Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ drzakirnaiki — ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ drzakirnaiki — ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @drzakirnaiki
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.08K
የሰርጥ መግለጫ

Any comment 👉 @Ri_3s

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-02 20:55:11 ተናፋቂው ረመዷን ~~ በእርግጠኝነት ባለፈው አመት ረመዳን ሲጠናቀቅብህ ብዙ የተፀፀትክባቸው ጉዳዮች አሉ። ቁርአን ያከተምከው ትንሽ ጊዜ መሆኑ የሌሊት ሶላት ላይ የነበረብህ ክፍተት የሰጠኸው ሰደቃ አናሳ መሆን ሰዎችን አለማስፈጠርህ ያልተፈቀዱ ነገራቶችን መመልከትህና  ማድመጥህ ከቤተሰብና ጓደኛ ጋር የነበረህ ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት ዚክር ላይ የነበረህ ድክመት ሶላትን በጀመዓ አለመስገድህ…
674 views ° ꧁༺ًًًٍٍٰٰٰٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡❁➳R.B.I.A❥︎➳⃝ ͢ ̶ͥ, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 23:44:57
ባለ ትዳር ነሽ ወይስ ገና አላገባህም
ወይስ መንገድ ላይ

ስለ ፍቅር እና ትዳር በጣፋጭ ትረካዎች እያዋዛ የሚያቀርብ ፍቅር የሆነ ቻናል ይዘን ብቅ አልን!

JOIN በማለት ብቻ ቤተብ ይሁኑ!
290 viewsᴍ ᴛʜᴇ ᴅᴀƦᴋ ʙᴏʏ, 20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 21:03:22 ተናፋቂው ረመዷን
~~
በእርግጠኝነት ባለፈው አመት ረመዳን ሲጠናቀቅብህ ብዙ የተፀፀትክባቸው ጉዳዮች አሉ።
ቁርአን ያከተምከው ትንሽ ጊዜ መሆኑ
የሌሊት ሶላት ላይ የነበረብህ ክፍተት
የሰጠኸው ሰደቃ አናሳ መሆን
ሰዎችን አለማስፈጠርህ
ያልተፈቀዱ ነገራቶችን
መመልከትህና  ማድመጥህ
ከቤተሰብና ጓደኛ ጋር የነበረህ ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት
ዚክር ላይ የነበረህ ድክመት
ሶላትን በጀመዓ አለመስገድህ ...
:
:
:

ታዲያ
አላህ አድሎህ ለዚህ ረመዳን ካደረሰህ
የዘንድሮውን ረመዳን ከአምናው ረመዳን በምን ልትለየው አስበሃል? እንዲሁ እንደተጃጃልክ? ዝንጉ ሁነህ? ወይስ ሃሳብህ ተመሳሳይ ረመዳንን ለማሳለፍ ነው ? ካሁኑ ስለ ረመዷን እንሰብ እንዘጋጅ እንቅራ እንናዳምጥ እናንብብ እኔንም እንንተንም አላህ ያግራልን አሚን።

#share
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki
1.1K viewsŘěď.. [99.9%] , 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 21:11:34 ዱዓ አድርግ
=========
«የሆነ ነገር ፈልገህ ዱዓ ታደርግና ያ የፈለከው ነገር ከብዙ አመታትና ከረሳሀው ቡሀላ እውን ይሆንልሀል አንተ ብትረሳውም አላህ ግን አይረሳም ብቻ ዱዓ አድርግ እሱ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቆ እውን ያደርግልሃል»

በተለይ መጭው ወር ረመዷን እንደመሆኑ በዚህ ወር በኢባዳና፣ በዱዓ ወደ አላህ ልንቀርብ ግድ ይለናል፣ ረመዷንንም ልንጠቀምበት ይገባል።

#ለእኔም ዱዓ አድርጉልኝ
2.4K viewsŘěď.. [99.9%] , 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 07:10:01 ወላሂ! ትልቅ ሱናህ!!!
ያላፈዝነው እናፍዘው፡፡ ያፈዝነው እንተግብረው፡፡
5 የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚባል ዋጋው የገዘፈ አንድ ትልቅ
ዚክር!!
[ ﺳﺒْﺤﺎﻧَﻚ ﺍﻟﻠَّﻬُﻢّ ﻭﺑﺤَﻤْﺪﻙَ ﺃﺷْﻬﺪُ ﺃﻥْ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺃﻧْﺖ
ﺃﺳْﺘﻐْﻔِﺮﻙَ ﻭَﺃﺗَﻮﺏُ ﺇﻟﻴْﻚَ ]
[ሱብሓነከልሏሁመ ወቢሐምዲከ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢላ አንተ
አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ]
1. ከዚክር ቆይታ በኋላ ይህንን ያለ ልክ እንደ ማሸጊያ፣ ጥሩ
መቋጫ ይሆነዋል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 81]
2. ከዛዛታና ቀልድ በኋላ ይህንን ያለ ከቦታው የተፈፀሙ
ወንጀሎቸን አላህ ያብስለታል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 2651]
3. ከውዱእ በኋላ ይህንን ዚክር ያለ እስከ እለተ ቂያማ ምንዳው
ባስተማማኝ መቀመጫ ታሽጎ ይቀመጥለታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ፡
225]
4. ይህንኑ ዚክር ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሶላት በኋላም
ይሉት ነበር፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3164]
5. ቁርኣን ከቀሩ በኋላም ይሉት ነበር ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
[ነሳኢይ]
እንዲህ አይነት ትልቅ ሀብት ይዘው ዝም አይበሉ፡፡ ለወዳጅ
ዘመዶችዎ ያድርሱ፡፡ ተጨማሪ አጅረዎን ይፈሱ

#SHARE
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki
1.7K viewsᴰᴬᴰ๔єคг ๓๏๓ᴰᴬᴰ, 04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 21:17:04
#የሩሕ መስከረም
*
ደርሰው ከሚፆሙት እንዲሁም ፆመው ከሚጠቀሙበት ያድርገን
Amin
:
#Share https://t.me/drzakirnaiki
2.0K views ° ꧁༺ًًًٍٍٰٰٰٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡❁➳R.❥︎➳⃝ ͢ ̶̶ͥ ̶ ➣, edited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:50:55 ​​
#ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ
እነሆ በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው እውነተኛ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ይዘንላቹ መተናል
እውነተኛ ታሪክ
#ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ

ሊያመልጦት አይገባም!!
ከመጀመሪያ ጀምሮ ለመከታተል ከታች
ክፍል ⓵ የሚለውን ይጫኑት።
ወላሒ ውሸት አይደለም ግቡና አንብቡት
127 views ° ꧁༺ًًًٍٍٰٰٰٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡❁➳R.❥︎➳⃝ ͢ ̶̶ͥ ̶ ➣, 12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 16:37:23 ስለ ረመዷን  
▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል:- አንድ
አላህ ሰማያት እና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ 12 ወራትን ፈጠረ ከአስራ ሁለቱ አራቱ የተከበሩ ወሮች ናቸው።
በነዚህ የተከበሩ ወሮች ሚሰሩ መልካምም ይሁን መጥፎ ስራዎች  ከሌሎች ወሮች በተለየ እጥፍ ይደረጋሉ።
1. ዙል ቃኢዳ
2. ዙል ሒጃ
3. ሙሐረም
4. ረጀብ
ነገር ግን ቁርኣን ውስጥ ስሙ የተጠቀሰ ብቸኛው ወር የ "ረመዷን" ወር ነው
እንዲህ በማለት:-
شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِىٓ أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْءَانُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنٰتٍ مِّنَ الْهُدٰى وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهََُ۝
«የረመዷን ወር ያ ቁርኣን የወረደበት ወር ነው። (ቁርኣኑ) ለሰው ልጆች ቀጥተኛውን መንገድ የሚያመላክት ቀጥተኛውን መንገድና የጥመት መንገድ የተብራራበት ነው። ከእናንተ ወሩን የተጣደ (የደረሰበት)  ሰው ይፁመው።»
አል-በቀራ (185)
:
ፆም ማለት ምን ማለት ነው
ፆም (الصوم) የሚለው የዐረብኛ ቃል ከቋንቋ አንፃር ፍቺው [الإمساك] (መቆጠብ) የሚል ትርጓሜ ይሰጠናል።
ይህንን ቋንቋዊ ፍቺ ይዘን ወደ ሸሪዓ ትርጓሜው ስንሄድ የዲን ሊቃውንቶች ከሚያስቀምጡት ማብራሪያ ቀጣዩን እናገኛለን።
الإمساك عن الأكل والشرب والجماع وسائر المفطرات بنية التعبد لله، من طلوع الفجر إلى غروب الشمس
«ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነት እና ከሌሎችም ፆምን ከሚያፈርሱ ነገሮች ለአላህ አምልኮትን ታስቦበት ጎህ ሲወጣ ጀምሮ ፀሀይ እስከ ምትገባ ድረስ መቆጠብ ማለት ነው።»
*
ፆም ለስንት ይከፈላል
ምሁራኖች አጥንተው ባስቀመጡት መልኩ ፆም ለአራት (4) ይከፈላል፦

1ኛ) በድንጋጌ ግዴታ የተደረገ የፆም ዐይነት (የረመዷን ወር) ፆም፤
*
2ኛ) በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚከሰቱ ወንጀሎች ላይ ለማበሻነት የሚደረግ (ከፋራ) የሚባለው የፆም ዐይነት፤
*
3ኛ) አንድ ሰው በራሱ ፍቃድ ስለት አደርጎ የሚፆመው (ነዝር) የሚባለው የፆም ዐይነት እና፤
*
4ኛ) በየትኛውም ጊዜና ለየት ባሉ ወቅቶች ላይ በፍላጎት የሚፆመው (ተጠዉዕ) (የሱና) ፆም ነው።
*
የረመዷን ፆም ፍርዱ ምንድን ነው
የረመዷን ፆም እስልምና ከተገነባባቸው አምስቱ መሰረቶች አንዱ ሲሆን በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ መፆሙ ግዴታ ነው።
:
የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
بُنِيَ الإِسْلامُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةِ أَنْ لا إِلَهَ إِلا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامِ الصَّلاةِ وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ وَالْحَجِّ وَصَوْمِ رَمَضَانَ
«እስልምና በአምስት ነገሮች ተገንብቷል
1) ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደ ሌለ እና ሙሐመድ መልዕክተኛው እንደ ሆኑ መመስከር፣
2) ሰላትን ቀጥ አድርጎ መስገድ፣
3) ዘካትን መስጠት፣
4) የአላህን ቤት መዘየር (ሐጅ ማድረግ) እና
5) የረመዷንን ወር መፆም።
*
የረመዷን ወር መፆም በምን ዐይነት ሰው ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው
ለአቅመ አዳም በደረሰ፣
ሰውነቱ እና አዕምሮው ጤነኛ በሆነ፣
ነዋሪ በሆነ (መንገደኛ ያልሆነ)፣
ከወር አበባ እና ከወሊድ ደም ነፃ በሆነች ሴት ላይ ግዴታ ይሆናል።
*
የረመዷን ወር እንኳን መጣላችሁ መባባል ሱና ነው እኔም ከወዲሁ ለናንተ
እንኳን መጣላችሁ ብያለው
*
ረመዷን 27 ቀን ይቀሩታል!
ደርሰው ከሚፆሙት እንዲሁም ፆመው ከሚጠቀሙበት ያድርገን!
:
ረጀብ 3, 1444 H.C

https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki
2.5K viewsŘěď.. [90.5%] , edited  13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 15:05:37
ያረብ በዱአችን አንርሳቸዉ ።

#ቦረና የተከሰተ ድርቅ

#ያረብ ራህመትህን አዉርድላቸዉ.

Amiiin
2.1K viewsŘěď.. [90.5%] , 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 07:30:29 ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል:
ረመዳን
  

ረመዳን የተከበረው ወር ስያሜ መሆኑ ይታወቃል። ለመሆኑ ረመዳን ማለት ምን ማለት
ነው?

ረመዳን የሚለውን ስያሜ የቋንቋው ሊቃውንቶች በተለያየ መልኩ አብራርተውታል።
ከፊሎች ረመዳን (ረመደ ወይም ረምዳእ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ።
ይህ ማለት ደግሞ ጥማትና ረሀብን የሚያመጣ እጅጉን የበረታ ሀሩር (ሙቀት) ማለት
እንደሆነ አያይዘው ይገልፃሉ።
ሌሎችም ከዚህ ጋር ተቀራራቢ ባለው መልኩ አብራርተውታል።


ለምሳሌ ታላቁ ሙፈሲር ኢማሙል ቁርጡብይ :—
"ረመዳን እኮ የተባለው ወንጀሎችን
በመልካም ስራዎች አቃጥሎ አመድ ስለሚያደርጋቸው ነው።" በማለት አብራርተውታል።
ቁም ነገሩ:—
ማነው በዚህ በተከበረ ወር መልካም ስራዎችን አብዝቶ በመስራት አመቱን ሙሉ
ያከማቸውን ወንጀል አቃጥሎ አመድ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ!?

ረመዳን ቁርአን የወረደበት ወር
ረመዳን የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ️የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት
ረመዳን ሰይጣኖች የሚታሰሩበት ወር
ረመዳን ከሺህ ወር የምትበልጥ አንድ ሌሊት የያዘ ወር
ረመዳን ከምንጊዜውም በበለጠ ዒባዳ የሚደረግበት ወር
ረመዳን ፈርድ ስራዎቻችን በ 70 የሚባዙበት ሱናዎቻችን የፈርድን ዋጋ የሚያገኙልን ትልቁ
የረመዳን ወር ነው።

ረመዳን መጣ!!!!!!

እንግዲህ ጓዴ ሆይ፤
ሾይጣን ሊታሰር ነው፤ ረመዳን መጣ፤
መቼስ ሰው ነኝና፤
የበደልኩህ ካለ፤
አኡፉ በሉኝና!!!!!
እኔም ሸክሜ ይቅለል፤ አንተም ነጃ ውጣ።

         (((  ሬድዋን ሙስጠፈ )))

#እዚህ ቻናል አባላት ላይ ባለማወቅ ያስቀየምኳቹ  ፣ በምፅፈው ነገር ቅር የተሰኛቹ ወንድምና እህቶቼም ካላቹ ያው ካለማወቅ ካለመብሰል ሊሆን ስለሚችን አውፍ (ይቅርታ ) አድርጉልኝ ከልባቹ!!

#መልካም_ጁምዓ
   #ሼር_አድርጉት

https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki

  
258 viewsᴰᴬᴰ๔єคг ๓๏๓ᴰᴬᴰ, 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ