Get Mystery Box with random crypto!

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የሰርጥ አድራሻ: @debre_markos_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-03-07 22:02:27
1.4K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:42:44 አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ምሁራዊ የፖለቲካ ገለልተኝነት እንዳለ ተጠቆመ

================

ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 27/2015 ዓ.ም| ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኔኬሽን ዳይሬክቶሬት |

በደብረ ማርቆስ ዪኒቨርስቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትም/ክፍል "#በአሁኗ_ኢትዮጵያ_ፖለቲካዊ_ተሳትፏችን_ምን _መምሰል_አለበት?" በሚል መሪ ሃሳብ ትምህረተ ጉባኤ አካሂደ፡፡

በትምህርተ ጉባኤው ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይኸይስ ሐረጉ አሁን የገጠመንን ችግር ለመጋፈጥ ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በመተው አንድነታችንን ማጠናከር ፤ የፖለቲካ አመራሮችን ቀርበን ማስተማርና ክፍተቶቻቸውን መሙላት እና ምሁራን እና አመራሮች ጠላቶቻችንን በጋራ መታገል እና ለመጪው ትዉልድ ሲባል መስዕዋትነት መክፈል እንደሚገባ ገልፀዋል። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምሁራዊ የፖለቲካ ገለልተኝነት እንዳለና ምሁራን ያገባኛል በሚል ስሜት ፖለቲከኞችን ቀርቦ ማገዝ እንዳለባቸውም ጨምረው ጠቁመዋል።

"#በአሁኗ_ኢትዮጵያ_ፖለቲካዊ_ተሳትፏችን_ምን _መምሰል_አለበት?" በሚል መሪ ሃሳብ ፅሁፋቸውን ያቀረቡት የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትም/ክፍል መምህር ዶ/ር መኮንን አለኸኝ፦
* የምሁራን ፓለቲካዊ ተሳትፎ አናሳ መሆኑን፤
* የአንድነትና የመለያየት ሃይሎች ትልቅ ትግል እያደረጉባት ያለች ሀገር መሆኗን
* ከ1960ዎቹ ጀምሮ ያለው የፖለቲካ ችግር የመደብ ወይስ የብሔር የሚለው ጥያቄ ያልተለየበት መሆኑን
* በኢትዮጵያ ፖለቲካ የምዕራባውያን ጫና ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን፤
* የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን ግልጽ አለመሆኑን፤ እና
* የፖለቲካ ተሳትፎን ጠንቅቆ ያለመረዳትና የመለየት ችግሮች በጉልህ መልኩ እንደሚስተዋሉ
* አለማቀፋዊ የሆኑ የፖለቲካ ጫናዎች እንደሚስተዋሉ በሰፊው በመግለፅ የሚከተሉትን የመፍትሔ ሀሳቦችም ጠቁመዋል።

* የፖለቲካ ፖርቲዎች ተሳትፎቸውን ማሳደግ እንደሚገባ
* የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ምሁራን ተቀራርቦ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ፤
* ስለ አገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በቂ መረጃና ግንዘቤ መያዝ እንደሚገባ ፤
* ማንኛውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች መደገፍ እንደሚገባን እና በግል ወይም በቡድን ፖለቲካዊ ተሳትፎአችንን ማጠናከር እንደሚገባ በመግለፅ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል ።

በመጨረሻም በቀረበው መነሻ ፅሁፍ ላይ ሰፊና ጥልቅ ወይይት ተደርጎበት ትምህረተ ጉባዔው ተጠናቋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

=============

ለተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች



#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
3.7K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:42:31
3.5K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 11:30:11 ለአዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

============

ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 25/2015 ዓ.ም| ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኔኬሽን ዳይሬክቶሬት

ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፣ወጣቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ዳይሬክቶሬት በ2015 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች በትናንትናው ዕለት የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በህይወት ክህሎት ስልጠናው ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ የስልጠናውን አስፈላጊነትና ዓላማ ገለፃ ያደረጉት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፣ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላም መክብብ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲያችን የተመደቡ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ለቀጣይ ህይወታቸው ስንቅ የሚሆናቸውን ቁም ነገር ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ጠቁመዋል።

የዚህ ስልጠና ዋና ዓለማም ተማሪዎች በራስ የመተማመን ስሜት እንዲያዳብሩ ፣ የሌሎችን ሀሳብ እንዲያከብሩ ፣ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ ክህሎት እንዲያጎለብቱ፣ መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ ፣የአቻ ግፊትን እንዲቋቋሙ እና በአጠቃላይ ተማሪዎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነም አክለው ገልፀዋል።

ይህ የህይወት ክህሎት ስልጠና ለሁሉም አዲስ ገቢ ሴትና ወንድ ተማሪዎች በተጠናከረ መልኩ ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል ፡፡

በስልጠና መረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች የህይወት ተሞክሯቸውን ያካፈሉት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ስነ ሰብ ኮሌጅ የአማረኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል መምህርት ወይዘሮ ሀይማኖት እጅጉ እንደገለጹት እንደ ሃገር አሁን እታየ ያለውን ውዥንብር በጥልቀት በመረዳት ተማሪዎች ለመጡበት ዓላማ ብቻ ትኩረት በመስጠት ራሳቸውን ከአልባሌ ቦታ መቆጠብ ፣ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም፣ ጓደኛን መምረጥና የአቻ ግፊትን በመቋቋም ራሳቸውን በዕውቀትና በአመለካከት ብቁ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ተማሪዎችን በዕውቀት ማነጽና ማስታጠቅ ተገቢ በመሆኑ እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎችና ውይይቶች ተጠናከረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም አክለዋል ፡፡

በህይወት ክህሎት ስልጠናው ተሳታፊ የነበሩት ተማሪ ማስተዋል ፈቃዱና ቃል ኪዳን ይታየው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከአቀባበል ጀምሮ ያደረገላቸው መስተንግዶ እንዳስደሰታቸው ገልጸው የዛሬው የህይወት ክህሎት ስልጠና ደግሞ ለቀጣይ ህይወታችን መሰረት የሚሆነን ብዙ ቁምነገርና ስንቅ ያገኝንበት ስልጠና ነበር ሲሉ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል። በቀጣይም ይህን የወሰድነውን ስልጠና ተግበር ላይ በማዋል ለመጣንበት ዓላማ ብቻ ትኩረት በማድረግ በትምህርታችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል ብለዋል። ሀገራችንና ቤተሰቦቻችን ከእኛ ብዙ ይጠብቃሉ ፤ የተሰጠን የህይወት ክህሎት ስልጠናም ጥሩ ስንቅ ይሆነናል በማለት ሀሳባቸውን አጋርተውናል ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

=============

ለተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች


#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
2.7K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 11:30:01
2.5K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:34:22 የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲከፍተኛ አመራሮች በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

=============
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 24/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |

የደብረ ማረቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር)፣ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ይኸይስ አረጉ (ዶ/ር) እና የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አስካለ ማርያም አዳሙ (ዶ/ር) እንዲሁም ከአማራ ክልልና ከደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የትምህርት መምሪያ ሃላፊዎች በተገኙበት የተክለሃይማኖት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና ኢትዮ ጃፓን ደብረ ማርቆስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

በዚህ መርሃ ግብር በትምህርት ቤቶቹ ግቢ ውስጥ የሚገኙ አረንጓዴ ተክሎች ፣ ቤተ-ሙከራ ክፍሎች፣ የፈጠራ ስራዎች፣ የመረጃ አደረጃጀቶች፣ የልዩ ፍላጎት ትምህርትና ስልጠና እና ድጋፍ አሰጣጥቶች እና እንዲሁም የምርምር ማዕከላት ተጎብኝተዋል።


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ልዩ ተግባራት በትብብር እየሰሩ እንደሆነ የዛሬው የጉብኝት መርሃ ግብር አመላካች ነው።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ


=============

ለተጨማሪ መረጃዎች


#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
1.3K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:34:10
1.2K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:34:08
1.1K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:34:03
1.1K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 12:27:28 127ኛው የአደዋ ድል በዓል መታሰቢያ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሐዲስ ዓለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከበረ

==============
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 23/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |

"አንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት" በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚህ በዓል የምስራቅ ጎጃም ዞን የስራ ኋላፊዎቸ ፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር እና የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና ተማሪዎች እና እንዲሁም የዩኒቨርስቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈውበታል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ በንግግራቸውም ከአድዋ ጀግኖች የተማርነው ርህራሄ ፣ የአመራር ጥበብ፣ የአንድነት መንፈስ ፣ ነፃነትና እኩልነትን መሆኑን ጠቁመው የአሁኑ ትውልድ የጀግኖች አባቶቹን ፈለክ መከተል እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ረ/ፕሮፈሰር ግዛቸው አንዳርጌ የዓድዋ ድልን በተመለከተ ከመነሻ እስከ ፍፃሜው የነበረውን ታሪካዊ ሁነት የሚያስቃኝ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል።
እንደ ተመራማሪው ገለፃ የካቲት ወር ለኢትዮጵያ በጣም በብዙ ነገር ታሪካዊ ወር እንደሆነ የታሪክ መዛግብቶችና ድርሳናት እንደሚያመላክቱ ጠቁመዋል። ይካቲት 12 ግራዚያኒ አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የፈጸመበት ወቅት በመሆኑ ፤ ይካቲት 23 ደማቁን ያአደዋ ድል ያስመዘግንበት መሆኑ ፤ የካቲት 26 ወራሪው የዚያድባሬ ጦር በካራ ማራ ላይ ድል ተደርጎ የተመለሰበት ወር መሆኑን ለአብነት ጠቅሰው ባጠቃላይ የካቲት ወር የኢትዮጵያ ትንሳዔ ወር ነው ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይኸይስ አረጉ የበዓሉን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የዓድዋ ዘመን ጀግኖች እነሱ ለማይኖሩበት ዓለም መስዋዕትነት ከፍለውልን እኛ በነፃነት እንድንኖር አስችለውናል። በመሆኑም የታሪክ ምሁራን ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን ወጣቱን ትውልድ መቅረፅ ፣ እውነትን መመስከር ፣ ማስተማርና ማንቃት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ከትውልዱ ደግሞ ደፍሮ መማር እና ማወቅ ፣ የአድዋን ዘመን ጀግኖች መንፈስ መላበስ እንደሚጠበቅ በአንክሮ ገልፀዋል።


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ


=============

ለተጨማሪ መረጃዎች


#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
1.6K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ