Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ረመዷን   ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ክፍል:- አንድ አላህ ሰማያት እና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ 12 | Ethio Muslims ☪️

ስለ ረመዷን  
▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል:- አንድ
አላህ ሰማያት እና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ 12 ወራትን ፈጠረ ከአስራ ሁለቱ አራቱ የተከበሩ ወሮች ናቸው።
በነዚህ የተከበሩ ወሮች ሚሰሩ መልካምም ይሁን መጥፎ ስራዎች  ከሌሎች ወሮች በተለየ እጥፍ ይደረጋሉ።
1. ዙል ቃኢዳ
2. ዙል ሒጃ
3. ሙሐረም
4. ረጀብ
ነገር ግን ቁርኣን ውስጥ ስሙ የተጠቀሰ ብቸኛው ወር የ "ረመዷን" ወር ነው
እንዲህ በማለት:-
شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِىٓ أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْءَانُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنٰتٍ مِّنَ الْهُدٰى وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهََُ۝
«የረመዷን ወር ያ ቁርኣን የወረደበት ወር ነው። (ቁርኣኑ) ለሰው ልጆች ቀጥተኛውን መንገድ የሚያመላክት ቀጥተኛውን መንገድና የጥመት መንገድ የተብራራበት ነው። ከእናንተ ወሩን የተጣደ (የደረሰበት)  ሰው ይፁመው።»
አል-በቀራ (185)
:
ፆም ማለት ምን ማለት ነው
ፆም (الصوم) የሚለው የዐረብኛ ቃል ከቋንቋ አንፃር ፍቺው [الإمساك] (መቆጠብ) የሚል ትርጓሜ ይሰጠናል።
ይህንን ቋንቋዊ ፍቺ ይዘን ወደ ሸሪዓ ትርጓሜው ስንሄድ የዲን ሊቃውንቶች ከሚያስቀምጡት ማብራሪያ ቀጣዩን እናገኛለን።
الإمساك عن الأكل والشرب والجماع وسائر المفطرات بنية التعبد لله، من طلوع الفجر إلى غروب الشمس
«ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነት እና ከሌሎችም ፆምን ከሚያፈርሱ ነገሮች ለአላህ አምልኮትን ታስቦበት ጎህ ሲወጣ ጀምሮ ፀሀይ እስከ ምትገባ ድረስ መቆጠብ ማለት ነው።»
*
ፆም ለስንት ይከፈላል
ምሁራኖች አጥንተው ባስቀመጡት መልኩ ፆም ለአራት (4) ይከፈላል፦

1ኛ) በድንጋጌ ግዴታ የተደረገ የፆም ዐይነት (የረመዷን ወር) ፆም፤
*
2ኛ) በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚከሰቱ ወንጀሎች ላይ ለማበሻነት የሚደረግ (ከፋራ) የሚባለው የፆም ዐይነት፤
*
3ኛ) አንድ ሰው በራሱ ፍቃድ ስለት አደርጎ የሚፆመው (ነዝር) የሚባለው የፆም ዐይነት እና፤
*
4ኛ) በየትኛውም ጊዜና ለየት ባሉ ወቅቶች ላይ በፍላጎት የሚፆመው (ተጠዉዕ) (የሱና) ፆም ነው።
*
የረመዷን ፆም ፍርዱ ምንድን ነው
የረመዷን ፆም እስልምና ከተገነባባቸው አምስቱ መሰረቶች አንዱ ሲሆን በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ መፆሙ ግዴታ ነው።
:
የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
بُنِيَ الإِسْلامُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةِ أَنْ لا إِلَهَ إِلا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامِ الصَّلاةِ وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ وَالْحَجِّ وَصَوْمِ رَمَضَانَ
«እስልምና በአምስት ነገሮች ተገንብቷል
1) ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደ ሌለ እና ሙሐመድ መልዕክተኛው እንደ ሆኑ መመስከር፣
2) ሰላትን ቀጥ አድርጎ መስገድ፣
3) ዘካትን መስጠት፣
4) የአላህን ቤት መዘየር (ሐጅ ማድረግ) እና
5) የረመዷንን ወር መፆም።
*
የረመዷን ወር መፆም በምን ዐይነት ሰው ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው
ለአቅመ አዳም በደረሰ፣
ሰውነቱ እና አዕምሮው ጤነኛ በሆነ፣
ነዋሪ በሆነ (መንገደኛ ያልሆነ)፣
ከወር አበባ እና ከወሊድ ደም ነፃ በሆነች ሴት ላይ ግዴታ ይሆናል።
*
የረመዷን ወር እንኳን መጣላችሁ መባባል ሱና ነው እኔም ከወዲሁ ለናንተ
እንኳን መጣላችሁ ብያለው
*
ረመዷን 27 ቀን ይቀሩታል!
ደርሰው ከሚፆሙት እንዲሁም ፆመው ከሚጠቀሙበት ያድርገን!
:
ረጀብ 3, 1444 H.C

https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki