Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል: ረመዳን    ረመዳን የተከበ | Ethio Muslims ☪️

ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል:
ረመዳን
  

ረመዳን የተከበረው ወር ስያሜ መሆኑ ይታወቃል። ለመሆኑ ረመዳን ማለት ምን ማለት
ነው?

ረመዳን የሚለውን ስያሜ የቋንቋው ሊቃውንቶች በተለያየ መልኩ አብራርተውታል።
ከፊሎች ረመዳን (ረመደ ወይም ረምዳእ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ።
ይህ ማለት ደግሞ ጥማትና ረሀብን የሚያመጣ እጅጉን የበረታ ሀሩር (ሙቀት) ማለት
እንደሆነ አያይዘው ይገልፃሉ።
ሌሎችም ከዚህ ጋር ተቀራራቢ ባለው መልኩ አብራርተውታል።


ለምሳሌ ታላቁ ሙፈሲር ኢማሙል ቁርጡብይ :—
"ረመዳን እኮ የተባለው ወንጀሎችን
በመልካም ስራዎች አቃጥሎ አመድ ስለሚያደርጋቸው ነው።" በማለት አብራርተውታል።
ቁም ነገሩ:—
ማነው በዚህ በተከበረ ወር መልካም ስራዎችን አብዝቶ በመስራት አመቱን ሙሉ
ያከማቸውን ወንጀል አቃጥሎ አመድ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ!?

ረመዳን ቁርአን የወረደበት ወር
ረመዳን የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ️የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት
ረመዳን ሰይጣኖች የሚታሰሩበት ወር
ረመዳን ከሺህ ወር የምትበልጥ አንድ ሌሊት የያዘ ወር
ረመዳን ከምንጊዜውም በበለጠ ዒባዳ የሚደረግበት ወር
ረመዳን ፈርድ ስራዎቻችን በ 70 የሚባዙበት ሱናዎቻችን የፈርድን ዋጋ የሚያገኙልን ትልቁ
የረመዳን ወር ነው።

ረመዳን መጣ!!!!!!

እንግዲህ ጓዴ ሆይ፤
ሾይጣን ሊታሰር ነው፤ ረመዳን መጣ፤
መቼስ ሰው ነኝና፤
የበደልኩህ ካለ፤
አኡፉ በሉኝና!!!!!
እኔም ሸክሜ ይቅለል፤ አንተም ነጃ ውጣ።

         (((  ሬድዋን ሙስጠፈ )))

#እዚህ ቻናል አባላት ላይ ባለማወቅ ያስቀየምኳቹ  ፣ በምፅፈው ነገር ቅር የተሰኛቹ ወንድምና እህቶቼም ካላቹ ያው ካለማወቅ ካለመብሰል ሊሆን ስለሚችን አውፍ (ይቅርታ ) አድርጉልኝ ከልባቹ!!

#መልካም_ጁምዓ
   #ሼር_አድርጉት

https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki