2023-02-11 06:37:08
አንድ ዒባዳ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አንድ ዒባዳ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ መሟላት ያለባቸው ስድስቱ መሰረታዊ ነገሮች!
||
ኡለማዎች በአጠቃላይ አንድን ዒባዳ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ የግድ ሁለት ነገሮች መገኘት እንዳለባቸው ተስማምተዋል።
:
1ኛው «አል-ኢኽላስ» (ለአላህ ብቻ ብሎ መስራት) ሲሆን፤
2ኛው «አል-ሙታባዕ (የአላህ መልዕክተኛ በሰሩት መልኩ መስራት) ነው።
*
አንድ ዒባዳ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ በሰሩት መልኩ ሊሰራ አይችልም የግድ ስድት መሰረታዊ ነገሮች ገጥሞ ከተገኘ እንጂ።
:
እነሱርም:- የዒባዳው ምክንያቱ፣
ዐይነቱ፣ መጠኑ፣ አፈፃፀሙ፣ ጊዜው እና ቦታው ናቸው።
:
(እስኪ በዝርዝር አንድ በአንድ እንያቸው! ተረጋግታችሁ ፁሁፉን ለመጨረስ ሞክሩ ከጨረሳችሁም በኋላ አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ ለሌሎች አድርሱት!)
:
አንድ ዒባዳ እነዚህ ስድስት ነገሮች ሳይገጥም ቢሰራ ዒባዳው አላህ ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም ተመላሽ ይሆናል! ምክንያቱም በአላህ ዲን ላይ የተጨመረ ፈጠራ ስለ ሚሆን።
||
1ኛ) የዒባዳው ምክንያት
የትኛውንም ዒባዳ ሲሰራ ምክንያቱ ሸሪዐውን የገጠመ መሆን አለበት። ከሸሪዐዊ ምክንያቱ ከወጣ ስራው ውድቅ ይሆናል።
:
ለምሳሌ:-
አንድ ሰው ሁሌም ቤቱ በገባ ቁጥር ሁለት ሁለት ረከዐ መስገድ ሱና አድርጎ ቢይዝ ይህ ሰላት ውደቅ ይሆንበታል።
ሰላት የተደነገገ ከመሆኑም ጋ እዚህ ቦታ ላይ ግን ሸሪዐዊ ምክንያት ባለ መግጠሙ ውድቅ ይደረግበታል።
*
2ኛ) የዒባዳው ዐይነት
የትኛውንም ዒባዳ ዐይነቱን ሸሪዐን የገጠመ መሆን አለበት። የዒባዳው ዐይነት ከሸሪዐው የወጣ ከሆነ ዒባዳው ውድቅ ይሆናል።
:
ለምሳሌ:-
አንድ ሰው የዑዱሂያ ቀን ፈረስ አርዶ ዑዱሂያ ይሁንልኝ ቢል ተቀባይነት አይኖረውም። ምክንያቱም ሸሪዐ ባዘዘን መልኩ ለኡዱሂያ ሊታረዱ የሚችሉት ﺑﻬﻴﻤﺔ اﻷﻧﻌﺎﻡ ተብለው የተጠቀሱት ናቸው። እነሱም በሬ (ላም)፣ በግ (ፍየል) እና ግመል ናቸው። ከእነዚህ ውጪ ያለ እንስሳ ግን አርዶ መብላቱ የሚበቃ ቢሆንም ለኡዱሂያ ማረድ ግን አይቻልም።
*
3ኛ) የዒባዳው መጠን
የትኛውንም ዒባዳ ሲሰራ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ መጠኑ በሸሪዐ ከተቀመጠው መጠን መግጠም አለበት። ከተቀመጠው መጠን ቢያልፍ ወይንም ቢያንስ ዒባዳው ውድቅ ይሆናል።
:
ለምሳሌ:-
አንድ ሰው ውዱዕ ሲያደርግ አራት አራት ጊዜ ቢታጠብ ይህ ሰው መጠኑን አልፏልና ዒባዳው ውድቅ ይሆናል።
ወይንም አራት ረከዐ የሚሰገደው ሰላት ሶስት ረከዐ አድርጎ ቢሰግድ ሰላቱ ውድቅ ይሆናል። ምክንያቱም ሸሪዐ ካስቀመጠው መጠን አሳንሷልና።
:
4ኛ) የዒባዳው አፈፃፀም
የትኛውንም ዒባዳ ተቀባይነት እንዲኖረው አፈፃፀሙ በሸሪዐ በተቀመጠው መልኩ መሆን አለበት። ከዚህ ውጪ ሆኖ በሌላ አፈፃፀም ከሆነ ውድቅ ይሆናል።
:
ለምሳሌ:-
አንድ ሰው ዉዱዕ ሲያደርግ መጀመሪያ እግሩን ታጥቦ ከዝያም ፀጉሩን አብሶ ከዝያም እጁን አጥቦ ወደ ፊቱ ቢሄድ ይህ ውዱዕ ውድቅ ይሆንበታል።
ወይንም እየሰገደ ሩኩዕ ሳያደርግ ሱጁድ አድርጎ ከዝያም ሩኩዕ እያደረገ ቢሰግድ ሰላቱ ውድቅ ይሆንበታል። ሸሪዐዊ አፈፃፀሙን አልጠበቀምና።
*
5ኛ) የዒባዳው ጊዜ
የትኛውንም ዒባዳ ሲሰራ ተቀባይነት እንዲኖረው በሸሪዐ የተደነገገለት ጊዜ መድረስ አለበት። ጊዜውን ሳይደርስ ቢሰራው ወይንም ያለ ምንም ምክንያት ከጊዜው ቢያሳልፈው ዒባዳው ተቀባይነት አይኖረውም።
:
ለምሳሌ:-
ሰላት መስገድ ፈልጎ ነገር ግን ጊዜውን ሳይደርስ ቢሰግደው ሰላቱ ውድቅ ይሆንበታል።
ወይንም ኡዱሂያ ማረድ ፈልጎ ነገር ግን ዒድ ከመስገዱ በፊት ቢያርደው ተቀባይነት አይኖረውም።
*
6ኛ) የዒባዳው ቦታ
የትኛውንም ዒባዳ ሲሰራ ተቀባይነት እንዲኖረው በሸሪዐ የተቀመጠለት ቦታው ላይ ነው መሰራት ያለበት። በሸሪዐ የተቀመጠለት ቦታ እያለ ከዝያ ውጪ በሆነ ቦታ ላይ ቢፈፀም ዒባዳው ውድቅ ይሆናል።
:
ለምሳሌ:-
አንድ ሰው ኢቲካፍ መግባት ፈልጎ ነገር ግን ቤቱ ውስጥ ወይንም መድረሳ ሄዶ ኢቲካፍ እቀመጣለሁ ቢል ተቀባይነት አይኖረውም። ምክንያቱም ኢቲካፍ መቀመጥ የፈለገ ሰው በሸሪዐ የተደነገገለት ቦታ መስጅድ ብቻ ነውና።
*
እነዚህ ስድስቱ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን በመገንዘብ እና ተግባራዊ በማድረግ ዒባዳችንን ውድቅ እንዳይሆንብን እንታደገው።
:
ከሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ምክር የተወሰደ ነው
*
አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሼር ማድረግ አትርሱ!
#ሼር_አድርጉት
ቻናሉን ተቀላቀሉ!
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki
655 viewsᴰᴬᴰ๔єคг ๓๏๓ᴰᴬᴰ, 03:37