Get Mystery Box with random crypto!

ወላሂ! ትልቅ ሱናህ!!! ያላፈዝነው እናፍዘው፡፡ ያፈዝነው እንተግብረው፡፡ 5 የተለያዩ ቦታዎች ላይ | Ethio Muslims ☪️

ወላሂ! ትልቅ ሱናህ!!!
ያላፈዝነው እናፍዘው፡፡ ያፈዝነው እንተግብረው፡፡
5 የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚባል ዋጋው የገዘፈ አንድ ትልቅ
ዚክር!!
[ ﺳﺒْﺤﺎﻧَﻚ ﺍﻟﻠَّﻬُﻢّ ﻭﺑﺤَﻤْﺪﻙَ ﺃﺷْﻬﺪُ ﺃﻥْ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺃﻧْﺖ
ﺃﺳْﺘﻐْﻔِﺮﻙَ ﻭَﺃﺗَﻮﺏُ ﺇﻟﻴْﻚَ ]
[ሱብሓነከልሏሁመ ወቢሐምዲከ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢላ አንተ
አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ]
1. ከዚክር ቆይታ በኋላ ይህንን ያለ ልክ እንደ ማሸጊያ፣ ጥሩ
መቋጫ ይሆነዋል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 81]
2. ከዛዛታና ቀልድ በኋላ ይህንን ያለ ከቦታው የተፈፀሙ
ወንጀሎቸን አላህ ያብስለታል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 2651]
3. ከውዱእ በኋላ ይህንን ዚክር ያለ እስከ እለተ ቂያማ ምንዳው
ባስተማማኝ መቀመጫ ታሽጎ ይቀመጥለታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ፡
225]
4. ይህንኑ ዚክር ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሶላት በኋላም
ይሉት ነበር፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3164]
5. ቁርኣን ከቀሩ በኋላም ይሉት ነበር ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
[ነሳኢይ]
እንዲህ አይነት ትልቅ ሀብት ይዘው ዝም አይበሉ፡፡ ለወዳጅ
ዘመዶችዎ ያድርሱ፡፡ ተጨማሪ አጅረዎን ይፈሱ

#SHARE
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki