበረታታ መሆኑን በአድናቆት የገለፁ ሲሆን “በቀጣይ ከእንደነዚህ መሠል ተቋማት ጋር አብረን ለመሥራት አቅደናል፡፡ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ በእናንተ በኩልም ቋሚ ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ ሥራዎችን ብትሠሩ መልካም ነው” ብለዋል፡፡
ማዕከሉ ማንኛውንም ድጋፍ በደስታ እንደሚቀበል የገለፁት አቶ ካሌብ ከተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች በርካታ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ፣ የዓይነት እና ሌሎች ዘርፈ-ብዙ ድጋፎች እንዲደረግላቸው ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ማዕከሉ ራሱን በራሱ መደገፍ ይችል ዘንድ የዶሮና የከብት እርባታ ለማካሄድ እንዲሁም በረጅም ጊዜ ዕቅድ ደግሞ ትምህርት ቤት ለመክፈት ማቀዱን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የመምሪያው ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጡማ ጀማል ለሕፃናቱ መጠቀሚያ የሚያገለግሉ የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችን ለማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ለአቶ ካሌብ ፀጋዬ አበርክተዋል፡፡
2.9K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:21:55 sent for release on the website
3.2K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 16:56:54
6.1K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:42:32 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከ “The Big 5 Construct Ethiopia” ጋር በሚቀጥለው ዓመት በሚያዘጋጁት ኤግዚቢሽን ዙሪያ የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ የተላለፈውን ዘገባ ለመመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

6.4K viewsedited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:55:28
5.6K views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ