Get Mystery Box with random crypto!

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የሰርጥ አድራሻ: @debre_markos_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-08-21 15:22:17 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በሁለት የፈጠራ ስራዎች ዘርፍ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የምስክር ወረቀት አገኘ
===================

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ :- ነሐሴ 15/2014 ዓ.ም (ደማዩ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከ"እንሰት" የሚሰራ ጠላና አዘገጃጀት እና እንዲሁም ከ"እንሰት" የሚሰራ አረቂና አዘገጃጀት ዘርፎች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአዕምሯዊ ባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቶችን ማግኘቱን የዩኒቨርሲቲያችን የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስርናቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፈ ይበልጣል ታረቀኝ አሳውቀውናል።

ከዳይሬክተሩ ባገኘነው መረጃ መሰረት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የእነዚህ ሁለት የፈጠራ ስራ ባለቤት ሊሆን የቻለው የፈጠራ ስራ ምርምር ካደረጉት መምህርና ተመራማሪ አቶ ባወቀ ጥሩነህ ጋር በትብብር በተሰራ የምርምር ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል ።

ይህ ፈጠራ ስራ ውጤት እውን እንዲሆን በዩኒቨርሲቲው የአዕምሯዊ ንብረት ፖሊሲ መሰረት በምርምር ሂደቱ ወቅት የሚያስፈልጉ የቤተ ሙከራ፣ የተመራማሪ እና ሌሎችም ለሂደቱ አስፈላጊ ወጭዎችን በሙሉ ዩኒቨርሲቲው የሸፈነ ሲሆን ተመራማሪው በበኩሉ ደግሞ የፈጠራ ሀሳቡንና ዝርዝር ሂደቱን በተመለከተ ሙያዊ ደረጃውን የጠበቀ የፕሮጀክት እቅድ በማቅረብ በትብብር እንደተሰራና ዩኒቨርሲቲያችንም የፈጠራ ስራው ባለቤትነትን ማግኘት እንደቻለ ረ/ፕ ይበልጣል ታረቀኝ ጨምረው ገልፀዋል።

በመጨረሻም እንደዩኒቨርሲቲ በዚህ የፈጠራ ስራ ዘርፍ በተገኘው ምስክር ወረቀት መደሳተቸውን ገልፀው ሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ተመራማሪ ማህበረሰብ ደረጃቸውን የጠበቁና ከዚህ በፊት በሌላ አካል ያልተሰሩ የፈጠራና ምርምር ስራዎቻቸውን ለዩኒቨርሲቲው እያቀረቡ በጋራ እንድንሰራ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ይህ የፈጠራ ስራ ሙሉ በሙሉ ወደተግባር ሲገባ በተለይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለምንም አገልግሎት እንዲሁ የሚታወቀውን የእንሰት ተክል በሰፊው እንዲመረትና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ የሚያስችል የምርምር ውጤት እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

ከታች ያስቀመጥናቸው የዩኒቨርሲቲያችን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር አድራሻዎች ናቸው። ተራ በተራ ሊንኮቹን እየተጫናችሁ ትወዳጁን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን



ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ዌብሳይት www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"

ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን
6.2K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 15:22:13
5.3K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 10:53:11
Notice
6.8K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 17:14:07 የተወደዳችሁ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂዎች ፣ ይህ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የተከፈተ ይፋዊ የዩኒቨርሲቲያችን የቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ማህበር ቡድን ( Debre Markos University Alumni Association Group ) መሆኑን ስንገልፅላችሁ በደስታ ነው። ይህ ግሩፕ ከቀድሞ ተራቂዎቻችን ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና መረጃዎችን ለመለዋወጥ እንድንችል ታስቦ የተከፈተ ግሩፕ ነው።

በመሆኑም በየትኛውም አመተ ምህረት፣ በማንኛውም መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲያችን ተመርቃችሁ በስራ ዓለም ላይ ያላችሁም ሆነ ስራ ለመቀጠር በመፈለግ ላይ የምትገኙ ወይም የራሳችሁን ስራ ፈጥራችሁ እየሰራችሁ ያላችሁ ሁሉ የዚህ ቡድን አባላት መሆን የምትችሉ ስለሆነ ወደ ግሩፑ እንድትቀላቀሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ( ነሐሴ ፦ 12/2014 ዓ.ም )

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ !

ግሩፑን ለመቀላቀል ከታች ያስቀመጥነውን ሊንክ ይጫኑ



https://www.facebook.com/groups/604704201179469/

https://t.me/dmu_pralmuni2014
7.2K viewsedited  14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 13:41:16 በግንባታ ግዥ፣ በምክር አገልግሎት ግዥ (Consultancy Service) ፣ በውልና በንብረት አስተዳደር እንዲሁም አወጋገድ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ
===========================
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፡- ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም (ደ.ማ.ዩ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በሀገራችን ከ16 ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የግዥ እና ንብረት አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የግዥ አፅዳቂ ኮሚቴዎች የተሳተፉበት በዩኒቨርሲቲዎች አከባቢ የሚታዩ የግንባታ ግዥ፣የምክር አገልግሎት ግዥ፣ውል አስተዳደር እና በንብረት አስተዳደርና አወጋገድ ዙሪያ ከነሐሴ 4 እስከ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 4 ቀናት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሐዲስ ዓለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ ከኢፌዲሪ ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመጡ አሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ዝርዝሩን ለመመልከት



ዌብሳይት www.dmu.edu.et

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"

ከእኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
7.4K viewsedited  10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 13:40:43
6.2K views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 15:19:39
2.4K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:19:21
3.3K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:18:12 “ግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም” እና “የሕይወት ቃርሚያ” በሚል ርዕስ የተደረሱ ሁለት መጽሐፍት ተመረቁ

====================

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰኔ 28/2014 ዓ.ም ( ደ.ማ.ዩ. ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ድሬክቶሬት ) በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በማሀበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ በአማርኛ ቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ በድሉ አዳም “ግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም” እንዲሁም በዲያቆን አሻግሬ አምጤ “የሕይወት ቃርሚያ” በሚል ርዕስ የተደረሱ ሁለት መጽሐፍት የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች፣የአካባቢዉ ማህበረሰብ አካላትና የደራሲዎቹ ቤተሰቦች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡


በዩኒቨርሲቲያችን የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ.ር አማረ ሰውነት የመጻሕፍቱን መመረቅ በማስመልከት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸዉም የግአዝ ቋንቋ በሀገራችን ትልቁን ታሪክ መዝግቦና ሰንዶ የያዘ ቋንቋ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ህልውናዋ ነዉ ብለዋል፡፡ ካለ ግእዝ ኢትዮጵያ ከየት ተነስታ የት እንደደረሰች ማወቅ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ግእዝ የኢትዮጵያን ሚስጢራት በትልቁ ጨምቆ የያዘ ቋንቋ በመሆኑ፡፡ የግዕዝ ቋንቋ መፈላሰፊያችንና ታሪካችንን የምናውቅበት ቋንቋ ነው፡፡ በመሆኑም ታሪካችንን ለማወቅ ሀገራችንን ለማሳደግ የግእዝን ቋንቋ መማር ማወቅ ማሳደግ ይገባል ፤ስለሆነም በዛሬው ዕለት ለመመረቅ የበቃው ይህ የግዕዝ አማረኛ ቃላት ለሁሉም ቋንቋውን ለማሳደግና ሚስጢራትን ለማወቅ የማይተካ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡


በሌላ መልኩ በደራሲ ዲያቆን አሻግሬ አምጤ የተደረሰው የሕይወት ቃርሚያ የተሰኘው መጽሐፍ ትውልዱ ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ መልካም እሴቶችን ጠብቆ እንዲይዝና ወደ ማንነቱ እንዲመለስ በሚያግዝ መልኩ የቀረበ መጽሐፍ በመሆኑ ጠቀሜታዉ የጎላ እንደሚሆን እተማመናለሁ፡፡ ስለሆነም የሁለቱም መፅሐፍት ደራሲያን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡


ግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም በተሰኘዉ መጽሐፍ ላይ መምህር ሰናይ ታረቀኝ፣ የሕይወት ቃርሚያ በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ደግሞ ዶ.ር አራጋው አንተነህ ሙያዊ ዳሰሳ አድርገዉበታል፡፡


መምህር በድሉ አዳም የግእዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም መፃፍ ደራሲ እንደገለፁት ከዋናዉ የመማር ማስተማር ስራዬ በተጨማሪነት የግእዝ ቋንቋን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሳስተምር ተማሪዎቼ ቋንቋዉን ለማጥናት ሲቸገሩ በማየቴ ችግሩን ለመቅረፍ በማሰብ ይህን መፅሀፍ ለማዘጋጀት እንደተነሳሱ ገልፀዋል፡፡ የግእዝ ቋንቋን መማር የኢትዮጵያን ጥበብ ፈልፍሎ ለማውጣት ትልቅ አቅም እንዳለዉና የዚህ መፅሐፍ መታተምም አንድም ለተማሪዎች እንደማጣቀሻ ያገለግላቸዋል በሌላ በኩልም የግእዝ ቋንቋን ለማሳደግ ብዙ ፍይዳ እንደሚኖረዉ አስረድተዋል፡፡


በሌላ በኩል የህይወት ቃርሚያ የተሰኘው መፅሐፍ ደራሲ ዲያቆን አሻግሬ አምጤ እንደገለፁት መጽሐፉ በዋናነት የቀደሙ አባቶቻችንን አኗኗር ዘይቤ፣ መልካም እሴቶችንና ትውፊቶችን መሠረት አድርጎ እንደተፃፈ ገልፀዋል፡፡ ታሪክን ፣ ስነ- ፅሑፍን ፣ ስነ- ምግባርን ፣ ስነ-ልቦናን ህግና ፍትህን ለሰዎች መልካም ማድረግን ርህራሄንና ሌሎችንም እየጠፉ ያሉ መልካም ነገሮችን መመለስ እንደሚያስፈልግና ሀገራችን የተጋረጠባትን የባህል ወረራ ፣ የማንነት ጥያቄና የዕውቀት ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ በምረቃ ፕሮግራሙ ስነ ፅሑፍ ና ልዩ ልዩ ቅኔዎችም ቀርበዋል።
4.3K viewsedited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:18:08
3.8K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ